ዮሐንስ ወንጌል 5፥30 || ኢየሱስ ከራሱ አንዳች ሊያደርግ አይቻለውም? David Wood Amharic

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 21 ส.ค. 2024
  • I found this video useful, so I translated it to the best of my ability. Use this link to find the first video I translated. I apologize for the minor mistakes I make.‌‌
    • Dr. David Wood vs Dr. ...
    What the Quran REALLY Says about the Gospel • ቁርአን ስለ ወንጌል ምን ይላል? ከ...
    መልካም ዜና
    የምስራች፣ የምስራች፣ የምስራች! የምስራች ማለት መልካም ዜና ማለት ነው። የእግዚአብሔር ቃል ደጋግሞ የሚነግረን ይሄ መልካም ዜና ምንድነው? ዛሬ፣ በእግዚአብሔር ረዳትነት፣ በእግዚአብሔር ቃል ላይ ስለተጠቀሰው ስለዚህ መልካም ዜና እንነጋገራለን። ነገር ግን ስለ መልካሙ ዜና ከመነጋገራች በፊት ስለ መጥፎው ዜና ማስታወስ አለብን።
    ምንድነው መጥፎው ዜና? በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ከፈጠረ በኋላ አዳምንና ሔዋንን በምድራዊዋ ገነት ውስጥ እንዳስቀመጣቸው ታስታውሳላችሁ። እግዚአብሄር እንዲያውቁት፣ እንዲወዱት፣ እንዲታዘዙት እና ለዘላለም እንዲያከብሩት ፈጥሯቸዋል። ይሁን እንጂ እግዚአብሔር እነሱን ለመፈተን አዳምን እንዲህ አለው፡-
    “በገነት ካለው ከዛፉ ፍሬ ብሉ፥ ነገር ግን እንዳትሞቱ በገነት መካከል ካለው ከዛፉ ፍሬ አትብሉ አትንኩትም።”
    መጥፎው ዜና አዳምና ሔዋን እባቡን ማለትም ከተከለከለው ዛፍ ፍሬ እንዲበሉ የፈተናቸውን ዲያብሎስን ማዳመጣቸው ነው። የአዳምና የሔዋን ኃጢአት እነርሱንና ዘሮቻቸውን ሁሉ በመበከል በዓለም ላይ ችግርንና ሞትን አመጣ። ብዙ ጊዜ እንደምንሰማው፡ "ወረርሽኝ መነሻው ላይ ብቻ አይወሰንም!" የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል መጥፎ ዜና ይነግረናል፡-
    “ለሰዎችም አንድ ጊዜ መሞት ከእርሱ በኋላም ፍርድ እንደ ተመደበባቸው፥...
    እነሆ፥ ጌታ በሁሉ ላይ እንዲፈርድ፥ በኃጢአተኝነትም ስላደረጉት ስለ ኃጢአተኛ ሥራቸው ሁሉ ዓመፀኞችም ኃጢአተኞች በእርሱ ላይ ስለ ተናገሩ ስለ ጭከና ነገር ሁሉ ኃጢአተኞችን ሁሉ እንዲወቅስ ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋር መጥቶአል ብሎ ለእነዚህ ደግሞ ትንቢት ተናገረ።” (ዕብራውያን 9፥27 ይሁዳ 1፥15)
    ስለዚህ፣ መጥፎው ዜና ሁላችንም ኃጢአተኞች ነን እናም የእግዚአብሔርን የጽድቅ ፍርድ መጋፈጥ አለብን! ይሁን እንጂ፣ መልካሙ ዜና (የምስራቹ) በዚያው በገነት ውስጥ፣ በምረቱ ባለጠጋ የሆነው እግዚአብሔር፣ አንድ ቀን ከድንግል የሚወለድን ኃጢአት የሌለበትን ሰው ወደ አለም እንደሚልክ ማስታወቁ ነው። ይህ ቅዱስ ሰው፣ ይህ ጻድቅ አዳኝ፣ ለአዳምና ለዘሮቹ ሁሉ ኃጢአት ለመክፈል ራሱን መስዋእት አድርጎ ይሞት ነበር። ለኛ የሚገባን የኃጢአት ቅጣት በዚህ ኃጢአት በሌለበት