#ኦቴሎ
ฝัง
- เผยแพร่เมื่อ 28 ต.ค. 2022
- ጸኅፈ-ተውኔት፡- ዊሊያም ሼክስፒር ውርስ ትርጉም፡- ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድኅን
ሚካኤል ቃሲዮ በኦቴሎ ጋሻ ጃግሬነት መሾም በስልጣን ጥም ለተጠማው ኢያጎ ትልቅ ውድቀት ሆኖ ታይቶታል፡፡ የስልጣን ጥሙን ኦቴሎ ላይ በበቀል ለመቁረጥ ይረዳው ዘንድ በዴዝዴሞና ፍቅር ክንፍ ያለውን ሮድሪጎን መጠቀሚያ ለማድረግ አስቧል፡፡ ልበ-ደሀው ሮድሪጎ ዴዝዴሞናን ለማግባት ከአባቷ ጌታ ብራቫንሺዮ ዘንድ ደጋግሞ ደጅ ቢጠናም መልካም ይሁኝታን አላገኘም፡፡ ዴዝዴሞና ከጀግናው የጦር ጄነራል ኦቴሎ ፍቅር አድሮባታል፡፡ የኢያጎ የሴራ ጉንጉን በሮድሪጎ ሰሪነት አምሮና ተውቦ የዴዝዴሞናን በድብቅ ኦቴሎ ዘንድ መሄድ አባቷ ብራቫንሺዮ ባወቁ ግዜ ቀንድ አብቅለው ለአቤቱታ ምክር ቤት ያደርሳቸዋል፡፡ በብራቫንሺዮ አሰያየም ብቸኛ ልጃቸው ዴዝዴሞና ''ለሻንቅላው፣ ፍትወታሙ መተተኛው ሙር'' ኦቴሎ አትገባም ነው፡፡ ከዚያስ. . .