ከ40 ዓመታት በላይ የጸና አገልግሎት! ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 11 ก.ย. 2024
  • "ቤተ ክርስቲያን ለማሠራት ሙዚቃ ይዘጋጅ ተብለን ነበር"
    youtube.com/@M...

ความคิดเห็น • 223

  • @GedionGashaw-xs8mu
    @GedionGashaw-xs8mu 9 หลายเดือนก่อน +106

    ሊቀ መዘምራን ይልማ ሀይሉ በጣም የምወደው ዘማሪ ከልጅነቴ ጀምሮ ስሰማው ነው ያደኩን እስከ አሁን ድረስ አልበሞቹን እሰማቸዋለሁ መቼም የማይጠገቡ ናቸው የአገልግሎት ዘመንህን ይባርክልህ ።

  • @melesgaga2368
    @melesgaga2368 8 หลายเดือนก่อน +1

    እፉፉፉፉ እንጃ ሊቀ መዘምራን ይልማ ሀይሉ ምን ብዬ እንደምገልፅህ ባላቅም እግዚአብሔር አምላክ እድሜና ጤና ይስጥህ

  • @yohanesmengesha1525
    @yohanesmengesha1525 8 หลายเดือนก่อน +2

    ሊቀ መዘምራን ይልማ ሀይሉ በጣም የምወደው ዘማሪ ነው ከሱ ሊላ ሰምቸም አላቅም ❤❤❤❤❤❤

  • @user-bm4lb2gl7p
    @user-bm4lb2gl7p 9 หลายเดือนก่อน +10

    ለኔ ለማልረባዋ የንሠሐ አይኔ እንዲገለጥ የረዳኝ እግዚአብሔር ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉን ተጠቅሞ ነው እግዚአብሔር ይመስገን የመዳኔ ሚስጥር ፀጋውን ብዝት ያድርግልን መምህራችን እህታችን ተባረኪ በስራሽ ሁሉ ድንግል ማርያም ትቅደምልሽ ለኢትዮጵያ ማስተዋልን ይስጥልን አሜን

  • @solomonasratie8575
    @solomonasratie8575 9 หลายเดือนก่อน +37

    ይልማየ በአንተ መዝሙር አማካኝነት ቸሩ እግዚአብሔር ስንቱን ወደ ንስሐ ወደ ተመስጦ መለሰው መሰለህ። ዝማሬ መላእክትን ያሰማልን

  • @estifanossolomon7008
    @estifanossolomon7008 8 หลายเดือนก่อน

    እልል ልልልልልልልልልልል❤❤❤❤❤ሁሌም እማይጠገቡ ልዩ የእግዚአብሔር ስጦታ እድሜ ከጤና ጋር ይስጥልን አሜን አሜን አሜን አሜን ❤❤❤❤

  • @MinasDawit
    @MinasDawit 9 หลายเดือนก่อน

    ሊቀ መዘምራን ይልማ ድፍረት ባይሆንብኝ የእነ መሪጌታ ጸሐይ ብርሃኑ ፣ የመሪጌታ ብርሃኑ ውድነህ እና የሌሎችም የድሮ ዝማሬዎችን በዛ ዘመን የነበሩ ምእመናን ይጠቀሙበት የነበሩ መዝሙሮችን ከማህበረ ቅዱሳን ጋር እና ከሌሎች መዘምራን ጋር ሆናችሁ ብታዘጋጁ ለትውልድ በጣም የሚጠቅምና ለትውልድም አስተማሪ ይሆን ነበር፡፡
    እረጅም እድሜ ከጤና ጋር አምላከ ቅዱሳን የስጥልን!!!

  • @user-od5nv7mi9n
    @user-od5nv7mi9n 8 หลายเดือนก่อน

    ሊቀ መዘምራን ይልማ ሀይሉ በጣም በጣም በጣም የምወደው እኔ ብቻ አይደለውም ልጄ እራሷ የሱን መዝሙር በጣም ነው የምትወደው እና በቢሮም በቤቴም በተለይ በፆም ወራት የሱን ስሰማ ውስጤ ለእግዚአብሄር ቅርብ ይላል ብርታት አገኛለሁ በእውነት በጣም ነው መዝሙሩ ስብከት ናቸው እና እግዚአብሄር እድሜና ጤና ይስጥህ፡፡

  • @nahomNahi-oy6ns
    @nahomNahi-oy6ns 8 หลายเดือนก่อน

    መንፈሳዊ ሕይወቴ እግዚአብሔር በሰጠህ የመዘመር ሀብት ታለመልመዋለህ የዘመኑን መጥፎ እሳቤ በመዝሙሮችኽ ሀይል አልፋቸዋለው መዝሙሮችኽ ለእኔ ያረጉትን ነገር እግዚአብሔር ያቃል።

  • @yeshumethiolove275
    @yeshumethiolove275 9 หลายเดือนก่อน +19

    ዘመን አይሽሬው ድንቅ መዝሙሮቹ እንቁ የተዋህዶ ልጅ ሊቀመዘምራን ይልማ ሀይሉ አሁንም ረጅም እድሜና ጤናን ከአገልግሎት ጋር ያድልልን ❤❤❤