አዳኝ ላይ ይወድቃል። አዳምና ሔዋን ኃጢአት በሠሩበት ቀን እግዚአብሔር የሰበከው ወንጌል (የምስራች) ይህ ነው። እግዚአብሔር የዚህን አዳኝ መምጣት ለማወጅ ብዙ ሰዎችን ተጠቅሟል፣ እንዲሁም መሲህ ይባላል። እያንዳንዱ የእግዚአብሔር ነቢያት ስለ መሲሑ አንድ ነገር አውጀዋል፣ ስለዚህም እርሱ ሲመጣ እግዚአብሔር የሾመው እርሱ መሆኑን ሁሉም ይገነዘባል። ለምሳሌ ያህል፣ ከመሲሑ መምጣት ሰባት መቶ ዓመታት ቀደም ብሎ የነበረው ነቢዩ ኢሳይያስ፣ መሲሑ እንዴት እንደሚወለድ ተንብዮአል። "ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው።"( ማቴ. 1:23፤ ኢሳ. 7:14 ) ሚክያስ የተባለ ነቢይ ደግሞ መሲሁ ከሰማይ መጥቶ በቤተልሄም መንደር በምድር ላይ እንደሚወለድ ትንቢት ተናግሯል። በትክክል መሲሑ የተወለደበት ቦታ ይህ ነበር። ሆኖም ሚክያስ ይህን ትንቢት የተናገረው መሲሑ ከመወለዱ ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት ነው። ነገር ግን ነቢያት የመሲሑን መወለድ ብቻ አላወጁም። በተጨማሪም መሲሁ በኃጢአተኞች ምትክ መከራ እንደሚደርስበትና እንደሚምት ትንቢት ተናግረዋል። ለምሳሌ ነቢዩ ዳዊት ሰዎች መሲሑን እንደሚንቁት፣ እንደሚያሰቃዩት፣ እጁንና እግሩን እንደሚወጉ እና እንደሚገድሉት ጽፏል። ዳዊት የመሲሑን ሞት ማወጅ ብቻ ሳይሆን፣ እግዚአብሔር መሲሁን ከሞት እንደሚያስነሳውም ተንብዮአል፤ ይህም እግዚአብሔር የአዳምን ልጆች ከኃጢአት ቅጣት ለማዳን የላከው አንድና ብቸኛ አዳኝ መሆኑን አረጋግጣል።
    ስለ መሲሁ መወለድ ብዙም ክርክር የለም፣ ነገር ግን ብዙዎች በሞቱና በትንሳኤው ይሰናከላሉ። ሰዎች የላከውን መሲህ ሲያዋርዱት እግዚአብሔር እንዴት ሊቆም እና ሊመለከት እንደሚችል አይገባቸውም። ብዙ ሰዎች ሊረዱት ያልቻሉት ነገር መሲሑ ለኃጢአታችን እንዲህ አይነት መከራ እንዲደርስበት ያቀደው እኛን የሚወደን አምላክ መሆኑን ነው። ነገር ግን ነቢያቱ እንዲህ ሲሉ አውጀዋል፡- “እግዚአብሔርም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈቀደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።”
    - (ኢሳይያስ 53፥10)
    ነቢያትን እናምናለን? አዎ እናምናቸዋለን እንላለን። ነቢያትን በእርግጥ የምናምን ከሆነ የጻፉትንም ማመን አለብን። ነብያት የራሳቸውን ሃሳብ እንዳልተናገሩ ማስታወስ አለብን። እግዚአብሔር የሚናገሩትን በመንፈሳቸው ውስጥ አኖረ። እንግዲያውስ እነዚያን ነቢያት ለማመን ብንቃወም፣ ማንን ነው ምንቃወመው? የምንቃወመው እግዚአብሔርን ነው። ምክንያቱም ነቢያት መሲሁ ኃጢአትን ለማስወገድ መስዋዕት ሆኖ እንደሚሞት ትንቢት እንዲተነብዩ ያነሳሳው እርሱ ነውና።
