ไม่สามารถเล่นวิดีโอนี้
ขออภัยในความไม่สะดวก

በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በሚገኙ እስረኞች መካከል ተነሳ በተባለ ግጭት ታራሚዎች መጎዳታቸው ተነገረ

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 18 ส.ค. 2024
  • በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ባለፈው ቅዳሜ በእስረኞች መካከል ተነሳ በተባለ ግጭት ሳቢያ፤ ቢያንስ አምስት ታራሚዎች መጎዳታቸውን የእስረኛ ቤተሰቦች እና የአካባቢው ነዋሪዎች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን በዕለቱ ግጭት እንደነበር ቢያረጋግጥም፤ በክስተቱ “ቀላል ጉዳት የደረሰበት አንድ ታራሚ ብቻ ነው” ሲል አስተባብሏል።
    ግጭቱን ተከትሎ በማረሚያ ቤቱ ሆነው የፍርድ ቤት ጉዳያቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ጋዜጠኞች እና ሌሎች እስረኞች ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት እንዲዘዋወሩ መደረጉን የእስረኞቹ ቤተሰቦች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አስረድተዋል። በቃሊቲ ማረሚያ ቤቱ ግጭት ተቅስቅሶ የነበረው፤ ከሁለት ቀን በፊት ጠዋት ሶስት ሰዓት ገደማ እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።
    ልጃቸው በቃሊቲ ማረሚያ ቤት እንደታሰረ የጠቀሱ አንድ የአካባቢው ነዋሪ፤ ቅዳሜ ጠዋት በቤት ውስጥ እንዳሉ “የመሳሪያ ተኩስ ድምጽ” መስማታቸውን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። በድንጋጤ ውስጥ ሆነው ሁኔታውን ለማጣራት ወደ ማረሚያ ቤት አቅጣጫ ሲሄዱ፤ በአቅራቢያው ባሉ መንገዶች “በፓትሮል የመጡ” በርካታ የፌደራል ፖሊሶች መመልከታቸውን አስረድተዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
    🔴 ዘገባው ን በጹሁፍ ለማንበብ ይሄን ሊንክ ይጫኑ 👉 ethiopiainside...
    -------------------------------------------------------------------------------------------
    የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ትኩስ ዜናዎችን እና ወቅታዊ ዘገባዎችን ለመከታተል፦
    ድረ ገጽ ፦ ethiopiainsider...​
    ፌስቡክ ፦ / ethiopiainsider
    ትዊተር (ኤክስ) ፦ / ethiopiainsider
    ቴሌግራም፦ t.me/EthiopiaI...
    ቲክቶክ፦ / ethiopiainsider

ความคิดเห็น •