15 - የእንግሊዝ እስራኤላዊነት (British Israelism) ምንድነው? (በዶ/ር መስከረም ለቺሣ) Dr. Meskerem Lechissa

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 23 พ.ย. 2023
  • • የእንግሊዝ እስራኤላዊነት (British Israelism)፥ ወይም የእንግሊዝ ጽዮናዊነት (British Zionism) እንቅስቃሴ ምንድነው?
    • ምን ማለት ነው?
    • ሃሳቡ መቼ ተጀመረ?
    • ማን ጀመረው?
    • አሁንስ ምን ላይ ነው?
    • ምን ዓይነት ዓለም አቀፍ ተጽዕኖ አለው?
    • ከእኛ (ከኢትዮጵያውያን) ጋርስ ምን ያገናኘዋል?
    ዋቢ መጻሕፍት (References)፦
    የብሉይና የሓዲስ ኪዳን መጻሕፍት
    ዶ/ር መስከረም ለቺሳ (2008 ዓ.ም)። (ኢ)ዩቶፕያ። አዲስ አበባ፥ አፍሪካ ማተሚያ ቤት።
    Allen, J.H. (1917). Judah's Sceptre and Joseph's Birthright (16 ed.). Haverhill, MA: Destiny Publishers.
    Armstrong, H. W. (1967). The United States and Great Britain in Prophecy. World Wide Church of God, 1973(1975), 1980.
    Beaumont, C. (1946). Britain Key to World History. Britain: William Brendan & San.
    Burgess, Thomas. Tracts on the Origin and Independence of the Ancient British Church: On the Supremacy of the Pope, and the Inconsistency of All Foreign Jurisdiction with the British Constitution; and on the Differences Between the Churches of England and of Rome. FC and J. Rivington, 1815.
    Devlin, H. (2018). First modern Britons had ‘dark to black skin’, Cheddar Man DNA analysis reveals. The Guardian, 7.
    Elder, I. H. (1947). Celt, Druid and Culdee. Covenant Publishing Company.
    Hexham, Irving (2001). "British Israelism". In Elwell, Walter A. (ed.). Evangelical Dictionary of Theology (2 ed.). Grand Rapids, MI: Baker Book House Company. p. 187.
    Hine, Edward (1874). Forty-Seven Identifications of the British Nation with the Lost Ten Tribes of Israel: founded upon Five Hundred Scripture Proofs. London.
    Murray, B. H. (2020). Jeremiah in Tara: British Israel and the Irish past. In Chosen peoples (pp. 88-108). Manchester University Press.
    Odlum, E. (1916). God's Covenant Man: British-Israel.[Based on Prophecies in the Bible]. Robert Banks & Son.
    Saddler, J. (1649). Rights of the Kingdom or Customs of our Kings and Parliaments. London: Kidgell.
    "The Ark at the seat of kings" (www.irishtimes.com/news/the-a... 282). The Irish Times. Retrieved 13 November 2023.
    “The British-Israel-World Federation - Beliefs”. British-Israel-World Federation. Retrieved 6 August 2023 from www.britishisrael.co.uk/belie...
    Wild, Joseph (1888). The Future of Israel and Judah: Being the Discourses on the Lost Tribes from How and when the World Will End. Nabu Press.
    Wilson, J. (1850). Our Israelitish Origin. Daniels & Smith.
    * * *
    የዶ/ር መስከረም ለቺሣን መጻሕፍት ለማግኘት፦ አገር ውስጥ፦ አራት ኪሎ፡ ገለን ሕንጻ (ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ቀጥሎ፤ ወይም ቅዱስ ፕላዛ ፊት ለፊት) ሦስተኛ ፎቅ፡ ሱቅ/ቢሮ ቁጥር 303 ጎራ ይበሉ። 0978212223
    የፀሓይ ከተማ - "City of the Sun"
    (ኢ)ዩቶፕያ - (E)Utopia

ความคิดเห็น • 323

  • @tsionwistienat4604
    @tsionwistienat4604 8 หลายเดือนก่อน +8

    እግዚኦ!! የሚገርም የሚደንቅ ነው!!!
    ስንት የማናውቀው ታሪክ እንዳለ ይህ በደንብ ያሳያል::
    ኢትዮጵያና ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ምቀኞቻቸውና ተፎካካሪዎቻቸው አበዛዛቸው!!
    እኛም ሰነፎች ነን:: ያለንን የማንገነዘብ::
    ጸጋውን ያብዛልሽ!!! ይጠብቅሽ!!!