    {የሚቀጥለው ማሊክ የሚባል ሰው የግል ምስክርነት ነው።} እዚህ ጋር ቆም ላድርገውና እንዴት በኢየሱስ ክርስቶስ አማኝ እንደሆንኩ ልንገራችሁ። በወጣትነቴ በቀን አምስት ጊዜ ለመጸለይ እና አመታዊ ጾምን ለመጾም ታማኝ ነበርኩ፣ ነገር ግን ከሞትኩ በኋላ ወዴት እንደምሄድ አላውቅም ነበር። ዙሪያዬ ያሉትን ሁሉ ጠየኩ፣ ሆኖም ግልጽ የሆነ መልስ አላገኘሁም። ወንጌልን (ኢንጂልን) ሳጠና ግን፣ ከሞቴ በኋላ ወዴት እንደምሄድ ማወቅ እንደምችል አወቅሁ፤ ምክንያቱም መሲሁ ኢየሱስ ራሱ በወንጌል እንዲህ ይላል፦ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም።” (ዮሐንስ 5፥24) እንዲሁም እንዲህ ብሏል፦ “ኢየሱስም፦ ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤” (ዮሐንስ 11፥25) ስለዚ፣ ራሴን ለማዳን ከራሴ ጥረት ንስሃ ገብቼ ነቢያት ሁሉ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ በስሙ የኃጢአቱን ስርየት ይቀበላል" ብለው ትንቢት በተናገሩለት መሲህ አመንኩኝ (ሐዋርያት 10፥43)። ተስፋዬን ሁሉ ወስጄ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ አስቀመጥኩት። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔር ለመንፈሴ ሰላም አምጥቶላታል። አሁን ህሊናዬ አይረበሽም። ኢየሱስ በመስቀል ላይ ከሰራው ሥራ የተነሳ የወደፊት እጣዬ በሚያስደንቅ ሁኔታ ብሩህ ነው። በሕይወቴ እንደ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር፣ አንዳንድ ጊዜ ችግር እና መከራ ያጋጥመኛል ምክንያቱም እምነቴ ከዘመዶቼ እና ከጓደኞቼ አስተያየት ስለሚለያይ፤ ግን ሰላም አለኝ። የእግዚአብሔር ሰላም ልቤንና አእምሮዬን ሞልቶታል። ይህን የሰጠኝ ኢየሱስም እንዲህ ይላል፦ “ዓለም ቢጠላችሁ ከእናንተ በፊት እኔን እንደ ጠላኝ እወቁ።” (ዮሐንስ 15፥18) “ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም።” (ዮሐንስ 14፥27) እና ወዳጆች ሆይ፣ ጌታ ለእኔ እና በእኔ ያደረገውን ለእያንዳንዳችሁ ሊያደርግ ይችላል። ካንተ ወይም ካንቺ አንድ ነገር ይጠይቃል፡-ሙሉ ልብህን እንድትሰጠው። ሙሉ ልብሽን እንድትሰጪው። የቀረውን እሱ ያደርገዋል። ጌታ ኢየሱስ ራሱ እንዲህ ብሏልና። "እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤" (ማቴ. 11:28-29)
    እግዚአብሔር ታላቁን ማዳኑን መቼም ቢሆን አይሸጥልህም ወይም አይሸጥልሽም። እንዲሁ ያለ ምንም ዋጋ (ከእናንተ ባልሆነ ዋጋ) በነጻ ሊሰጣችሁ ነው ሚፈልገው። መልካም ስራ፣ ፀሎት (ሶላት) እና ፆም በውስጣችሁ ጥሩ ስሜት ይሰጡ ይሆናል፣ ነገር ግን የእግዚአብሔርን ፅድቅ አያረኩም! ወደ እግዚአብሔር ገነት የምትገባበት/የምትገቢበት መንገድ አንድ ብቻ ነው።
    1.) በመጀመሪያ ኃጢአተኛ እንደሆንክና አምላክን ለማስደሰት የሚያስችል ኃይል እንደሌለህ መገንዘብ ይኖርብሃል።
    2.) ከዚያም ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝ እንደሆነ፣ ኃጢአትህን ለማስወገድ እግዚአብሔር በመስቀል ላይ እንዲሞት እንደ ላከውና እግዚአብሔር የዘለአለም ሕይወትን ይሰጥህ ዘንድ እንዳስነሳው ማመን አለብህ።
    የኦሮምኛውን ቻናሌን ለማግኘት ይህንን ተጫኑ👇
    / @dhugaanniboqachiisa
    አስተያየታችሁን በውስጥ ማድረስ የምትፈልጉ ይህንን የቴሌግራም ሊንክ ተጠቀሙ👇
    t.me/BibleAndMe