  • @selamawitzewdu4341
    @selamawitzewdu4341 8 หลายเดือนก่อน

    ዝማሬዎች ሁሉ እንዴት እንደምወዳቸው ምንም አላወራርደውም በጣም ድንቅ መዝሙሮች ናቸው ያሳደጉኝ መዝሙሮች ናቸው ቅዱስ ኡራኤል ከደጁ እርቄም አላውቅም ነበር ብዙዎቹ እውነትም እኔ ሐጢያተኛ ስለሆንኩኝ በእንባ ነው የምሰማው

  • @mekdesgullat4281
    @mekdesgullat4281 9 หลายเดือนก่อน +70

    ለሁሉ ሰንበት ት/ቤት ምሳሌ የሚሆን አገልጋይ መዝሙሮቹ ስብከቶች ናቸው
    እድሜ ይስጥልን ከነመላው ቤተሰቦችህ❤

    • @atz7247
      @atz7247 9 หลายเดือนก่อน +2

      አሜን ወንድማችን እናከብርሃለን። እግዚአብሔር ዕድሜና ጤና ያብዛልህ።

    • @yohanessileshe9190
      @yohanessileshe9190 9 หลายเดือนก่อน +1

      እድሜ ከጤና ይስጥልን

  • @alextekebatarekegn2217
    @alextekebatarekegn2217 5 หลายเดือนก่อน

    ሊቀ መዘመር ይልማ ኃይሉ እግዚአብሔር እድሜ እና ጤና ይስጥልን ::

  • @asekilemarayimeyimareyamli7205
    @asekilemarayimeyimareyamli7205 9 หลายเดือนก่อน

    ዝማሬ መላእክት ያሰማልን ማኅበረ ቅዱሳንን ያስፋልን በእውነት አሜን❤❤❤

  • @girmaagumas6886
    @girmaagumas6886 9 หลายเดือนก่อน

    ይልምሽ ልዩ ሰው እግዚአብሔር ዕድሜ እና ጤና ይጨምርልህ!!
    ❤❤❤
    የእንደነዚህ አይነት ሰዎች የህይወት ተሞክሮ በእውነት ለኦርቶዶክሶች አስፈላጊ ናቸው።
    በዚህ አጋጣሚ ማህበረ ቅዱሳንን እናመሰግነዋለን

  • @user-ob3pi9iv4y
    @user-ob3pi9iv4y 9 หลายเดือนก่อน

    ስለሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን የቅዱሳን አምላክ ያገልግሎት ዘመንህን ይባርልክ

  • @gizawbekuretsion1889
    @gizawbekuretsion1889 9 หลายเดือนก่อน +25

    ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ ያንተ መዝሙሮች ከኦሪት ዘፍጥረት እስከ ዮሐንስ ራእይ ያሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል የሚሰብኩ ስለሆኑ ስለ ዘለዓለማዊው ሕይወታችን እንድናስብ የሚያደርጉ ናቸው ። መምህር ዝማሬ መላእክትን ያሰማልን።

  • @lulitsemunigus6201
    @lulitsemunigus6201 9 หลายเดือนก่อน

    ዝማሬ መልእክት ያሰማልን። የአገልግሎት ዘመንህን ይባርክልህ።

  • @user-ie1lm6kb9k
    @user-ie1lm6kb9k 9 หลายเดือนก่อน +27

    ቴክሳስ ዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ለመጀመሪያ ጊዜ ሳየዉ እንዴት እንደተደሰትኩ..እድሜ እና ጤና ይስጥልን ቃለሂወት ያሰማልን ዘማሪ ይልማ ሀይሉ...

  • @saratesfaya2329
    @saratesfaya2329 8 หลายเดือนก่อน

    እረ ክፍል ሁለት😢 ደሞ 1 ደቂቃ የሞላ አልመሰለኝም ሊቀ መዘምራን ይልማ እረጅም እድሜ ከጤና ጋር ይስጥህ🙏

  • @gunatube12
    @gunatube12 9 หลายเดือนก่อน +26

    እውነት ለመናገር የእርስዎን መዝሙር ሰምቸ ወደ አሁኑ ዘማሪዎች ስገባ ከመዝሙር ወደ ሙዚቃ የገባው ይመስለኛል በእውነት አባታችን የቤተክርስቲያን ትልቅ በረከት ነዎት

    • @MulluTesfaye-pw7qo
      @MulluTesfaye-pw7qo 9 หลายเดือนก่อน +2

      የምር እኔም ተቸግሬአለሁ ጓድኞቼ ዘማሪዎች አትምረጭ እያሉ ይነቅፉኛል😂

  • @user-qi6zk6ml3d
    @user-qi6zk6ml3d 8 หลายเดือนก่อน

    እግዚአብሔር ይመስገን አሜን ፫ቃለ ሕይወት ዝማሬ መላእክት ያሰማልን በእድሜ በጤና በቤቱ ይጠብቅልን !🤲🎚

  • @melakubelayneh7850
    @melakubelayneh7850 9 หลายเดือนก่อน +1

    በጣም የማከብርህ እንቁ የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ስላየንህ ደስ ብሎኛል።እግዚአብሔር የአገልግሎት ዘመን ይባርክልን