  • @legesse8909
    @legesse8909 8 หลายเดือนก่อน +38

    ዶ/ር መስከረም፣ አመሰግናለሁ። ተማርኩበት፣ ተመሳሳይ ነገር አጋጥሞኛል፣ ከአንድ ፊንላንዳዊ ጋር ተከራከርን ነገር ግን ባለመስማማት ተስማምተን ተለያየን። ማንነትን ዘርፈውናል ለካ አልኩኝ። አይገርምም! ብዙ ነገር ተማርኩኝ፣ ተባረኪ ዶ/ር።

  • @tibebemenkir2893
    @tibebemenkir2893 8 หลายเดือนก่อน +15

    ዶ/ር እንኳን በደህና መጡ። በዚህ በሆድ አደር ዘመን ጥቂት የአርስዎ ዓይነት አስተማሪ ምሁራን በመኖራቸው እድለኞች ነን። ስለ አኢትዮጵያዊ ማንነታችን፣ ስለሀገራችን ባህል አና ታሪክ: ስለ ሀገራችን ጥንታዊ መንፈሳዊነት፣ ትልቁን የመደምሰስ ሥራ ግልጽ በሆነ መንገድ የምንሰራው አጥፊዎቻቸ‍እንን እየረዳን ያለን እኛው ኢትዮጵያውያን ነን። እነሱ ሥራቸውን ሰርተው ጨርሰዋል። ኢትዮጵያን የሚያጠፉ ኢትዮጵየአውያን አምርተው ጨርሰዋል ያመረቱትን ተኝተው እየበሉ ነው። መድኃኔዓለም በአለቀ ሰዓት መድረስ የሚያውቅበት በማያልቀው ቸርነቱ :ምሕረቱ ከወደቅንበት ጨለማ ያንሳን ይታደገን። መድኃኔዓለም አሁንም ሁልግዜም ኃይሉን ብርሀኑን ያፍስልዎት ብርታቱን ይስጥወት።

  • @user-qy2ox8lw7f
    @user-qy2ox8lw7f 8 หลายเดือนก่อน +12

    ዶ/ር መስከረም ለቺሳ @"Utopia meadia" ቃላት የለኝም ዶ/ር ስለ አንቺ የኢትዮጵያን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ! ህዝቤ ሆይ ንቃ አዚሙ ይልቀቀን የእመ አምላክ ምልጃ ያግዘን መድሐኒአለም ማስተዋሉን አድለን።

  • @birhanieayalew8908
    @birhanieayalew8908 8 หลายเดือนก่อน +7

    በጣም ነዉ የሚገርመዉ ፈረንጅ ጥሩ ነዉ ብሎ የገመተዉን ታሪክ የኔ ነዉ ከማለት ወደ ኋላ አይሉም የተሰራዉን ሥራም ለመቀማት አይታቀቡም ታሩኩ እራሳቸዉ ይሰሩታልስግብግብ ናቸዉ ዘራችን ናቸዉ ካሉ ምነዉ በጀርመን ያን ያህል ግፍ የሰሩባቸዉ እንደ እዉነቱ ከሆነ ለእስራኤላዊነት ከነሱ ኢትዮጵያ ትቀርባለች እነሱ ግን መስማት አይፈልጉም

  • @user-qb8su6gv2r
    @user-qb8su6gv2r 8 หลายเดือนก่อน +16

    ገና ብዙ መጽሐፎችን ካንቺ እንጠብቃለን በእውነት በርቺልን እግዚአብሔር ይጠብቅሽ

  • @andud9200
    @andud9200 8 หลายเดือนก่อน +8

    ዶ/ር መስከረም እግዚአብሔር ይስጥልን አሁንም ዕዉቀትሽን ያብዛልሽ ሌላዉ አንድ መጨረሻ ላይ የጠቀስሻት ልጅ አክሱም ዩቱብ ላይ የምታቀር ልጅ ብዙ ነገሮችን ሳታዉቅ ነዉ የምታቀርበዉ ስለዚህ ይህ ለሷ ለመማር ጥሩ አጋጣሚ ነዉ ከሰማች