ความคิดเห็น • 89

  • @ewnetyasarfal
    @ewnetyasarfal  8 หลายเดือนก่อน +14

    ጨርሳችሁ ማየታችሁና like ማድረጋችሁ እንዲሁም Comment መጻፋችሁ ዋጋ ስላለው እንዳትረሱት🥰🥰🥰

    • @wendimuwedajo7917
      @wendimuwedajo7917 8 หลายเดือนก่อน +1

      ተባረክ ብራ

    • @bettybreaep
      @bettybreaep 3 หลายเดือนก่อน +2

      Enwedhalennn❤❤❤❤

    • @BeBeMa489
      @BeBeMa489 3 หลายเดือนก่อน

      ጌታ ማስተዋሉን ያብዛልህ ❤

    • @PetrosGetachew-rw7pf
      @PetrosGetachew-rw7pf หลายเดือนก่อน

      አስኪ ያንተን logic ተናገር።እሱ የናንተን ኩርዐን አና ተርጓሚ መፅሐፍት ተተቅሞ አቀረበ አንተ ደግሞ በግድ ተቀበል እንዳለህ ተሰማህ። ለነገሩኮ እሱ እንደነገረህ ከሆነ እንደ ሙስሊም ከራሱ እምነት ጋር እየተጋጨ የሚኖር እምነት በአለም የለም።

  • @khankpk8346
    @khankpk8346 9 หลายเดือนก่อน +10

    ቃለ ህይወት ያሰማልን ወንጌላችን የተከደነ ቢሆንም የተከደነባቸው ለሚጠፉት ነው❤

  • @user-uh2iz3cf8v
    @user-uh2iz3cf8v 7 หลายเดือนก่อน +5

    ተባረክ

  • @amanahmed8838
    @amanahmed8838 4 หลายเดือนก่อน +8

    ወንድሜ እውነታውን እንዲ እየተረጎምክ ማቅረብህ በጣም ጥሩ ነው ቀጥልበት ብዙዋች ይማሩበታል።

  • @Motivation-9-M9
    @Motivation-9-M9 5 หลายเดือนก่อน +5

    ኦ ጌታ ኢየሱስ አብዝቶ ይባርክህ ወንድሜ

  • @user-sw4yf5qt3w
    @user-sw4yf5qt3w 6 หลายเดือนก่อน +7

    የምር ላተ ቃላት ያጥረኛል ማርያምን ጥያቄ የፈጠረብኝን ጥቅስ መልስ አገኘሁ😢 ተባረክ አቦ ቀጥልበት

    • @ewnetyasarfal
      @ewnetyasarfal  6 หลายเดือนก่อน +1

      አመሰግናለው!!🥰

  • @Fikadu-sr7bq
    @Fikadu-sr7bq หลายเดือนก่อน

    እግዚአብሔር ይባረክ 🙏

  • @berryberry2124
    @berryberry2124 3 หลายเดือนก่อน +2

    ፈጣሪ ይባርክህ ወንድሜ ጤናና እድሜውን ይስጥህ🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