  • @woyneshetdejene6880
    @woyneshetdejene6880 9 หลายเดือนก่อน +17

    እውነት ነው ሊቀ መዘምራን
    በየቤተክርስቲያኑ ያሉ የአብነት መምህራን ሰንበት ትምህርት ቤቱ የአብነት ትምህርት ቤት። አድርጉት
    በእውነት እግዚአብሔር ቢረዳን ቢሆን የምመኘው ነገር ነው

  • @user-ze1ow4sz9p
    @user-ze1ow4sz9p 9 หลายเดือนก่อน +10

    አክብሮትና ዉዴታ በምን ይገለጻል……… እንዲያዉ ዝም ልበል የብዙዎቻችን ሕይወት መለወጥ አንዱ አንተ ነህ የመዝሙር መምህራችን እንዎዶታለን እናከብሮታለን
    እረጅም እድሜ ከጤናጋ ይስጥልኝ ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሌ ፍጻሜዎት ይመር ተስፋ መንግስተ ሰማያትን ያዋርስልን❤

  • @hirutkebede1319
    @hirutkebede1319 9 หลายเดือนก่อน +4

    እኔ የሊቀ መዘምራንን መዝሙር ስሰማ በቃላት ልገልፀው የማልችለው ልዩ ስሜት ነው የሚሰማኝ። እግዚአብሔር ዕድሜ ከጤና ጋር ይስጥልን። ፀጋውን ያብዛልህ።

  • @alexdrsha1079
    @alexdrsha1079 8 หลายเดือนก่อน

    እግዚአብሔር ያክብርልን በእውነት አስተማሪ የሆነ ህይወት ነው

  • @GashuMan-zo1xg
    @GashuMan-zo1xg 9 หลายเดือนก่อน +4

    እንደኔ የሚወደው ይኖር ይሆን ከቃላት በላይ በሆነ መልኩ የሕይወት ትምህርት ቤቴ ነው ልዑል እግዚአብሔር በእድሜ በፀጋ ይጠብቀው።

  • @ZemaritFirehewotAlemu-ms6ec
    @ZemaritFirehewotAlemu-ms6ec 8 หลายเดือนก่อน

    በአንተ መዝሙር ያልተጽናናው ማነው?እረዥም እድሜ ከጤና ጋር ሰጥቶ ያኑርልን።ዝማሬ መልአክትን ያሰማልን።

  • @MimiMimi-bf5gg
    @MimiMimi-bf5gg 9 หลายเดือนก่อน

    በጣም የምወደውን ዘማሪ ስላቀርብሺልን አንቺንም እናመሰግናለን መስኪየ አቡዳቢ መጠሽ በአይን ብቻ አይቺሽ ደንግጬ በርቱ ብቻ ብየሽ በመሄዴ ይቆጨኛል ግን ስላልጠበኩ ደንግጬ ነው በጣም ነው ምወድሽ ማር ዘማሪና ስአኢ ይልማ በጣም ነው ምወድህ እድሜና ጤናውን ያድልልን

  • @SolomonVA
    @SolomonVA 9 หลายเดือนก่อน +2

    ሊቀ መዘምራን ይልማ ሀይሉን በጣም በጣም በጣም የማከብረው ወንድማችን ነው፡ መዝምሮቹን ከ30 አመት በላይ አውቃቸዋለሁ፡ በሀይማኖት አጽንተውኛል፡ ለትንሽ ጊዜም ቢሆን በሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥም በዝማሬ እንዳገለግል መሰረት ሆነውኛልና ስለሱ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፡ እግዚአብሔር ፀጋውን ያብዛልህ፡ ከነ መላው ቤተሰብህ እግዚአብሔር ጠብቆ ለቅድስት አገርህ ያብቃህ፡ እኔም እሱ ያለበት አገር ስለሆነ የምኖረው ወደ አገሬ ለመመለስ የእግዚአብሔር ቀን እየጠበኩ ነው። ሁላችን ከአገር ውጭ የምንኖረውን የተዋህዶ ልጆች እግዚአብሔር በያለንበት ጠብቆ ለቅድስት አገራችን ያብቃን። አሜን !

  • @azabmenbere7528
    @azabmenbere7528 9 หลายเดือนก่อน +2

    የተዋህዶ እንቁ እድሜ ከጤና የድንግል ማርያም ልጅ ያድልልን

  • @user-ti5os6oh8o
    @user-ti5os6oh8o 9 หลายเดือนก่อน +15

    እጅግ የምንወድህ የምናከብርህ የቤተክርስቲያናችን እንቁ አገልጋይ! በአንተ መዝሙር ያልተሰበከ ያልተማረ የቤተክርስቲያን ልጅ አይኖርም!❤❤❤ እድሜና ጤና አብዝቶ ይስጥልን❤ እንደእኔ በማልቀስ መዝሙሮቹን የሚዘምራቸው ማንአለ? እንደ ፀሎት ነው የምጠቀማቸው ብዙዎቹን!

