34 - የግብፅ እና የኢትዮጵያ ታሪካዊ ግንኙነት፤ የተቀደሰ? ወይስ ያልተቀደሰ? (በዶ/ር መስከረም ለቺሣ)

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 5 ก.ค. 2024
  • የግብፅ እና የኢትዮጵያ ግንኙነት፡ እጅግ ጥንታዊ እና ውስብስብ ነው። በበጎ ጎኑ ስናየው፡ ግብፅ እና ኢትዮጵያ፡ በክርስትና እምነት በኩል፡ የቆየና የጠበቀ ግንኙነት አላቸው።ከዚያ በተቃራኒ ደግሞ፡ በዐባይ ወንዝ እና በሌሎች ፖለቲካዊ ምክንያቶች፡ ከጥንት ጀምሮ የቆየ ጠላትነትም በመካከላቸው አለ። ለመኾኑ፡ ይኽን ታሪካዊ ጠላትነት አልፈው፡ ኢትዮጵያውያን ነገሥታትና በጥቅሉ ሕዝበ ክርስቲያኑ፡ ከግብፅ ጳጳሳት በማስመጣት ጭምር፡ ግንኙነቱ እንዲቀጥል ይፈልጉ የነበረው፡ ለምን ይኾን?
    ሰባት ምክንያቶችን በዚህ ትምህርታዊ ቪድዮ ውስጥ ታገኛላችሁ። እስከመጨረሻው ተከታተሉት!
    ዋቢ መጻሕፍት (References):-
    የብሉይና የሓዲስ ኪዳን መጻሕፍት
    ዶ/ር መስከረም ለቺሳ (2014 ዓ.ም)። የፀሓይ ከተማ። አዲስ አበባ፥ ወይንሸት ማተሚያ ቤት።
    “መጽሓፈ ስንክሳር፥ ከመጋቢት እስከጳጕሜን።” አዲስ አበባ፥ ትንሣኤ ማሳተሚያ ድርጅት፤ 1993።
    ተስፋ ሥላሴ ሞገስ (አባ)። ቅዱስ ማርቆስ ኢትዮጵያዊ ነው፤ የተዋሕዶ አንበሣም መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። (አዲስ አበባ፥ 1988)
    “ገድለ ቅዱስ ማርቆስ፥ በግእዝና በዐማርኛ።” አዲስ አበባ፥ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/ሰ/ት/ቤ/ማ/መ/ ማኅበረ ቅዱሳን፤ 2013።
    “ገድል ዘቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ።” መሪጌታ ጽጌ ዘርይሁን እና መምህር ዘሚካኤል ገ/ኢየሱስ (ተርጓሚዎች)።አዲስ አበባ፥ አኰቴት አታሚዎች፥ 2005።
    “የአቡነ ዜና ማርቆስ ገድል፥ በአማርኛ።” አዲስ አበባ፥ ሳቤላ ማተሚያ ቤት፤ 2005።
    ጌጡ ዘለቀ ገ/ማርያም (ሊቀ ትጉኃን)። ክብረ አበው ነገሥት፤ የአበው ቀደምት ነገሥታት ገዳማት እና ቅዱሳን ነገሥታት ወአድባራት ታሪክ (2007 ዓ.ም)።
    አዜብ በርሄ (ተርጓሚ) (2008)። ዝክረ ቅዱሳት አንስት ዘተዋሕዶ። አዲስ አበባ፥ ጃጃው አታሚዎች እና ዴቬሎፐርስ ኃ.የተ.የግ.ማ.
    Williams, C. (1974). The Destruction of Black Civilization: Great Issues of a Race from 4500 B.C. to 2000 A.D. Chicago: Third World Press.

ความคิดเห็น • 264

  • @badriyaamhbashih-hj5bn
    @badriyaamhbashih-hj5bn 21 วันที่ผ่านมา +60

    እኔ በጣም ነው የምወድሽ እርጋታሽ እወቀትሽ ያስደንቀኛን ለትውልዱ ታሪኩን እንዳውቅ እውቀት እንዲጨብጥ እየሰራሽ ነው እግዚአብሔር አምላክ ለፋትሽን ይቀበልልሽ እመቤቴ ማርያም ከተኩላ እጅ ትጠብቅሽ አመሰግናለሁ እህቴ አድናቂሽ ነሽ

  • @save7997
    @save7997 21 วันที่ผ่านมา +27

    መስኪ ደርባባዋ የኢትዮጵያ እናት እንቁአችን ነሽኮ ቸሩ መድኅኒዓለም ከነ ቤተሰቦችሽ ይጠብቅሽ 💚💛❤️

  • @Getachew-n2f
    @Getachew-n2f 21 วันที่ผ่านมา +10

    የኔ ልጅ አኔ ሽማግሌ ነኝ ልመርቅሽ እግዝአብኼር ስራሽን ይባርከው አንቺና ዶ/ር ሮዳስ የኢትዮጵያ ታላቅነት ከመሠረቱ በማስረጃ አስደግፋችሁ እንዲበራ እያደረጋችሁ ሰለ ሆነ ብርሀናችሁ ይብራ ዕድሜና ጤና ይስጣችሁ

  • @afro90s78
    @afro90s78 21 วันที่ผ่านมา +3

    ዶር መስከረምን እኔ ነገ አደለም ማደንቃት ማከብራት ያሬዶ ዛሬ ነው በቃ የዲያቢሎስን እና የተከታዮቹን አሰራር እግር በእግር እየተከተለች እያጋለጠች ስለሆነ ዛሬ ላይ ምህራባውያን ፈጣሪ የለም ወደ ማለት የደረሱት በጴንጤዎች አስተምህሮ በልጽገው ነው የኛዎቹም መንገድ ላይ ናቸው የመጀመሪያ እቅዳቸው ደሞ ኦርቶዶክሳዊ ስነ ምግባርን መሸርሸር ነው ...... መዳኒያለም ረጅም እድሜና ጤናን ያድልሽ ዶክተር መስከረም በጣም ለዚ እየጠፋ ላለ ትውልድ ታስፈልጊዎለሽ!!