  • @YonasAklilu-ip6ej
    @YonasAklilu-ip6ej 8 หลายเดือนก่อน +7

    ❤🎉❤🎉🎉 ተባረኪ አንደኛ ነሽ

  • @ethiopianorthodoxtewahdoki5308
    @ethiopianorthodoxtewahdoki5308 8 หลายเดือนก่อน +8

    እረ በጣም ጠፋሽ እህታችን ፣ እንኳን በሰላም መጣሽ ❤❤❤

  • @kasstubetruth7756
    @kasstubetruth7756 8 หลายเดือนก่อน +19

    በእውነት ሴት ልጄ እግዚአብሔር እንዳንች አይነት ሀገር ወዳድ እውነተኛ ሃይማኖተኛ እንዲያደርግልኝ እለምነዋለሁ🙏 በጣም ነው የማከብርሽ ዶክተር🙏🙏🙏

  • @Hailye-fd8th
    @Hailye-fd8th 8 หลายเดือนก่อน +5

    አስተማሪና አንቂ የሆነ ገለጻ ከነ ማስረጃው አቅርበሽልናል!! በርችልን ዶ/ር መስከረም
    በቅድስት ቤተክርስቲያን ውስጥ የተሠገሰጉ መምሕራን ውጫዊ ቆዳ ቀለማቸው ዕኛን መሣዮች : አስተሳሠባቸው ግን በአውሮጳ አስተምሮ የተጠመቁ ዕንደሆነ ዕየተገለጠ ነው::
    ዕነዚሕ ነጣቂ ተኩላዎች ድፍረታቸው የበዛ ነው!! የተዋሕዶ ዕምነታችን ለመሸርሸር እየሠሩ ያሉና ባለንበት ዘመን ደግሞ ከቀደምት ታሪካችን ገፍተው ለማራቅ ወደ መድረክ ብቅ ብለዋልና ትውልድ ሆይ ንቃ ! በመንፈሳዊ ዕውቀት በኩል ሞግት

  • @YemsrackDegaf
    @YemsrackDegaf 8 หลายเดือนก่อน +5

    ናፍቀንሻል 😭😭
    ተሎ ተሎ ነይልን የእውቀት እናታችን 😭😭

  • @ablove3257
    @ablove3257 8 หลายเดือนก่อน +6

    እንኳን በደህና መጣሽ በእዉነት ስትጠፊ እንደ ስጋ ዘመዴ ነዉ ምን ሆና ይሆን ብዬ የተጨነኩት።

  • @tsionpetros4979
    @tsionpetros4979 8 หลายเดือนก่อน +10

    እንኳን ደህና መጣሽ እህታችን እንደዚህ በማስረጃ የተደገፈ ታሪክን እንድናውቅ ስለረዳሽን ከልብ እናመሰግናለን!
    "እውነት ተሸፍና አትቀርም"

  • @user-iw2pr8sl4p
    @user-iw2pr8sl4p 8 หลายเดือนก่อน +15

    እጅጉን፡ እግዚአብሔር፡ ይስጥልን፥ ዶ/ር፡ መስከረም🙏🙏🙏

  • @bethelephrata7487
    @bethelephrata7487 8 หลายเดือนก่อน +7

    ዶ/ር በየቀኑ ስፈልግሽ ስፈልግሽ ነበር !! እንኳን ደህና መጣሽ !! ደስ ብሎኛል !! አሁን ወደ ትምህርት ገለጻው ልግባ !!