  • @mintesnot6857
    @mintesnot6857 7 หลายเดือนก่อน +3

    ተባረክ🥰🥰🥰

  • @fevenfevi4100
    @fevenfevi4100 4 หลายเดือนก่อน +2

    ተባረኩ ወንጌል ለ ዓለም

  • @user-cr5dv4vz3t
    @user-cr5dv4vz3t 8 หลายเดือนก่อน +2

    ክብር ለእ/ር ይሁን❤❤❤❤

  • @user-is5np9bi7h
    @user-is5np9bi7h 3 หลายเดือนก่อน +2

    የጌታ ፀጋ ይብዛልህ

  • @user-eg7uc1hc9u
    @user-eg7uc1hc9u 9 หลายเดือนก่อน +2

    ጥሩ ትንታኔ ነውጌታ ይባርክህ ❤❤

  • @AbinetDaniel-gh6mf
    @AbinetDaniel-gh6mf 5 หลายเดือนก่อน +2

    Thank you God bless you

  • @YosephWoldetsadik
    @YosephWoldetsadik 17 วันที่ผ่านมา

    ጌታ አብዝቶ ይባርክህ ቀጥልባት

  • @mengistuabebe6603
    @mengistuabebe6603 3 หลายเดือนก่อน +2

    ኢየሱስ የሞተው መነሣት ስለሚችል ነው

    • @user-pg4pv4ov4q
      @user-pg4pv4ov4q 3 หลายเดือนก่อน

      ብራ ከራሱ አንዳልሆነ አታውቅም እንዴ እሱ ሚሰራውን ስራ ሁሉ በእግዚአብሔር ፈቅድ በሎ አንደሰራ አታውቅም ? ዮሐንስ 5፦30 ማቲዮስ 16፦21

  • @AbinetDaniel-gh6mf
    @AbinetDaniel-gh6mf 5 หลายเดือนก่อน +3

    በጣም በትኩረት የማደምጣው channel nw❤

  • @TizitaBelachew-ze9zg
    @TizitaBelachew-ze9zg 7 หลายเดือนก่อน +2

    ተባረክ❤

  • @user-my7gc6fw6z
    @user-my7gc6fw6z 9 หลายเดือนก่อน +2

    ይብዛልህ ወንድሜ

  • @meseretbekele9832
    @meseretbekele9832 8 หลายเดือนก่อน +2

    እግዚአብሔር ይባርክ ወንድማችን በርታ

  • @user-xs8vl3hf6s
    @user-xs8vl3hf6s 3 หลายเดือนก่อน

    አላህ በራሱ አምላክ መሆኑን መኖሩ የተገለጠበት ቦታ አንድ እንኮን የለም ካለ ቢነግሩን ከመሐመድ ውጪ የተገለጠት ክርሰቶሰ ተገልጦ ሰለኛ አጢያት ደሙን አፍሶ ሞቶ ተቀብሮ በራሱ ስልጣን በሶስተኛው ቀን አምላካዊ ሰልጣኑን ተጠቅሞ ድንጋዩን ፈቅሎ ተነሰቶአል ክብር ለሰሙ ለመፍረድም ይመጣል ያለሱ መዳን የለም መፃፍአቹን መርምሩ

  • @Meron-li2mv
    @Meron-li2mv 3 หลายเดือนก่อน +1

    ቃለ ህይወት ያሰማልን

  • @user-tc2bm7ph7x
    @user-tc2bm7ph7x หลายเดือนก่อน

    ፀጋይብዛልህ

  • @user-np9kp3kt2u
    @user-np9kp3kt2u 6 หลายเดือนก่อน +2

    ❤❤❤❤❤❤

  • @tjcccbdg8082
    @tjcccbdg8082 3 หลายเดือนก่อน +1

    እግዚአብሔር ይባርክሕ

  • @user-ij2sd3sg9x
    @user-ij2sd3sg9x 2 หลายเดือนก่อน

    Thank you❤

  • @Jesus_is_Lord_stn25
    @Jesus_is_Lord_stn25 3 หลายเดือนก่อน +1

    ኢየሱስ ያድናል።

  • @amanuelhalake3855
    @amanuelhalake3855 22 วันที่ผ่านมา

    Blessed 🎉🎉🎉

  • @mahinisu7434
    @mahinisu7434 9 หลายเดือนก่อน +1

    ተባረክ ወንድሜ

  • @MilkiDesta
    @MilkiDesta 4 หลายเดือนก่อน +2

    God bless you !!