    • @MulluTesfaye-pw7qo
      @MulluTesfaye-pw7qo 9 หลายเดือนก่อน +3

      የእሱን መዝሙር ከመስማቴ የተነሳ የቸብቸቦ መዝሙር አይስበኝም።መዝሙሮቹ በዉስጣቸዉ መንፈስ ቅዱስ አለ ፀጋዉ ይብዛለት።

    • @dawitashenafi477
      @dawitashenafi477 8 หลายเดือนก่อน

      እውነት ነው

  • @meseretgenene2141
    @meseretgenene2141 9 หลายเดือนก่อน

    ሊቀ መዘምራን በጣም ነው መዝሙሮቿን የምወደው. መስኪዬ እንዲሁም ሌሎቻችሁም መርሐግብር የምታቀርቡ ወይም የምታዘጋጁ ፀጉራችሁን ሸፍኑ ከእናንተ የሚያንሱትን መመልከት እኮ በቂ ነው እንደምታስተካክሉ አምናለሁ አመሰግናለሁ!!!

  • @babydachew1757
    @babydachew1757 9 หลายเดือนก่อน +5

    ጥሩ ነው በርቺ ግን እባክሽን ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ከነ ቤተሰቡ አቅርቢልን እባክሽ …………ይቅረብ የምትሉ like arguu eski plz plz plz

  • @egziharya4826
    @egziharya4826 9 หลายเดือนก่อน +6

    ሊቀመዘምራን ይልማ እድሜ ከጤና ይስጥልን እኔ እሱና ሊቀ መዘምራን ኪነ ጥበብ መዝሙሮች ሰምቼ አልጠግብም ያኑፁኛል ይገስፁኛል ለንስዓ ያነሳሱኛል አመስጋኝ ያደርጉኛል ነውሬን ( ኃጢአቴን ) ያሳዩኛል

  • @yeshiwas8757
    @yeshiwas8757 9 หลายเดือนก่อน +3

    መጽሐፍ ቅዱስን በእናቶች ለልጆች = የተሰኘ ፕሮጀክት መጀመር እንዳለበት ከዚህ ቃለ ምልልስ ተረድቻለሁ ። እናም ዋና ማእከሉ ስርዓተ ትምህርቱን ቢያዘጋጅ የታችኛዉ መዋቅር እና ሰ/ት/ቤቶች ደግሞ ቢተገብሩት እላለሁ ።

  • @gunatube12
    @gunatube12 9 หลายเดือนก่อน +9

    እረጅም እድሜ ይስጥልን አባቶች መዝሙርዎ ከስብከትም በላይ ናቸው ❤

  • @menbereslasemenbereslase1242
    @menbereslasemenbereslase1242 9 หลายเดือนก่อน +7

    አንጋፋውን ሊቀ መዘምራን ኪነ ጥበብን ብታቀርቡልን በእርሱ መዝሙር ነው ለንስሐ የበቃሁት አሁንም መንኚ መንኚ ነው ሁሉም መዝሙራቸው የንስሐ ብቻ ነው እድሜና ጤና ይስጣቸው የነፍስ አባቴ ❤❤

  • @tsihonbedane5351
    @tsihonbedane5351 9 หลายเดือนก่อน +3

    ወደ አንቺ የመጣው በብሩህ ደመና ከሶስቱ አካል አንዱ ክርስቶስ ነውና... ..
    ውል ውል አለኝ ደጅህ ...
    ኢትዮጵያ ሆይ ተነሽ... ስንቱ ይነገራል:: በጣም ነው የማከብርዎት የምወድዎት:: ፀጋዎ ከአምላካችን መሆኑ ግልፅ ነው:: የሚያስተምሩ ቀናም የሚያረጉ ናቸው:: አሁንም በርቱልን:: ዝማሬ መላእክትን ያሰማልን:: መንግስተ ሰማያት ያውርስልን::

  • @kdox1tube
    @kdox1tube 9 หลายเดือนก่อน +1

    ከልቤ ከምወዳቸው አሉ ከምላቸው ዘማሪዎች መካከል አንዱ ነው ባገኝው ከልብ ደስ ይለኛል

  • @hirutabetu
    @hirutabetu 9 หลายเดือนก่อน +3

    በጣም የምወደዉ የማከብረዉ ሊቀመዘምራን ይልማ ኀይሉ ቀሪ ዘመንህን እግዚአብሔር ይባርክልህ

  • @user-tz1hf4dl4j
    @user-tz1hf4dl4j 9 หลายเดือนก่อน +13

    ከልጅ ልጅ የሚተርፍ ስራ ድንቅ የነፍስ ስራ
    አባታችን በእድሜ በጤና ይጠብቅልን የአገልግሎት ዘመንዎትን ይባርክልን ስዕል እንደሚስሉ አላውቅም ነበር።
    ሊቀ መዘምራን ይልማ ሐይሉ ያቆይልን 👏⛪