  • @etalembekele8831
    @etalembekele8831 8 หลายเดือนก่อน +8

    ፀጋውን ያብዛልሽ የእኔ እህት 🙏🙏🙏

  • @yo16685
    @yo16685 8 หลายเดือนก่อน +30

    በርቺልን !!
    እንደዚህ አይነት በማስረጃ የተደገፉ መግለጫዎች ናቸው ሃገራችንን እና ቤተክርስትያናችንን በጥንካሬ ልንከላከል የሚያስችለን መንገድ።

  • @maneaylegne3354
    @maneaylegne3354 8 หลายเดือนก่อน +7

    ዶክተር እንኳን ደህና መጣሽ

  • @bemnethailu1663
    @bemnethailu1663 8 หลายเดือนก่อน +9

    አረ ውድ እህታችን በእውነት በጣም ሳስብሽ ነበረ ጠፍተሽብን ነው እኮ 🙏 እና ባለፈው የጃዕፈር መጽሐፍ መደብር በፌስ ቡክ አይቸው ስለ አጼ ዘርአብሩክ እና አባ እስጢፋኖስ የሚል መጽሐፍ አለ የሚል አይቼ አንቺን አስታወስኩሽ እና ጠፋሽብን በሰላም ነው 🙏

  • @simretkebede3349
    @simretkebede3349 8 หลายเดือนก่อน +7

    እግዚያብሔር ቀሪ ዘመንሽን ይባርክ ዶ/ር!!!

  • @wutmahotel9679
    @wutmahotel9679 8 หลายเดือนก่อน +6

    እንደው ዶክተር የተባረክሽ ነሽ

  • @mollagedamu679
    @mollagedamu679 8 หลายเดือนก่อน +6

    ዶ/ር እናመሰግናለን ። እንግሊዞች ይህንን ተረት መናገር የፈለጉት ወደፊት የሐሳዊ መሲሕ መስራቾች ሰለሆኑ አኛ ጥንታዊ ክርስቲያን ነን አሁን የምንላችሁን ሐሳዊ መሲሕን መሆኑ ነው ተቀበሉ ብለው ለመናገር እንዲመቻቸው ያደረጉት የተንኮል ሴራ ነው። ስለዚህ እኛ ኢትዮጵያዊ ያን ልንነቃና ልንነጠቅ ይገባል።

  • @zenebechdemessia7852
    @zenebechdemessia7852 8 หลายเดือนก่อน +4

    Well came doctor

  • @hundetafa4450
    @hundetafa4450 8 หลายเดือนก่อน +9

    ብቻ እንኳን ደህና ሁነሽ ተመለስሽልን ! እኔስ ፀረ ኢትዮጵያ ኃይሎች ተፅናወኑሽ ብዬ ፈርቼ ነበር ::
    God bless you sis !!!

  • @user-dr6xe7dw2l
    @user-dr6xe7dw2l 8 หลายเดือนก่อน +12

    ፅጋውን አብዝቶ ይስጥልን በእውነት

  • @user-kn2dn5yb4n
    @user-kn2dn5yb4n 8 หลายเดือนก่อน +4

    እድሜና ጤና ይስጥልኝ ዶክተር፣ ሰሚ ካገኙ ምልከታችንን ማስተካከል የሚችሉ ሃሳቦችን ነው ሁሌም ምታነሽው ፣ክብር ይስጥልን ።

  • @m.t2022
    @m.t2022 8 หลายเดือนก่อน +9

    እጅግ መልካም ጠቃሚ የሆነ ትምህርት ነው የሰጠሽን፡
    እናመሰግናለን።

  • @admasugele7463
    @admasugele7463 7 หลายเดือนก่อน +1

    ፈጣሪ እድሜና ጤናውን ጨምሮ ይስጥሽ የማላውቀውን አሳወቅሽኝ አመሰግናለሁ ❤

  • @user-lf2zg1zz9m
    @user-lf2zg1zz9m 8 หลายเดือนก่อน +4

    ዶክተር እንኳን በደህና መጣሽ ቤተሰቦችሽ ሁሉ ደህና ናቸው አሁንም እግዚአብሔር ይጠብቅሽ ከነ ቤተሰብሽ ምነ እንዳልሽ እንኳን አልሰማሁሽም ብቻ አየኢትዮጵያ እውነተኛ ልጅ ስለሆንሽ አከብርሻለሁ

