ไม่สามารถเล่นวิดีโอนี้
ขออภัยในความไม่สะดวก

ቀጄላ መርዳሳ እና ገብረመስቀል ጫላ ከሚኒስትርነታቸው ተነሱ | Ethiopia | Kajela Merdassa | Gebremeskel Chala | Insider

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 18 ส.ค. 2024
  • በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ካቢኔ ውስጥ ካሉ ሶስት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች መካከል አንዱ የነበሩት አቶ ቀጄላ መርዳሳ፤ ከሚኒስትርነታቸው ተነስተው አማካሪ ተደረጉ። ለሶስት ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር የነበሩት ገብረመስቀል ጫላ ከካቢኔ አባልነታቸው ተሰናብተው፤ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሹመዋል።
    አቶ ቀጄላ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ካቢኔ የተቀላቀሉት፤ በአቶ አራርሶ ቢቂላ የሚመራውን የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አንድ አንጃ በመወከል ነበር። ገዢው ብልጽግና ፓርቲ ስድስተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ማሸነፉን ተከትሎ፤ በመስከረም 2014 ዓ.ም. በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከተሾሙ 22 ሚኒስትሮች መካከል አቶ ቀጄላ አንዱ ነበሩ።
    በዚህ ወቅት የባህል እና ስፖርት ሚኒስትርነት ሹመት ካገኙት አቶ ቀጄላ በተጨማሪ፤ ሁለት የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችም የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ካቢኔ አባል ሆነዋል። አቶ ቀጄላ ከስልጣናቸው መነሳታቸው በተነገረበት በዛሬው ዕለት፤ የሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸውን የ2016 በጀት ዓመት የዘርፍ ዕቅድ አፈጻጸም እና የመጪውን ዓመት እቅድ አስመልክቶ ውይይት ሲያደርጉ ነበር። (ኢትዮጲያ ኢንሳይደር)
    ተጨማሪውን ለማንበብ ይሄን ሊንክ ይጫኑ:- ethiopiainside...
    -------------------------------------------------------------------------------------------
    የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ትኩስ ዜናዎችን እና ወቅታዊ ዘገባዎችን ለመከታተል፦
    ድረ ገጽ ፦ ethiopiainsider...​
    ፌስቡክ ፦ / ethiopiainsider
    ትዊተር (ኤክስ) ፦ / ethiopiainsider
    ቴሌግራም፦ t.me/EthiopiaI...
    ቲክቶክ፦ / ethiopiainsider

ความคิดเห็น • 1

  • @nano2012
    @nano2012 หลายเดือนก่อน

    ጥርት ያለ ያልተንዛዛ ምርጥ ዜና:: Thanks❤❤