  • @abaynehtadesse1278
    @abaynehtadesse1278 9 หลายเดือนก่อน +1

    የሊቀ መዘምራን ይልማ ሀይሉ መዝሙሮችን ሁል ጊዜ በሰማሁ ቁጥር ሰላም እና መረጋጋትን ይሰጠኛል
    ወንድማችን እግዚአብሔር እድሜና ጤና አብዝቶ ይስጥልኝ ፡፡

  • @hanichokemerkato8873
    @hanichokemerkato8873 9 หลายเดือนก่อน

    ሊቀ መዘምራን ይልማ ሃይሉ ስለመዝሙሮች በሙሉ እናመሰግንሃለን ፣ በወጣትነቴ ጊዜ ካንተ መዝሙሮች በስተቀር ሌላ ነገር መስማት አልፈልግም ነበር ከቁጥር 3 - 9 ያሉትን በቃሌ እስካሁን አስታውሳለሁ ፣ ህይወቴንም ቀይሮታል ፣ ሁሌም በአካል ባገኘው ብዬ እመኝ ነበር፣ ቀሪው ጊዜህም የተባረከ ዪሁን,

  • @berhanuasnake7082
    @berhanuasnake7082 9 หลายเดือนก่อน +1

    የተወደድከው የእግዚአብሔር አገልጋይ ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ ረዥም እድሜና ጤና እግዚአብሔር ያድልህ!

  • @degusamrawi2123
    @degusamrawi2123 8 หลายเดือนก่อน

    እግዚአብሔር ይስጥልን ❤❤❤

  • @rahilmengusto4033
    @rahilmengusto4033 9 หลายเดือนก่อน +7

    መሻት ብቻ ነው የሚጠብቅብህ እግዚአብሔርን ጥራው እመን ትድናለህ አባታችን ሊቀ መዘምራን ይልማ ሐይሉ እማምላክ ትጠብቆት ከመላው ቤተሰቦት ጋር አቤት እርጋታ እኔ የርሶን መዝሙር ስሰማ በደንብ እንደዝማሬ ሳይሆን እንደትምህርት ነው የማዳምጠው❤❤❤❤❤

  • @terbinosmolla1695
    @terbinosmolla1695 9 หลายเดือนก่อน +1

    ውድ ወንድሜ እግዚአብሔር የአገልግሎት ዘመንህን ያርዝመው።ሁሌም ትናፍቀኛለህ በቅርቡ እንደማገኝህ ተስፋ አደርጋለሁ።

  • @Etho19pia
    @Etho19pia 7 หลายเดือนก่อน

    ዘማር መሆን ፈልጋለው ከወንድሜ ይልማ ጋር ብዘምር የዕድሜየ ምኞት ነው እግዚአብሔር ቀሪውን ዘመንህን ይባርክልህ

  • @meseretdessalegne9096
    @meseretdessalegne9096 9 หลายเดือนก่อน +1

    ዝማሬ መላዕክትን ያሰማልን ሊቀመዘምራን ይልማ። እጅግ አድርጌ አከብርሃለሁ። ረጅም የአገልግሎት ዕድሜ እና ጤና መድሃኒያለም ያድልህ።መስኪ ይሄን ቃለ መጠይቅ ስለ ዘጋጀሸ እናመሠግናለን ።

  • @ffitsumgenene
    @ffitsumgenene 9 หลายเดือนก่อน

    ቃለህይወት ያሰማልን ❤

  • @nisreenrabah6212
    @nisreenrabah6212 9 หลายเดือนก่อน +2

    ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ. እደሜና. ጤና የሰጦውቶ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤

  • @ZemaritFirehewotAlemu-ms6ec
    @ZemaritFirehewotAlemu-ms6ec 8 หลายเดือนก่อน

    ቁጥር አንድ ከልጅነቴም የምወደው መዝሙርና ዘማሪውም ተወዳጅ።ዕድሜ ይስጥልን።

  • @Embetebirmeji
    @Embetebirmeji 9 หลายเดือนก่อน +4

    ሊቀ መዘምራን ይልማ ሀይሉ በጣም የምወደው ዘማሪ ከልጅነቴ ጀምሮ ስሰማው ነው ያደኩን እስከ አሁን ድረስ መቼም የማይጠገቡ ናቸው የአገልግሎት ዘመንህን ይባርክልህ ።

  • @ayalneshgesese7412
    @ayalneshgesese7412 9 หลายเดือนก่อน +1

    የምናከብርዎት ፡ የምንወዶት ፡ ሊቀ ፡ መዘምር ራን ፡ ዝማሬ ፡ መላእክት ፡ ያሰማልን ፡

  • @Aresema29
    @Aresema29 9 หลายเดือนก่อน +11

    የደብረፅጌ ቅዱስ ኡራኤል ስንበት ትምህርት ቤት ፍሬ የሽዋማማሽ ልጅ ስላየሁክ ደስ ብሎኛል. እግዚአርያን የመስለች ፍሬ አፍርትሀል የአንተን እግር ተከትላ ስለምትዘምር ስለማያት በጣም ደስ ይለኛል. በሚገርም ሁኔታ በልጅነቴ እያየሁ አድጌ በድጋሚ አንድ ስቴት Minnesota በመኖሬ ሁልግዜ ሳይህ ደስ ይለኛል ረጅም እድሜ ከጤና ጋር ይስጥህ ቅዱስ ኡራኤል ከነመላው ቤተስብህ ይጠብቅህ🙏