  • @hilinayoutube590
    @hilinayoutube590 8 หลายเดือนก่อน +3

    ዶ/ር መስከረም እናመሰግናለን እግዚአብሔር ይስጥልኝ

  • @andombirhane4772
    @andombirhane4772 7 หลายเดือนก่อน +1

    እግዚአብሔር ምስክር ይሆኑት ዘንድ በየዘመኑ ህዝብን ያነቁ ዘንድ ሰው ያስነሳል።መስኪ እህታችን ዘመንሽን ቤተሰብሽንና ይኸንን ዐይምሮሽን እግዚአብሔር ይባርክ።

  • @bamatube7
    @bamatube7 8 หลายเดือนก่อน +3

    ዶ/ር ሰላም ነው???? በጣም ናፍቀሽኛል በእውነት። ምነው በሰላም ነው የጠፋሽው????? እስከ ሁለት ወር ድረስ ጠፋሽ። እና ቶሎ ቶሎ ነይልን ።❤

  • @user-zz8dx6si9n
    @user-zz8dx6si9n 8 หลายเดือนก่อน +4

    እንኳን ደሕና መጣሽ መስኪ

  • @GebrelaTed
    @GebrelaTed 8 หลายเดือนก่อน +4

    እንኳን ደና መጣሽ መስኪዬ

  • @user-us4vf5hb7v
    @user-us4vf5hb7v 7 หลายเดือนก่อน +1

    ዶክተር እጅግ እናመሰግናለን ኑሪልን 🙏😍🙏

  • @eyosafethebrom4517
    @eyosafethebrom4517 8 หลายเดือนก่อน +4

    እናመሰግናለን ዶ/ር መስኪ! እግዚአብሔር ከክፉ ይጠብቅሽ!❤❤❤

  • @melakuargaw5128
    @melakuargaw5128 8 หลายเดือนก่อน +4

    ዶክተር እንኳን በሰላም መጣሽልን እጅግ በጉጉት ስጠብቅሽ ነበረ።

  • @betynegouse1189
    @betynegouse1189 8 หลายเดือนก่อน +3

    እንኳን በደህና መጣሽ መስኪ በሰላም ጠፋሽ

  • @tsegayetaye3042
    @tsegayetaye3042 8 หลายเดือนก่อน +4

    በጣም ጠፍተሽ ነበር ዶር፡ እንኳን ተከሰትሽ

  • @user-cr8ex9co7g
    @user-cr8ex9co7g 8 หลายเดือนก่อน +3

    እህቶቻችን እንኳን በደህና መጣሽ እንወድሻለን በርችልን

  • @Maria_Henock
    @Maria_Henock 8 หลายเดือนก่อน +3

    ዶክተር መስከረም እንኳን ደህና መጣሽ። በጣም ነበር የናፈቅሽኝ። ስለትምህርቱ እናመሰግናለን።

  • @Embete-
    @Embete- 8 หลายเดือนก่อน +4

    ስላየሁሽ ደስ ብሎኛል ዶክተር 🙇

  • @rahelassefa1766
    @rahelassefa1766 8 หลายเดือนก่อน +2

    እናመሰግናለን

  • @berhanujazz5944
    @berhanujazz5944 8 หลายเดือนก่อน +2

    እንኳን በሰላም ተመለሽ ።

  • @sewentmeazameaza3076
    @sewentmeazameaza3076 8 หลายเดือนก่อน +2

    እንኳን ደህና መጣሽ

  • @eyerustiki2995
    @eyerustiki2995 8 หลายเดือนก่อน +3

    እኔ ደሞ የት ጠፋሽ ብዬ ጨንቆኝ ነበር መስኪዬ አንኳን መጣሽልን ሁሉም መርሀ ግብሮች ብርሀን ገላጭ ናቸው እናመሰግናለን❤ በጣም ነው ምወድሽ❤

