9ኛ ትምህርት : የዮሐንስ ወንጌል ዋና ዋና ሐሳቦች - የሕይወት ምንጭ

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 6 ก.พ. 2025
  • ለዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚተከሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ዮሐ. 1:4 ዮሐ. 10:10፤ ዮሐ. 1:12፣ 13፤ ዮሐ. 6፡61-68፤ ዘኁ. 13፡23-33፤ ማቴ. 4፡1-4።
    የመታሰቢያ ጥቅስ፡ “እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም” (ዮሐ. 14፡6)።
    በዮሐንስ ወንጌል ውስጥ፣ ኢየሱስ ማን እንደሆነ ሲጠየቅ፣ መለኮትነትን በሚያመላክት ቃል መለሰ። “እኔ ነኝ” የሚለው በሚቃጠለው ቁጥቋጦ ውስጥ ለሙሴ የተገለጠለት ጌታ እራሱ እንደሆነ የማያሻማ ማጣቀሻ ነበር። ሙሴን “እኔ እኔ ነኝ” ብሎ ተናገረ (ዘጸ. 3፡14)። ይህ “እኔ ነኝ” ያለው አምላክ “ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን” (ዮሐ. 1፡14)።
    “እኔ ነኝ” የሚለው ጭብጥ በመላው ዮሐንስ ወንጌል ውስጥ አለ። የዚህ ሳምንት መሪ ጥቅስ ያንን ጭብጥ ያንፀባርቃል፡- “እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ” (ዮሐንስ 14፡ 6)። “እኔ ነኝ” የዓለም ብርሃን፣ የሕይወት እንጀራ፣ በሩ ወይም የበጎች በር፣ መልካም እረኛና እውነተኛው የወይን ግንድ ነው።

ความคิดเห็น • 3