  • @Habtam-lh4zw
    @Habtam-lh4zw 9 หลายเดือนก่อน +3

    መዝሙሮች ሁሉ በእውነት በእግዚአብሄር መንፈስ ታግዘው የተዘመሩ ናችው።እጅግ በጣም ጥልቅ የሆነ ግጥምና ዜማ አላቸው። የመላዕክት ዝማሬ ያሰማልን።

  • @zemarittigestsileshi8386
    @zemarittigestsileshi8386 9 หลายเดือนก่อน +3

    ወይ ምነው አጠረ??
    ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ -- ምርጥ ሰው! በመዝሙር ብቻ ሳይሆን በብዙ ነገሮች ምርጥ የሆነ ሰው ነው! እንወድሀለን !

    • @cassiopeia4672
      @cassiopeia4672 9 หลายเดือนก่อน

      ክፍል ሁለት አለው እንጂ ደግነቱ

  • @melefufa
    @melefufa 9 หลายเดือนก่อน +1

    Yilmaye edme ena tena yistek tebarek

  • @papirocicvtrjd6738
    @papirocicvtrjd6738 9 หลายเดือนก่อน +8

    ሁሌ ተሞክሮውን መስማት የምፈልገው ሰው ነው ከልጅነቴ ጀምሮ ስሰማው ያደኩት የሱን መዝሙር

  • @emuyayene5811
    @emuyayene5811 9 หลายเดือนก่อน +2

    በጣም የሚቆጨኝ ይልማ የመጀመሪያውን መዝሙር የተቀረፀበት ባለ ሁለት ጎራሽ ቴኘ ማስቀረት አለመቻሌ በጣም ይቆጨኛል ያ ቴፕ የነማን እንደነበር መምህር ይልማ ያውቀዋል ያቺ ቴፕ የነ ታደለች አስፍሀ ነበረች

  • @mesismart1332
    @mesismart1332 9 หลายเดือนก่อน +2

    ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ ቃለ ሕይወት ያሰማልን፣ በጤና ፣ በዕድሜ ፣ በፀጋ ይጠብቅልን፧

  • @yosefYosef-zo1wj
    @yosefYosef-zo1wj 9 หลายเดือนก่อน +1

    በዝህ ዘመን ይልማን የመሰለ አገልጋይ ዘማሪ ስለሰጠን እግዚአብሔር እናመሰግናለን መዝሙሮችህ ሁሉ ቤተክርስቲያናችንን የሚያመለክቱ ናቸው ፀጋው ያብዛልህ

  • @semharsolomon2186
    @semharsolomon2186 9 หลายเดือนก่อน

    Zemari melaket yasemalen leka mezemeran. Egzabher tsegun yabzaleh. Betam meyastemer Hewitt 🙏🙏🙏

  • @መሲየወልድያዋ
    @መሲየወልድያዋ 9 หลายเดือนก่อน +2

    ሊቀመዘምራንይልማሀይሉ። የተዋህዶ። አይንነህየኛ። ጀግና❤❤❤❤❤❤❤

  • @AbebeTeka-ne4ux
    @AbebeTeka-ne4ux 9 หลายเดือนก่อน +1

    የይልማ የምስጋና መዝሙሮቹ በሙሉ በጣም እሚገርምና እሚመስጡ ናቸው

  • @brhanabi3755
    @brhanabi3755 9 หลายเดือนก่อน +2

    በጣም የምንወድህ ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ በእውነት እግዚአብሔር አምላክ በእድሜና በጤና ያቆይልን ይጠብቅልን

  • @Andinet-f6b
    @Andinet-f6b 9 หลายเดือนก่อน +1

    ሁለት ምርጦች መስኪዬ አለሽ ስወድሽ ጀግኒት አትጥፊብኝ ለልጆቼ ምሳሌ !!!ለኔ ሁሌም አንደኛ እንቁ የቤተክርስቲያን አገልጋይ ስስታችን መጨረሻህን ያሳምርልን !!!

