5ኛ ትምህርት : የእግዚአብሔር ፍቅር እና ፍትሕ - የመለኮታዊው ፍቅር ቁጣ

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 6 ก.พ. 2025
  • የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡- መዝ. 78፣ ዮና. 4:1-4፣ ማቴ. 10:8፣ ማቴ. 21:12, 13፣ ኤር. 51:24, 25፣ ሮሜ. 12፡17-21።
    የመታሰቢያ ጥቅስ፡ “እርሱ ግን መሓሪ ነው፥ ኃጢአታቸውንም ይቅር አላቸው፥ አላጠፋቸውምም፤ ቍጣውንም መመለስ አበዛ፥ መዓቱንም ሁሉ አላቃጠለም” (መዝ. 78፡38)።
    ብዙ ጊዜ የእግዚአብሔር ርኅራኄ ቢወደስም፣ የቁጣው ነገር ብዙዎችን ይረብሻቸዋል። እግዚአብሔር ፍቅር ከሆነ፣ ቁጣውን ፈጽሞ መግለጽ የለበትም ብለው ያስባሉ። ይህ አመለካከት ግን የተሳሳተ ነው።
    ቁጣው በቀጥታ የሚመነጨው ከፍቅሩ ነው። አንዳንዶች የብሉይ ኪዳኑ አምላክ የቁጣ አምላክ እንደሆነ እና የአዲስ ኪዳኑ አምላክ ደግሞ የፍቅር አምላክ እንደሆነ ይናገራሉ። ነገር ግን አንድ አምላክ ብቻ ነው ያለው፤ በሁለቱም ኪዳናት ተመሳሳይ እንደሆነ ተገልጿል። ፍቅር የሆነው እግዚአብሔር በክፋት ላይ ይቆጣል-ምክንያቱ ደግሞ እሱ ፍቅር ስለሆነ ነው። ኢየሱስ ራሱ በክፋት ላይ ጥልቅ ቁጣውን ገልጿል፤ አዲስ ኪዳንም ጻድቅና ተገቢ ስለሆነው የእግዚአብሔር ቁጣ ብዙ ጊዜ ያስተምራል።
    የእግዚአብሔር ቁጣ ሁልጊዜ በክፋትና በኢ-ፍትሐዊነት ላይ የሚገለጽ የጽድቅና የፍቅር ምላሽ ነው። መለኮታዊው ቁጣ ከፍፁም መልካምነቱና ፍቅሩ የተነሳ የሚመጣ የጽድቅ ቁጣ ነው፤ እናም የፍጥረትን ሁሉ ደህንነት ይሻል።
    ባጭሩ የእግዚአብሔር ቁጣ የምንለው ለክፋትና ለኢ-ፍትሐዊነት የሚሰጥ ተገቢ የሆነ የፍቅር ምላሽ ነው። ስለዚህ ክፋት እግዚአብሔርን የተገፉትን ለማዳን እና በአጥፊዎቹም ለመፍረድ እንዲነሳ ያደርገዋል። እንግዲህ መለኮታዊው ቁጣ የመለኮታዊ ፍቅር ሌላው ገጽታ ነው ማለት ነው።

ความคิดเห็น • 1

  • @MekdesTadesse-be4ks
    @MekdesTadesse-be4ks 10 วันที่ผ่านมา

    አሜን ተበረኩ ጌታ ይበርካችሁ❤