ไม่สามารถเล่นวิดีโอนี้
ขออภัยในความไม่สะดวก

በኢትዮጵያ “ቀዳሚ” እና “አሳሳቢው” የሰብአዊ መብት ጥሰት፤ በሲቪል ሰዎች ላይ የሚደርስ ሞት እና የአካል ጉዳት መሆኑን ኢሰመኮ አስታወቀ

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 5 ก.ค. 2024
  • በኢትዮጵያ ባለፈው አንድ ዓመት ከተከሰቱ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ውስጥ በቀዳሚነት አሳሳቢ የሆነው፤ በሲቪል ሰዎች ላይ የደረሰው የሞት እና የአካል ጉዳት መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ።
    በርካታ ሰዎች ለሞት እና ለአካል ጉዳት የተዳረጉት፤ በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች እና በታጣቂ ቡድኖች በተወሰዱ እርምጃዎች መሆኑንም ኮሚሽኑ አስታውቋል።
    ብሔራዊው የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ተቋም ይህን የገለጸው፤ “የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ሁኔታ” የዳሰሰ ዓመታዊ ሪፖርት ትላንት አርብ ሰኔ 28፤ 2016 በዋና መስሪያ ቤቱ ይፋ ባደረገበት ወቅት ነው።
    ከሰኔ 2015 እስከ ሰኔ 2016 ድረስ ያለውን ጊዜ የሚሸፍነው ይህ ሪፖርት፤ አሳሳቢ እና በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን፣ መልካም እምርታዎችን እና ምክረ ሀሳቦችን የያዘ ነው። በሶስት ክፍሎች የተሰናዳው ባለ 132 ገጽ ዓመታዊ ሪፖርት፤ በኢትዮጵያ ያለውን የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ “ጠቅለል ባለ መልኩ የሚያሳይ” መሆኑን የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ተናግረዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
    🔴 ይህን ሊንክ ተጭነው ethiopiainside... ዝርዝር ዘገባውን በጹሁፍ ያንብቡ
    ------------------------------------------------------------------------------
    የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ትኩስ ዜናዎችን እና ወቅታዊ ዘገባዎችን ለመከታተል፦
    ድረ ገጽ ፦ ethiopiainsider...​
    ፌስቡክ ፦ / ethiopiainsider
    ትዊተር (ኤክስ) ፦ / ethiopiainsider
    ቴሌግራም፦ t.me/EthiopiaI...
    ቲክቶክ፦ / ethiopiainsider

ความคิดเห็น •