  • @user-wz9xp9kl4d
    @user-wz9xp9kl4d 9 หลายเดือนก่อน +2

    በእውነት በጣም የምወደው ዘማሪ ነው መዝሙሮቹ የንሰሀ መዝሙሮች ስለሆኑ በተመስጦ ነው ምሰማው

  • @lidiyaseyum9009
    @lidiyaseyum9009 9 หลายเดือนก่อน +1

    ሊቀ መዘምራን በእድሜ በጤና ይጠብቅልን

  • @user-od3bc9xt4r
    @user-od3bc9xt4r 9 หลายเดือนก่อน +1

    ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ በጣም የምወድህ ዘማሪ ዝማሮችህ ሳልሰማ አልውልም ❤❤❤❤

  • @user-mj4ig4gv7n
    @user-mj4ig4gv7n 8 หลายเดือนก่อน

    Meskiye be ewinet egziabher yibarkish...ahun min teredahu meselesh, be gara yetetanew 1 yegara tsiwa endale tesemagn...yehewim yehen dink dink yebetekristian kuami kirs wendimachin zemawoch nachew...
    Egziabher abzito yibarkish...Like Mezemiran kalat yelegnim, kale hiwot yasemalen.

  • @meherat938
    @meherat938 9 หลายเดือนก่อน +5

    በጣም የምወዶት አባታችን ሊቀ መዘምራን ይልማ እድሜ ማቱሳላን ይስጥልን መዝሙሮች ሁሉ ስብከት ናቸው ሕይወት የሚለውጡ የማይሻሩ ዘመን ከዘመን የሚሸጋገሩ ናቸው ጌታ ፍቃዱ ሆኖ ለልጆቼ ጋብዣቸው ብዬ እመኛለው እንደ ጌታ ፍቃድ ልጅ ሲኖረኝ❤

  • @aynalemneri5787
    @aynalemneri5787 9 หลายเดือนก่อน +3

    በእውነት ቃለ ህይወትን ያሰማልን የአንተ መዝሙር ትምህርት ስብከት እንደሁም ወደ ሰማይ የሚነጥቅና የሚመስጥ ነው እረጅም እድሜ ከጤና ጋር ይስጥልን 🙏💕

  • @hanzemi13
    @hanzemi13 9 หลายเดือนก่อน +4

    ዘማሪ ይልማ ሀይሉ እእድሜ ጤና ይስጥልኝ በእውነት ከልድነቴ ጀምሮ ነው መዝሙሩን የማዳምጠው በዝማሬ የሚሰብክ ሰባኬ ወንጌል ነው🙏🙏🙏

  • @addisnega4662
    @addisnega4662 9 หลายเดือนก่อน +1

    Bedme bestega yanurlin yante mezmur stelotm sibketm nachew zimare melakt yasemaln

  • @YeshiAdmasu-tz9fy
    @YeshiAdmasu-tz9fy 9 หลายเดือนก่อน +1

    እዉነት ነዉ ሊቀ መዘምራን ሰንበት ተማሪ ነበርኩ እያሉ ወደ ምንፍቅናዉ አለም የሄዱት ጠለቅ ያለ እዉቀት ስለ ማያገኘ ነዉ

  • @eyasum.dessalegn2444
    @eyasum.dessalegn2444 9 หลายเดือนก่อน +2

    tewedaj lijishin himamun sitayi...የአገልግሎት ዘመንህን ይባርክልህ ።

  • @demewozakalu1058
    @demewozakalu1058 9 หลายเดือนก่อน +2

    ተወዳጁ ሊቀ መዘምራን ይልማ እግዚአብሔር
    የአገልግሎት ዘመንህን ይባክ።

  • @user-dj6xe1yh1k
    @user-dj6xe1yh1k 9 หลายเดือนก่อน +3

    የተዋህዶ እንቁ❤❤❤❤

  • @besufekadsiyabara9332
    @besufekadsiyabara9332 9 หลายเดือนก่อน +1

    እጅግ የምወዳውና የማከብረው ሊቀ መዘምራን ይልማ የዝማሬ ፋና ወጊ ነው ብል ማጋነን አትሆንብኝም። እኔም በተለይ *ወዴት ነው ያለህው*ን ከቤ/ክ ራቅ ለሚሉ ሁሉ የምጋብዘው ድንቅ መዝሙር ነው። እረጅም እድሜ ከጤና ጋር ያድልልን🙏

  • @hometube8205
    @hometube8205 9 หลายเดือนก่อน +2

    እግዚአብሔር አምላክ እድሜን ከጤና ጋር ያድልልን ይጠብቅልን አባቴ

  • @yordanosadigo
    @yordanosadigo 9 หลายเดือนก่อน

    So happy to see zemari Yilma ! ❤

  • @gizawbekuretsion1889
    @gizawbekuretsion1889 9 หลายเดือนก่อน +3

    ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ ያንተ ዝማሬዎች ከኦሪት ዘፍጥረት እስከ ዮሐንስ ራዕይ ያሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃልን የሚሰብኩ ስለሆኑ ስለ ዘለዓለማዊው ሕይወታችን እንድናስብ የሚያደርጉ ናቸው ፡፡ መምህር ዝማሬ መላዕክትን ያሰማልን፡፡

  • @MulluTesfaye-pw7qo
    @MulluTesfaye-pw7qo 9 หลายเดือนก่อน +1

    የእኔ አባት እግዚአብሔር ፀጋዉን ያበዛልህ
    መዝሙር ብቻ አይደለም መዝሙሮችህ ስብከት ንስሃ ምስጋና መፅናኛ ናቸዉ። አንተን ስለሰጠን እግዚአብሔር እናመሰግናዋለን! እረጅም እድሜ ጤና ኑርልን ሌላ መዝሙር እንጠብቃለን❤

