DEWOL | JERICHO | ISRAEL | PALASTINE በጥንታዊቷ ኢያሪኮ ከተማ የቅዱስ ገብርኤል በዓለ ንግስ በተመለከተ ቃለ ምልልስ

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 21 ม.ค. 2025
  • #JERICHO በጥንታዊቷ ኢያሪኮ ከተማ የቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል በድምቀት ተከበረ
    DEWOL ደወል ሚዲያ ታህሳስ 19 ቀን 2017 ዓ/ም
    በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ኢያሪኮ ቅድስት ስላሴና ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ገዳማት ዋና መጋቢ አባ ተክለሐይማኖት ሀይለ ማርያም እና በእስራኤል የኢትዮጵያ አምባሳደር አበው መነኮሳት ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በርካታ ምዕመናን በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል::
    ለሊቱን ከየመን ወደ እስራኤል በተለይም ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ ሚሳኤሎች በመተኮሳቸው ምክንያት የማስጠንቀቂያ ድምጾች ሰዎች ወደ አደጋ መከላከያ ክፍል እንዲገቡ ቢጮሁም ምዕመናኑ ግን በድፍረት ወደ በዓሉ ቦታ በመሄድ በድምቀት ለማክበር ተችሏል
    የበዓሉን ሙሉ መርሐ ግብር በ DEWOL TH-cam ላይ ይመልከቱ::
    ከዚ በታች በጥንታዊቷ ኢያሪኮ ከተማ እንዴት ገዳም ኖረን ?
    ኢያሪኮ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ገዳማት ኢየሩሳሌም
    በጥንታዊቷ የኢያሪኮ ከተማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ገዳም የራሷ የሆነ የይዞታ ቦታ አልነበራትም።
    የንጉስ ሳህለ ስላሴ የልጅ ልጅ የሆኑት ወ/ሮ አማረች ዋለሎ በዋላ መልኩሰው እማሆይ አማረች ዋለሉ የተባሉ እግዚአብሔር በቸርነቱ ለወዳጆቹ ቅዱሳን ከሚያወርሰው ሰማያዊ ተስፋ ርስት ለኔም ያድለኝ ይሆናል ብለው በማመን ከዘመድ ተለይተው ከሀገር እርቀው በኢየሩሳሌም ይኑሩ ነበረ።
    በ1920ዓ/ም ከኢየሩሳሌም 35 ኪ/ሜ ርቃ በምትገኘው በኢያሪኮ ከተማ 3388 ካ/ሜ ስፋት ያለው ቦታ ገዝተው መጠለያ ቤት ሰርተው ሲጠቀሞበት ቆይተዋል ።
    እማሆይ አማረች ዋለሉ በ1930 ዓ/ም በኢያሪኮ የሚገኘውን ቦታቸውንና በቦታው ላይ ያሰሩትን ባለ አንድ ፎቅ ህንጻ በሞት ለተለዩአቸው ለልጅ ልጃቸው ለወ/ሮ ክበበ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ለገዳሙ አውርሰዋል ።
    አሁን የሚታየው ህንፃ ቤ/ክ በገዳሙና በምዕመናን ከፍተኛ ትብብር ከ15 ዓመት በፊት የተሰራ ነው።
    ህንፃ ቤ/ክ ውስጥ የስላሴና የቅዱስ ገብርኤል ጽላት ገብቶበት በወራዊና በዓመታዊ በዓላት እግዚአብሔር ይመሰገንበታል ምዕመናንም በቦታው እየተገኙ በረከት እየተቀበሉ ይገኛሉ ።ቸር ይቆየን
    " ወስብሃት ለእግዚአብሔር"
    • ደወል ዜና እውነተኛ እና ውቅታዊ መ...
    DEWOL - MEDIA

ความคิดเห็น • 2

  • @TibebeSila
    @TibebeSila 20 วันที่ผ่านมา +2

    የቅዱስ ገብርኤል በረከት ይድረሰኝ።
    ቃለ ሕይወት ያሰማልን

  • @betigebeyehu2171
    @betigebeyehu2171 20 วันที่ผ่านมา +1

    ቃለህይወት ያሰማልን እናመሰግናለን ❤❤❤