  • @bluelife6722
    @bluelife6722 8 หลายเดือนก่อน +3

    በጣም ጥሩ አቀራረብ

  • @meazaayele4491
    @meazaayele4491 8 หลายเดือนก่อน +3

    እንኳን ደህና መጣሽ ዶ/ር። እግዚአብሔር ይስጥልን።

  • @seifealigaz4897
    @seifealigaz4897 8 หลายเดือนก่อน +3

    እግዚአብሔር ይጠብቅሽ ዶክተር 🙏

  • @fasikawsnbet2766
    @fasikawsnbet2766 8 หลายเดือนก่อน +8

    ቃለህይወት ያሰማልን ❤❤❤❤

  • @ghaliabafita
    @ghaliabafita 8 หลายเดือนก่อน

    በጣም አመሠግናለሁ ቁርጠኛ ነሽ፣ ዶ/ር መስከረም ለቺሣ

  • @mikaelsiyum4030
    @mikaelsiyum4030 8 หลายเดือนก่อน +4

    ጆሮ ያለው ይስማ!!! እውነቱ ይህ ነው። ልዑል እግዚአብሄር ጤና ከእድሜ ጋር ያድልልን። ወድ እህታችን ያገልግሎት ጊዜሽን አምላክ ይባርክልሽ። ያንቺን ጊዜ ማግኘት እጅግ ይናፍቃል።

  • @mekushanigus
    @mekushanigus 8 หลายเดือนก่อน

    ዶ/ር እግዚአብሔር ይስጥልን ። የተደበቀን እውነት ጥልቅ የሆነ ምርምርና ጥናት እያደረግሽ የምትሰጭው ገለፃ ትንታኔ የሚያስገርም ነው።

  • @clight214
    @clight214 8 หลายเดือนก่อน +2

    እንኳን በሰላም መጣሽ።

  • @TesfaMico
    @TesfaMico 8 หลายเดือนก่อน +2

    Welcome our beloved sister❤

  • @addiszemariam7240
    @addiszemariam7240 8 หลายเดือนก่อน +1

    ዶክተር እግዚአብሔር ያክብርልን በእድሜ በጤና ይጠብቅልን ድንቅ ትምህርት

  • @Haregi849
    @Haregi849 8 หลายเดือนก่อน +6

    ሰው ከዘርኝነት ወጥቶ እንደዚህ የሀገሩን ታሪክ ቢያጠና ኢትዮጵያ የት በደረሰች እናመሰግናለን መስኪ❤

  • @user-uc4le5fd1q
    @user-uc4le5fd1q 8 หลายเดือนก่อน +2

    welcome back Misky

  • @konjitbuta9661
    @konjitbuta9661 8 หลายเดือนก่อน +6

    Egezabehere yemesgen ehetaleme 🙏
    Enkune Demo metashelen ❤

  • @babyayalew8059
    @babyayalew8059 8 หลายเดือนก่อน +7

    እንኳን በሰላም ተመለሽ መምህር🙏

  • @dawitgezahegne9343
    @dawitgezahegne9343 7 หลายเดือนก่อน

    በጣም ጥሩ ድንቅ የሆነ ታሪክን ነው በሚገባን መልኩ አያቀረብሽልን ያለው ። ሠላምና ጤናሽን ያብዛልን።

  • @abisiniaethiopia7673
    @abisiniaethiopia7673 8 หลายเดือนก่อน

    ዶ/ር መስከረም ጥቃሚ ትምህርት ነው እናመሰግናለን

  • @biniammathewos390
    @biniammathewos390 8 หลายเดือนก่อน +14

    Wow it is very educational and eye opener. I can’t wait the part 2 of these video

  • @wogayhutesfaye3223
    @wogayhutesfaye3223 8 หลายเดือนก่อน

    እግዚያብሔር ፀጋውን ያብዛልሽ

  • @tesfayegizwe3141
    @tesfayegizwe3141 8 หลายเดือนก่อน +3

    አንኳን በደህና መጠሸ ዶክተሩ

  • @user-yz5zm6mm4k
    @user-yz5zm6mm4k 8 หลายเดือนก่อน +1

    ምስጋናና መልካም ምኞት!
    እንኳን ደህና መጣሽ ብርቅየዋ ዶ.ር መስከረም
    እየጠበቅኩሽ ነበር :: ሱቅሽንም ጎብቸ ያሉትን
    መፃህፍት ወስጃለሁ::
    ኑሪልን! እድሜ : ጤና: ፀጋ እና በረከት : ያብዛልሽ::
    ቤተሰብሽም: ይባረክ !
    የአገልግሎት ዘመንሽን ይባርክል:: የ" ደቂቀ እስቲፋኖስን " መጽሐፍ እየጠበቅኩ ነው:: ቢያንስ ለአራት ወራት እዚሁ አድስ አበባ ስለምቆይ ይዠው እንደምሄድ ተስፋ አለኘ::
    ወስብሐት ለእግ/ር!

