10ኛ ትምህርት : የዮሐንስ ወንጌል ዋና ዋና ሐሳቦች - መንገድ፣ እውነትና ሕይወት

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 6 ก.พ. 2025
  • ለዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚተከሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ዮሐ. 13:1-20፤ ዮሐ. 14:1-3፤ ዳን. 7:27፤ ዮሐ. 14:5-11፤ ዮሐ. 1:14፤ ቆላ. 1:16፣ 17፤ ዮሐ. 5፡38-40።
    የመታሰቢያ ጥቅስ፡ “መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው” (ዮሐ. 1፡18)።
    የዮሐንስ ወንጌል በአራት ዋና ዋና ክፍሎች የተከፈለ ነው፡ መቅድም (ዮሐ. 1፡1-18)፣ የምልክቶች መጽሐፍ (ዮሐ. 1፡19-12፡50)፣ የክብር መጽሐፍ (ዮሐ. 13፡1-20፡ 31) ) እና መደምደሚያው (ዮሐ. 21፡1-25)። እስካሁን የተደረገው ጥናት በዋናነት በመደምደሚያው እና በምልክቶቹ መጽሐፍ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው፤ በዚህም ኢየሱስ ማን እንደሆነ ለመግለጽ በተአምራቶቹ (በምልክቶቹ)፣ በንግግሮቹ እና በትምህርቶቹ ላይ ትኩረት ያደርጋል። ቀጥለው የሚመጡት የሰንበት ትምህርቶች፣ አሁን በተለይ ወደ ዮሐንስ ሦስተኛው ክፍል፣ ወደ ክብር መጽሐፍ ይሸጋገራሉ።
    የሚገርመው፣ ታዋቂዎቹ ሰባት “እኔ ነኝ” የሚሉ ሐረጎች በምልክት እና በክብር መጽሐፍ መካከል ድልድይ የሚፈጥሩ ናቸው። እነዚህም “የሕይወት እንጀራ” (ዮሐ. 6:35፣ 41፣ 48፣ 51)፣ “የዓለም ብርሃን” (ዮሐ. 8:12፣ ዮሐ. 9:5)፣ “በሩ” (ዮሐ. 10:7፣ 9)፣ “መልካም እረኛ” (ዮሐ. 10:11፣ 14)፣ “ትንሣኤና ሕይወት” (ዮሐ. 11:25)፣ “መንገድ፣ እውነትና ሕይወት” (ዮሐ. 14:6) እና “እውነተኛው የወይን ግንድ” (ዮሐ. 15:1፣ 5) ናቸው።

ความคิดเห็น • 1

  • @getdes7122
    @getdes7122 2 หลายเดือนก่อน

    Lemawrd lemndnw milew video