  • @bruktawittesfay-or7de
    @bruktawittesfay-or7de 21 วันที่ผ่านมา +16

    በነገራችን ላይ ስለ ሀገሬ ጥርት ያለ ግንዛቤ እንዲኖረኝ ከፍተኛ ፍላጎት ጭረሽብኛል። ገለጻዎችን በናፍቆት ነው ምጠብቀው የመስቀሉ ኃይል ከአንቺ ጋር ይሁን። 🙏

  • @Msalemkassa
    @Msalemkassa 21 วันที่ผ่านมา +14

    ከእግዚአብሔር እውቀት ሲሰጥ እንዲህ ነው ። እኔ በግሌ ሳዳምጥሽ የሚሰማኝን ስሜት መግለጽ በእውነት አልችልም ። ብቻ እግዚአብሔር ይባርክህ ። እታለም ❤❤❤

  • @Sahlemariam
    @Sahlemariam 21 วันที่ผ่านมา +12

    እጅግ ደስ የሚል አዕምሮን አልፎ የሚሄድ ዕውቀት ነው፣ ሳይበላ የሚያጠግብ ምግብ ይመስላል። እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ዕውቀት ይጨምርልሽ፣ ቤተሰቦችሽን ይባርክ።

  • @ElsaKetema
    @ElsaKetema 21 วันที่ผ่านมา +19

    እናመሰግናለን ዶ/ር ጊዜ ሰጥተሽ ታሪካችንን እንድናውቅ ስለምታደርጊን እድሜ ከጤና ፈጣሪ ጨምሮ ይስጥሽ

  • @abrehamendale4393
    @abrehamendale4393 21 วันที่ผ่านมา +12

    ዶ/ር መስከረም የኢትዮጵያ ብራና መፅሐፍ ነሽ

  • @kumlachewbizuneh3589
    @kumlachewbizuneh3589 21 วันที่ผ่านมา +10

    ሰላም መስኩ። ተበረኪ ዕድሜ እና ጤና ከፀጋ ጋር ይስጥልን። የዕውቀትን ወተት እንደ ጋትሺኝ ሁሉ መድኃይኔዓለም በፀጋ እና በበረከት ይሙላሽ።

  • @FekaduShiferaw
    @FekaduShiferaw 21 วันที่ผ่านมา +21

    ድንቅ ነሽ፣ሃያሏ ኢትዮጵያ ባንች ልቦና እንዳልለች ይሰማኛል።

  • @Ja-yu7sg
    @Ja-yu7sg 21 วันที่ผ่านมา +8

    The iron Lady from orthodox...proud

  • @Nevinhope
    @Nevinhope 21 วันที่ผ่านมา +6

    ❤❤❤ኣንቺና ዘርሽ ማንዘርሽ ይባረክ

  • @bruktawittesfay-or7de
    @bruktawittesfay-or7de 21 วันที่ผ่านมา +5

    ዛሬ ያቀረብሽልን ትምህርታዊ ገለጻ እኔም ጥርት ያለ ግንዛቤ እንዲኖረኝ ከምፈልጋቸው ነገሮች አንዱ ነበርና። ❤❤❤❤❤❤

  • @melkamumitkue2990
    @melkamumitkue2990 21 วันที่ผ่านมา +6

    መስክ እንኳን ደህና መጣሽልኝ እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማሪያም እናታችን ትጠብቅልኝ ከመላው ቤተሰብሽ የሀገር ሀብት /ኩራት /ችን ነሽ እረጅም እድሜ ከጤና ጋር ይስጥልኝ አሜን አሜን አሜን በሉ

  • @naty-dere-5739
    @naty-dere-5739 21 วันที่ผ่านมา +4

    I always think the Egyptian pharaohs look more Afar people than the modern Egyptians. Love and respect from Ethiopia Africa.

  • @danielbelete1311
    @danielbelete1311 21 วันที่ผ่านมา +6

    ስጦታችን የአገልግሎት ዘመንሽን ያርዝምልን

  • @bruktawittesfay-or7de
    @bruktawittesfay-or7de 21 วันที่ผ่านมา +6

    ያክብርልን መስኪ። ግራ መጋባቶችን ስለምታጠሪልን: በጌታ ኃይል ክፉ ሀሳቦችን ስለምትደረማምሽልን ጌታ ያክብርሽ። በሁሉ ነገር ከአንቺ ጋር ይሁን።

  • @user-wv6nd7rd4p
    @user-wv6nd7rd4p 21 วันที่ผ่านมา +12

    አሜን አሜን ቃል ህይወት ያስማልን። በዕድሜ በጤና በፀጋው በክብር ያቆይልን መምህር ትዶር / መስከረም እግዚአብሔር አብዝቶ እውቀት ን ይስጥህ ❤❤❤🎉🎉🎉

  • @helentesfaye5830
    @helentesfaye5830 21 วันที่ผ่านมา +3

    እድሜ፡ከጤናዬስጥሽ፡እህቴ፡እመብርሀን፡ትጠብቅሽ።