  • @ashufirmino596
    @ashufirmino596 8 หลายเดือนก่อน +1

    ኢትዮጵያ በዘር ተበጫጭቃ ሳትጠቀምባቸው ከቀሩ ጥቂት ምሁራን መካከል እንደነ ዶ/ር ሮዳስ አንቺን ጨምሮ በምጡቅ አዕምሮዋችሁ ሁሌም ነው እምደነቅባችሁ እምቆጭባችሁም ምክንያቱም ኢትዮጵያ አንቺና አንቺን በመሰሉ ምሁራን መጠቀም የሚገባትን ያህል ሳትጠቀም በመቅረቷ! ብቻ ተስፋ የምናደርገው እግዚአብሔርር አምላክ ይህን የዘር ኮተት አሽቀንጥሮ ጥሎ ውዲቷ ኢትዮጵያ ሐገራችን የቀድሞ ሠላሟ ተመልሶ ዶ/ር እንዳንቺ ባሉ ምሁራን ወደ ከፍታ ማማዋ ጉብ የምትልበት ጊዜ በቅርቡ እንዲሆን ምኞቴ ነው 🙏 በርችልን ዶ/ር መስከረም ❤

  • @soltray8427
    @soltray8427 8 หลายเดือนก่อน +1

    እንኳን: ደህና: መጣሽ❤

  • @alemzewdtaye6830
    @alemzewdtaye6830 8 หลายเดือนก่อน +3

    እንዃንደህናመጣሽ ዶክተር

  • @deguassefa1254
    @deguassefa1254 3 หลายเดือนก่อน

    እናመሠግናለን እህታችን

  • @hannawondimu5702
    @hannawondimu5702 8 หลายเดือนก่อน +1

    እግዚአብሔር ይስጥልን እድሜ ክጸጋጋር ያድልልን

  • @selmonmulugeta4659
    @selmonmulugeta4659 8 หลายเดือนก่อน +3

    Thank you 😮

  • @tefaraabayu9421
    @tefaraabayu9421 8 หลายเดือนก่อน

    ብዙ ቁምነገር አካፈልሽኝ።
    ተባረኪ።

  • @sahleshibru4759
    @sahleshibru4759 8 หลายเดือนก่อน

    DR.MESK, THINKS FOR YOUR THOUGHTFUL

  • @dawitetsegaye1472
    @dawitetsegaye1472 8 หลายเดือนก่อน +2

    እንደው ግርም ይለኛል የፈጣሬ ስራው::
    እስኪ ይሁን የአባቶቻችን አምላክ የአንችን አንደበት ተጠቅሞ እንዲህ ሲናገር ስሰማው ልቤ ይሞላል አንድም ልቤ ያለቅሳል::
    እረጅም እድሜ ከጤና ጋር ይስጥልን ዶክተር::
    በስጋ ያፈራሻቸውን ልጆችሽን የቅዱሳን አምላክ ይባርክልሽ::
    ወስብሓት ለእግዚአብሔር::

  • @habtamumulu7178
    @habtamumulu7178 8 หลายเดือนก่อน +3

    welcome back

  • @user-bg3dl4ko5l
    @user-bg3dl4ko5l 8 หลายเดือนก่อน +1

    በጣም እናመሰግናለን ጥሩ ነዉ የገለጥሽዉ ጎበዝ በርች♥♥♥

  • @samuelshiferaw4077
    @samuelshiferaw4077 8 หลายเดือนก่อน +1

    Good to hear from you again

  • @sophiasadick1320
    @sophiasadick1320 8 หลายเดือนก่อน +4

    Selam selam, Doctor.
    Welcome back 🙏🏽🙏🏽🙏🏽

  • @fireayalew9663
    @fireayalew9663 8 หลายเดือนก่อน

    እንኳን ደህና መጣሽ ዶ/ር

  • @gudayetessema5939
    @gudayetessema5939 8 หลายเดือนก่อน +1

    Dr.meskerem!edmesh yir,em zerish yilemlim Girum timihirt new amesegnalehu Tebarekee!