  • @Alemtsehay777
    @Alemtsehay777 3 หลายเดือนก่อน +1

    ፀጋዉ ይብዛልህ።

  • @tjcccbdg8082
    @tjcccbdg8082 3 หลายเดือนก่อน +1

    እግዚአብሔር ይባርክሕ ወንድማችን ❤❤❤

  • @tjcccbdg8082
    @tjcccbdg8082 3 หลายเดือนก่อน +1

    ተባረክ ወንድሜ ❤❤❤❤

  • @MessiKali
    @MessiKali 8 หลายเดือนก่อน +1

    ❤❤❤❤❤bertalin

  • @MarkosMenedo-cl6ki
    @MarkosMenedo-cl6ki 3 หลายเดือนก่อน +1

    እየሱስ ጌታ ነው !

  • @ruhamafati4217
    @ruhamafati4217 4 หลายเดือนก่อน +1

    ተባረኩ😊

  • @DessieWorku-gg2pd
    @DessieWorku-gg2pd 2 หลายเดือนก่อน

    ቀጥልበት ወንድሜ

  • @anayil3898
    @anayil3898 9 หลายเดือนก่อน +1

    ❤❤❤❤ work hard you are good you wil learn our

  • @melkamusonko
    @melkamusonko 8 หลายเดือนก่อน +5

    እባክህ ሁለ እንድህ አቅርብ ምክንያቱም
    ሙስሊሞች የዛክሪን ስብከት በመስማት ታውሩዋል እንደ ቅጠል ለምረግፍ ህዝብ መድረስ ግድ ይለናል
    የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የመጨረሻው ትዕዛዝ =ወደ አለም ሀሉ ህዱ ወንጌልን ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ
    ያመኔ የተጠመቀ ይድናል ያለመኔ ይፈረድበታል ❤❤

    • @ewnetyasarfal
      @ewnetyasarfal  8 หลายเดือนก่อน +3

      አሺ አላቆምም ገና ብዙ እሰራለው። ተባረክ!!🥰

    • @user-pg4pv4ov4q
      @user-pg4pv4ov4q 3 หลายเดือนก่อน

      የዶክተር ዛኪር ናይክ ያህል ትንሽ 🤏 እውቀት ቢናርህ አንተ ከኔ ውጭ ማንም የለም እኔን ብቻ ተከተሉኝ ትል ነበር አየህ አላህ ለሚሻው ሰው ነው እውቀት የሚሰጠው ቀድመህ ሰለሱ ከመናገርህ በፍት እያንዳንዱን የሀይማኖት መጻሕፍትን በ አይምሮህ ሴፍ አድርግ እወቅ እነ ዶክቶር አቡሀይደር አህድ ዲዳት ሁሉም ካንተ መጻሕፍ ነው አያወጡ አየተነተኑ ሚሰሩት

    • @TsionDawit-ty5rt
      @TsionDawit-ty5rt 3 หลายเดือนก่อน +1

      ​@@user-pg4pv4ov4qአይደል የናንተን ቁራን አየነው እኮ እኔ ሚገርመኝ የአህመድ ዲዳት መጨረሻ ነው

    • @user-pg4pv4ov4q
      @user-pg4pv4ov4q 3 หลายเดือนก่อน

      @@TsionDawit-ty5rt እውነት ከሚናገር ሰው በላይ የሚጠላ የለም ።!!!

    • @amanuelabako3640
      @amanuelabako3640 หลายเดือนก่อน

      @@user-pg4pv4ov4q ምኑ ለይ እውነት??? ....ለማንኛውም መጸሐፍ ቅዱሱን እና የአንተን መጸሐፍ ማንጻጸር ፈጸሞ ስለማይችል እና የሁለት ዓለም መጸሐፍ ስለሆነ ነው።

  • @ramatekadire384
    @ramatekadire384 9 หลายเดือนก่อน +2

    ታባራክ ወንድም እንደዝ ነው ምንፈልጋው❤❤

  • @cocobwatola7107
    @cocobwatola7107 4 หลายเดือนก่อน +1

  • @peac93
    @peac93 3 หลายเดือนก่อน

    Metsehaf kidusm quran tesastowal yilal sewuyew!

