ክፍል አምስት ኦሪት ዘዳግም/Part five Torah Deuteronomy

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 25 มิ.ย. 2024
  • የዘዳግም መጽሐፍ የመጽሐፍ ቅዱስ አምስተኛው መጽሐፍ ሲሆን ለኦሪት ደግሞ የመጨረሻው ክፍል ነው፡፡
    ኦሪት ዘዳግም፣ የእስራኤል ሕዝብ ለብዙ ጊዜ በምድረ በዳ ከተጓዙ በኋላ ወደ ከነዓን ለመግባት ጥቂት ሲቀራቸው በሞአብ ምድር በቆዩበት ጊዜ ሙሴ በተከታታይ ያደረገላቸውን ንግግር የያዘ ነው፡፡ የኦሪት ዘዳግም መጽሐፍ ቃል የመጣው ከግሪኩ ዲትሮኖሚዮን ከሚባለው ሲሆን ትርጉሙም ሁለተኛው ህግ ማለት ነው፡፡
    በኦሪት ዘዳግም ተመዝግበው ከሚገኙት በጣም ጠቃሚ ከሆኑት ነገሮች መካካል አንዳንዶቹ የሚከተሉት ናቸው‹-
    1. ሙሴ ባለፉት አርባ ዓመቶች ውስጥ ስለ ተፈጸሙት ታላላቅ ድርጊቶች በማስታወስ ይናገራል፤ እግዚአብሔር በምድረ በዳ እንዴት እንደ መራቸው ሕዝቡን በማስታወስ፣ ለእግዚአብሔር ታማኞች እንዲሆኑና በቅንነት እንዲታዘዙት ያሳስባቸዋል፡፡
    2. ሙሴ ዐሥሩን ትእዛዞች እንደገና እየጠቀሰ በተለይ ስለ መጀመሪያው ትእዛዝ ፍች አብራርቶ እያስረዳ፣ ሕዝቡ እግዚአብሔርን ብቻ እንዲያመልኩ ያሳስባቸዋል፤ ከዚህም ጋር በማያያዝ እስራኤላውያን በተስፋይቱ ምድር ስለሚተዳዳሩባቸው ልዩ ልዩ ሕጎች በድጋሚ እየጠቀሰ ያብራራል፡፡
    3. ሙሴ፣ እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር የገባው ቃል ኪዳን ምን ዐይነት እንደ ሆነ በመተርጎም፣ ሕዝቡ ለዚህ ቃል ኪዳን ያላቸውን ታማኝነት እንዲያድሱ ያስገነዝባቸዋል፡፡
    4. ኢያሱ በሙሴ እግር ተተክቶ የእግዚአብሔር ሕዝብ መሪ በመሆን ይሾማል፤ ሙሴ ስለ እግዚአብሔር ታማኝነት የተቀኘውን መዝሙር ከዘመረና የእስራኤልን ነገዶች በሙሉ ከባረከ በኋላ ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምስራቅ በሚገኘው በሞአብ ምድር ይሞታል፡፡

ความคิดเห็น •