የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ውይይት ያለ ውጤት ተጠናቀቀ

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 1 ก.ค. 2024
  • የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታዬ አጽቀስላሴ እና የሶማሊያ አቻቸው አህመድ ሙዓሊም ፊቂ በቱርክ አንካራ ያደረጉት ውይይት ያለ ውጤት ተጠናቀቀ። ሁለቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በመጪው ነሐሴ መጨረሻ ዳግም ለመገናኘት መስማማታቸውን አስታውቀዋል።
    ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር በተፈራረመችው የመግባቢያ ስምምነት ምክንያት ከሀገሪቱ ጋር ውዝግብ ውስጥ የገባችው ሶማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯን ወደ አንካራ የላከችው፤ በቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሐካን ፊዳን ግብዣ ነበር። የውይይት ግብዣውን የተቀበሉት ሁለቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፤ በአንካራው ውይይት ፊት ለፊት ተገናኝተው እንዳልተነጋገሩ በቱርክ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በኩል የወጣው መግለጫ ይጠቁማል።
    ሚኒስትሮቹ ትላንት ሰኞ ሰኔ 24፤ 2016 በቱርክ አመቻቺነት ባደረጉት ውይይት፤ ልዩነቶቻቸውን በሁለቱም ተቀባይነት ባለው ማዕቀፍ ለመፍታት “ቅን፣ ልባዊ እና ወደፊት የሚመለከት” የሃሳብ ልውውጥ ማድረጋቸውን መግለጫው አመልክቷል። የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ማክሰኞ ሰኔ 25፤ 2016 ባወጣው አጭር መግለጫ፤ በውይይቱ “ግልጽ እና ወዳጅነት የተሞላበት የሃሳብ ልውውጥ” እንደተደረገ አረጋግጧል።
    የአንካራው ውይይት “በሁለቱ አገራት መካከል ላሉ አለመግባባቶች መፍትሔ በሚያመጡ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ” እንደነበርም ሚኒስቴሩ በመግለጫው ጠቅሷል። አምባሳደር ታዬ እና የሶማሊያው አቻቸው አህመድ ሙዓሊም በሁለቱ ሀገሮች መካከል ያሉ “አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ እልባት ለመስጠት” መስማማታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
    ሚኒስትሮቹ “መልካም ጉርብትናን እና ቀጠናዊ መረጋጋትን ከግምት በማስገባት መፍትሔዎችን ለማመላከት ያለሙ ምክክሮች ለመቀጠል” መስማማታቸውን የቃል አቀባይ ጽህፈት ቤቱ መግለጫ ይጠቁማል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ ሁለተኛ ዙር ውይይት በመጪው ነሐሴ 27፤ 2016 በዚያው በአንካራ የሚካሄድ ይሆናል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
    የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ትኩስ ዜናዎችን እና ወቅታዊ ዘገባዎችን ለመከታተል፦
    ድረ ገጽ ፦ ethiopiainsider...​
    ፌስቡክ ፦ / ethiopiainsider
    ትዊተር (ኤክስ) ፦ / ethiopiainsider
    ቴሌግራም፦ t.me/EthiopiaI...
    ቲክቶክ፦ / ethiopiainsider

ความคิดเห็น •