  • @andualemsolomon2826
    @andualemsolomon2826 9 หลายเดือนก่อน +1

    ሊቀ መዘምራን ,ሰዓሊ ግጥምና ዜማ ደራሲ የተዋህዶ እንቁ ይልማ ሀይሉ ❤ረጅም እድሜ ከጤና ያድልልን እንወድሃለን ❤

  • @menbereslasemenbereslase1242
    @menbereslasemenbereslase1242 9 หลายเดือนก่อน +1

    የዛሬ 5 ዓመት ቤይሩት መጥቶ በአካል አይቸዋለሁ እግዚአብሔር አምላክ እድሜ ና ጤና ይስጥህ❤❤

  • @AaBb-kr3bi
    @AaBb-kr3bi 9 หลายเดือนก่อน +1

    የሊቀ መዘምራን ይልማ ሀይሉ መዝሙሮች ምስጋና አምልኮ ስብከት ናቸው ቢሰሙ ቢሰሙ የማይጠገቡ የማይሰለቹ ናቸው ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤

  • @gosaethiopia7089
    @gosaethiopia7089 9 หลายเดือนก่อน +1

    ሊቀ መዘምራን ይልማ ሀይሉ በጣም የምወደው ዘማሪ ከልጅነቴ ጀምሮ ስሰማው በካሴቶቹ ላይ ፎቶውን የማያስቀምጥ ትሁት አገልጋይ ነህ ቃለ ህይወት ያሰማልን

  • @wallelignzelalem7699
    @wallelignzelalem7699 9 หลายเดือนก่อน

    Erejim ye ageligilot zemen yisitilin!!!!!!!

  • @TeshomeTasdesse
    @TeshomeTasdesse 9 หลายเดือนก่อน +2

    ❤❤❤ እጅግ ውድ የተዋሕዶ ልጅ ዘማሪ ሰዓይ ገጣሚ የዜማ ደራሲ ሞዴል መሆን የሚችሉ የቤተክርስቲያናችን አንቱ የሚባሉ በስርአት በሕይወት የጸኑ አገልጋይ ረጅም ዕድሜ ከጤና ጋር ለእኛ እደዚህ አይነት ሰው ስናይ ዛሬ ላይ የሚታዩትን ነገሮች እንድናሸንፍ የሚያግዙን ለወደፊትም ትልቅ ተስፋ ለዛሬዎቹ አገልጋይ ነን ዘማሪ ነን ለሚሉ ትህትና ምግባር ሊማሩ ይገባል ብቻ በእንደዚህ አይነት አገልጋይ ስለሰጠን አምላካችን ይመስገን

  • @bahruashenafi1931
    @bahruashenafi1931 9 หลายเดือนก่อน +1

    እግዚአብሔር እረጅም ዕድሜ ና ጤና ይስጥልኝ በአንተ እስካሁን ሰሀት የማልሰማበት ዕለት የለም

  • @yafet2121
    @yafet2121 9 หลายเดือนก่อน +2

    እግዚአብሔር የአገልግሎት ዘመንህን ይባርከው !

  • @AaBb-kr3bi
    @AaBb-kr3bi 9 หลายเดือนก่อน +1

    ሊቀ መዘምራን ይልማ ሀይሉ እንኳን ወደ ሀገርህ በሰላም መጣህ ያንተ መዝሙሮች ምስጋና ብቻ ሳይሆን ስብከትም ናቸው ረጅም እድሜ እመኝልሀለው ሻሸመኔ ለአገልግሎት መጥተህ በአካል አይቼክ ነበር አሁን እዚህ ላይ ስላየሁክ ደስ ብሎኛል ❤❤❤❤❤❤❤ ኑርልን

  • @mikaelayele4047
    @mikaelayele4047 9 หลายเดือนก่อน +1

    የአገልግሎት ዘመንህ የተባረ ይሁን

  • @bahiranfekadie448
    @bahiranfekadie448 9 หลายเดือนก่อน +2

    እንዎድሃለን

  • @icjdjhfjjdkdro1453
    @icjdjhfjjdkdro1453 9 หลายเดือนก่อน +1

    .ለአባታችን ሊቀ መዘምራ ይልማሀይሉ እግዚአብሄር አምላክ እረጂም እድሜ ከጤናጋር ይስጥልን ነፍስን የሚአለምልም ዝማሪዎች ናቸዉ ሲከፋኝ የእርስዎን መዝሙር ነዉ የምሰማዉ እግዚአብሄር አመላካች ይጠብቀዎት አባታችን❤❤❤🎉

  • @nohamingetahun8833
    @nohamingetahun8833 9 หลายเดือนก่อน

    Egziabher edme ena tena yestelen

  • @rass6636
    @rass6636 8 หลายเดือนก่อน

    በይልማ እና በኪነ ጥብ መዝሙር ......