  • @rohamaworld6764
    @rohamaworld6764 8 หลายเดือนก่อน

    bertaa yen wondim ene yefelkt new yeseraa

  • @user-fk3ud2gu3l
    @user-fk3ud2gu3l 3 หลายเดือนก่อน +1

    ልብ ካለው ለምን እንደ ሌሎቹ ቄስ አጠገቡ ሆኖ ከይከራከርም ወገኖቼ የዛኪርን ከDr. ካምቤል ጋር ያደረገውን ክርክር እዩ ት

  • @NasirHasan-qd7nf
    @NasirHasan-qd7nf 3 หลายเดือนก่อน

    Outside the Bible

  • @user-wd3ig3no4f
    @user-wd3ig3no4f 2 หลายเดือนก่อน

    አንድ ጥያቄ አለኝ እየሱሱ በፊት የነበር ስዎች ምየመለክት አምለክ መን ነበራ ።

  • @BurokAyalehu
    @BurokAyalehu 7 หลายเดือนก่อน

    ዴቪድ ዉድ ጥሩ ነዉ
    but Christian Prince is the best becouse he is from areb

    • @ewnetyasarfal
      @ewnetyasarfal  7 หลายเดือนก่อน

      ሁለቱም በየራሳቸው ጥሩ ነገር አላቸው አይወዳደሩም። ሁለቱም በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ሰራተኞች ናቸው። ስለዚ ማበላለጡ ይቅር።

  • @ZeynebAli-gb3rq
    @ZeynebAli-gb3rq 2 หลายเดือนก่อน

    እስቲ አንድሰው እግዛብሄር ለአዳም ከልጅልጅተወልጄ አድንሃለው ብሎ ቃል የገባለት ከመፅሀፍቅዱስ?

    • @ewnetyasarfal
      @ewnetyasarfal  2 หลายเดือนก่อน +1

      “በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥ አንተም ሰኰናውን ትቀጠቅጣለህ።”
      - ዘፍጥረት 3፥15
      እንኳን ይሄንን፣ ቀላሉንም ነገር መረዳት አልቻላችሁም። መረጃ ስላልክ እንጂ ይገባሃል ብዬ አይደለም።

  • @peac93
    @peac93 3 หลายเดือนก่อน

    1Nachew ab wald ! who sent him yilal ! yelakegnin yilal sewuyew irasu eko.meliktegna naw eyale naw.Please listen! Dr zakir batam tikikil naw semichewalew! meslam shinfet aydelam!

  • @fajrushamsuSerwanna
    @fajrushamsuSerwanna 3 หลายเดือนก่อน

    በየ-ቀኑ-እየሳላሙ-ስለሆና-ነዉ-እንደዚ-የተቀጠለቹት-ወዳደቹም-ጠላቹም-ከእስልምና-ዉጪ-እዉነተኛ-ሀይመኖት-ዬላም

    • @Bellazekichen
      @Bellazekichen 3 หลายเดือนก่อน +1

      እና ሰው ሁሉ ስለሰለም ከውሸት ጋር መቆም አለብህ 😂

  • @peac93
    @peac93 3 หลายเดือนก่อน

    Ye lakegnin fikad min malet naw?

  • @peac93
    @peac93 3 หลายเดือนก่อน

    logiku ayasaminim .father son ! bagid fatari enargew bagid! min malet naw wald ayferdim ab yiferdal.amlake amlake leman tewkegn yilal eyesus endet kediya fetari erdata yifaligal ende? naw fatari erdata miteyikew!.eyesus yitseliyal,yisegdal,yitsomal so fetari laman naw mitsomew mitseliyew,misegdew? shaytan eyesusin tefetatnotal endet naw fetarin mifetatenaw shaytan! ende dr zakir abrarulin.ayaskedim sewuyew milew.asredugn isti?