  • @muluneshalemayehu5775
    @muluneshalemayehu5775 8 หลายเดือนก่อน +1

    በርች የኔ ጎበዝ❤❤❤

  • @rasbahiru5303
    @rasbahiru5303 8 หลายเดือนก่อน +1

    ዶክተር ሰላም ለአንቺ ይሁን ሁለቱ መፃፎችሽን አግኝቻለሁ ።
    መፅሐፈ ደቂቀ እስጢፋኖስን በጉጉት እጠብቃለሁ ።

  • @woldegeor
    @woldegeor 8 หลายเดือนก่อน

    ድንቅ መምህርት ነሽ::

  • @adonayemesekelu1739
    @adonayemesekelu1739 8 หลายเดือนก่อน

    መስኪ ውድ በጣም እናመሰግናለን 🥰

  • @AshenafiAmbelu-pj4jd
    @AshenafiAmbelu-pj4jd 8 หลายเดือนก่อน +3

    Girum nwu memeherachin, ehetachen bertulen endenante yalu memheran ayasatan MEDEHANIALEM! Elalehu.

  • @challewgebrhiwot7364
    @challewgebrhiwot7364 8 หลายเดือนก่อน +1

    Well come back

  • @aberesendek9037
    @aberesendek9037 7 หลายเดือนก่อน

    እንወድሻለን መረጃን መሰረት አድርገሽ ለምትሰጭን ትምህርታዊ እዉነት:!!

  • @zenebechdemessia7852
    @zenebechdemessia7852 8 หลายเดือนก่อน +2

    Enkwan Dena mtashe d,r,

  • @deressadinka7063
    @deressadinka7063 7 หลายเดือนก่อน

    We are really grateful, thankyou.

  • @saregebre3906
    @saregebre3906 8 หลายเดือนก่อน +1

    Thank you 🙏 and welcome back.

  • @thefreedomchannel4548
    @thefreedomchannel4548 8 หลายเดือนก่อน +3

    I am so happy to hear from you , thank to God 🙏🏽🙏🏽🙏🏽🙏🏽

  • @user-qt3fm2co6m
    @user-qt3fm2co6m 8 หลายเดือนก่อน

    ዶክተር እናመሰግናለን

  • @biniyamkindie
    @biniyamkindie 7 หลายเดือนก่อน

    ዋውውውውው ዶክተር እናመሰግናለን።

  • @kassa4882
    @kassa4882 6 หลายเดือนก่อน

    ❤️❤️❤️❤️🙏🙏🙏 long life for you.

  • @sileshegirma2909
    @sileshegirma2909 8 หลายเดือนก่อน

    እንኳን ደህና ተመለሽ🎉

  • @marmaria787
    @marmaria787 6 หลายเดือนก่อน

    God Bless you More!

  • @kekunhasen2717
    @kekunhasen2717 หลายเดือนก่อน

    thanks for explaination

  • @MintesnotMinte-le3qi
    @MintesnotMinte-le3qi 7 หลายเดือนก่อน

    የሚገርም ነው በዚህ ደረጃ አይናችን ስር የሚሰራውን ስራ አለማወቃችን ይገረማል የመሪእራስ በአማንን መፅሀፈ ክቡር 8 ክፍል እያለው አንብቤው ለሰዎች ስናገር በጣም የሚያሳዝን ሁኔታ በጣም ብዙ ሰው አልተቀበለኝም እንደውም ትንሽ እውቀት ያለው ሰው ሰለ ኢትዮጵያ ያለው አመለካከት በጣም የወረደ ነው ያሳዝናል በዚህ ልክ እራሳችን እንኳን ሰለ እራሳችን አናቅም ዶክተር ስለ ሰጠሽን እውቀት እግዚአብሔር ይስጥልን ቃለህይወት ያሰማለን 🙏🙏