  • @peac93
    @peac93 3 หลายเดือนก่อน

    እኔ ኢሄ ነገር አይገባኝም አሳማኝ አይደለም!የዛኪር ናይክ አሳማኝ ነው ! ሌላ ለዛኪር ንግግር አሳማኝ ፈልግና አቅርብልን !

    • @selamusamuel7772
      @selamusamuel7772 หลายเดือนก่อน

      Libonan sikefitlhn newu gn andi tkis ene abi ale mehonen alemameni erasu behatiyat the yasigedilhal yohans wengel 8:23 and 8:24...

    • @selamusamuel7772
      @selamusamuel7772 หลายเดือนก่อน

      Ya maletu EYESUS ABI kehone ABI EYESUS NEWU MALETU NEWU ABI YEMIYADERIGEWUN EYESUSM YADERIGAL ZEDAGM 6:4 EFESON 4:4 YOUANNIS RAEY MULUNI AMIBIB

  • @NasirHasan-qd7nf
    @NasirHasan-qd7nf 3 หลายเดือนก่อน

    Contradiction...

  • @user-pg4pv4ov4q
    @user-pg4pv4ov4q 4 หลายเดือนก่อน

    ብቻ ይገርማል ሂዳያ ይሰጣቹ

    • @ewnetyasarfal
      @ewnetyasarfal  4 หลายเดือนก่อน +2

      ዋናው መገረምሽ ነው። አትጥፊ🥰

    • @misganabere6115
      @misganabere6115 3 หลายเดือนก่อน

      @@ewnetyasarfal tiyake mefterm kelal aydelem keep it up

  • @user-pg4pv4ov4q
    @user-pg4pv4ov4q 4 หลายเดือนก่อน

    ቆይ ቆራርጠህ በዛኪር ከምትሰራ ለምን ከራሱ አይሰራም ደሞ ሚያዎራው ሰለ ስንት ነገረ ነው ሚያዎራው ግን ምን አይነት ጭንቅላት ያልን ውስብስብ የሆነ ነገር

    • @ewnetyasarfal
      @ewnetyasarfal  4 หลายเดือนก่อน +2

      ቀስ ብለሽ ደጋግመሽ ስሚው ምንም የተወሳሰበ ነገር የለውም። መልስ እየሰጠ ነው።

  • @Uvbnn
    @Uvbnn 8 หลายเดือนก่อน

    😂😂ይሄ ላም የሆነ ሰውዬ አትስሙት ምንም ምያውቀው ታርክ የለም

    • @ewnetyasarfal
      @ewnetyasarfal  8 หลายเดือนก่อน +1

      ላምንማ የምትሰማው አንተ ነህ። አል በቀራን ከቁርአን ውስጥ ስወግደው። እሱን እየተከተልክ ነው ሰውን እንዲ ምታንጓጥጠው።

    • @Uvbnn
      @Uvbnn 8 หลายเดือนก่อน

      @@ewnetyasarfal አል ባቀራ ከቁርአን ለምን ነው ሚወደገደው? ስለ ማታውቂነው እንጂ

    • @Uvbnn
      @Uvbnn 8 หลายเดือนก่อน

      David wood ማለት ምንም ማያውቅ ሰው ነው ወደድሽም ጠላሽም

    • @ewnetyasarfal
      @ewnetyasarfal  8 หลายเดือนก่อน +1

      ጾታ እንኳን መለየት አትችልም። አሳዘንከኝ። መወገድ ያለበትማ የላም ምእራፍ ለላም እንጂ ለሰው ስማይጠቅም ነው።

    • @Uvbnn
      @Uvbnn 8 หลายเดือนก่อน

      @@ewnetyasarfal ዉይ ወንድ ነሽ እንዴ? 😄 አባቴ ቁርአን ላይ ምንም አይነት ስህተት አታገኝም ደሞ ቁርአን እንዴ bible biography አይደለም

  • @AhmedHamuda-ek7rp
    @AhmedHamuda-ek7rp 8 หลายเดือนก่อน

    online ግባ ቀጣፊ