ተሀድሶ | መጋቢ ሙሉጌታ ምትኩ |

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 27 ส.ค. 2024
  • #መጋቢ_ሙሉጌታ_ምትኩ
    #ተሀድሶ
    የመ.ቅ.ክ. ኢሳይያስ 40:27-31
    "ያዕቆብ ሆይ፥ እስራኤልም ሆይ፦ መንገዴ ከእግዚአብሔር ተሰውራለች፥ ፍርዴም ከአምላኬ አልፋለች፡ ለምን ትላለህ? ለምንስ እንዲህ ትናገራለህ?
    አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም።
    ለደካማ ኃይልን ይሰጣል፥ ጕልበት ለሌለውም ብርታትን ይጨምራል። ብላቴኖች ይደክማሉ ይታክቱማል፥ ጐበዛዝቱም ፈጽሞ ይወድቃሉ፤ እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም።"
    ሮሜ.12:1-2
    "እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው።
    የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ"
    - ተሃድሶ ማለት መዋቅራዊ ( Structural) ለውጥ ማድረግ፣ የተሰበረውን፣ ከመስመር ያፈነገጠውን ፣ መልኩ የተጨማደደውን እንደነበር አድርጐ መልሶ መጠገን ወደ ትክክለኛው ሥርዓት መመለስ ማለት ነው ::
    * በአዲስ እና የተለወጠ አመለካከት ካልሆነ በቀር ዛሬ በዘመናችን እግዚአብሔር በምድር ላይ ምን እየሠራ እንዳለ ልናውቅ አንችልም ::
    * ተሃድሶን ሰዎች ሊያመጡ አይችሉም። ጀማሪውም የበላይ ተቆጣጣሪውም ራሱ እግዚአብሔር ነው ።
    - ተሃድሶ( Reformation) እና መነቃቃት (Revival) ልዩነታቸው
    መነቃቃት (Revival) የመንፈሳዊ ህይወት መታደስን እና ከመንፈሳዊ ሞት መንቃትን ያመለክታል።
    ተሐድሶ(Reformation) ማለት እንደገና ማደራጀትን የሃሳቦችን እና የአሠራር ለውጦችን ያመለክታል
    - እግዚአብሔር በቤተክርስቲያናችን የሚያመጠው ተሃድሶ በ3 አቅጣጫዎች ላይ ነው
    1. የፀሎት ተሃድሶ ፦ ተሃድሶ ከሚያስፈልጋቸው የቤተክርስቲያን ዋነኛ ክፍሎች ውስጥ ፀሎት ነው
    ቻድዊክ የሚባል ሰው እንዲህ አለ፡ የሰይጣን አንዱ የስራ ድርሻ አማኞችን ፀሎት መከልከል ነው።
    ማቴ. 6፡5-13
    “ስትጸልዩም እንደ ግብዞች አትሁኑ፤ ለሰው ይታዩ ዘንድ በምኩራብና በመንገድ ማዕዘን ቆመው መጸለይን ይወዳሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል።
    አንተ ግን ስትጸልይ፥ ወደ እልፍኝህ ግባ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።
    አሕዛብም በመናገራቸው ብዛት እንዲሰሙ ይመስላቸዋልና ስትጸልዩ እንደ እነርሱ በከንቱ አትድገሙ።
    ስለዚህ አትምሰሉአቸው፤ ሳትለምኑት አባታችሁ የሚያስፈልጋችሁን ያውቃልና።
    “እንግዲህ እናንተስ እንዲህ ጸልዩ፦ ‘በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፥ ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤ የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን፤ እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል፥ በደላችንን ይቅር በለን፤ ከክፉም አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን፤
    መንግሥት ያንተ ናትና ኃይልም ክብርም ለዘለዓለሙ፤ አሜን።"
    2.የፍቅር ተሃድሶ - የሁል ጊዜ የሕይወት ምልልስ እና በአብዛኛው ግንኙነት (Communication) ላይ የሚያተኩር ነው።
    - ግንኙነት ማለት :- በንግግር መረጃ መለዋወጥ ሲሆን በተለያየ መንገድ ይገለጣል (በአካል ፣ በንባብበ ስልክ፣ በቲቪ )
    1 Corinthians 13 አማ - 1 ቆሮንቶስ 13
    "በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሽዋሽዋ ጸናጽል ሆኜአለሁ።1 Corinthians 13 አማ - 1 ቆሮንቶስ
    ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ።
    ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል፥ ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም።
    ፍቅር ይታገሣል፥ ቸርነትንም ያደርጋል፤ ፍቅር አይቀናም፤ ፍቅር አይመካም፥ አይታበይም፤
    የማይገባውን አያደርግም፥ የራሱንም አይፈልግም፥ አይበሳጭም፥ በደልን አይቆጥርም፤
    ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም፤
    ሁሉን ይታገሣል፥ ሁሉን ያምናል፥ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፥ በሁሉ ይጸናል።
    ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም፤ ትንቢት ቢሆን ግን ይሻራል፤ ልሳኖች ቢሆኑ ይቀራሉ፤ እውቀትም ቢሆን ይሻራል።
    ከእውቀት ከፍለን እናውቃለንና፥ ከትንቢትም ከፍለን እንናገራለንና፤
    ፍጹም የሆነ ሲመጣ ግን ተከፍሎ የነበረው ይሻራል።
    ልጅ ሳለሁ እንደ ልጅ እናገር ነበር፥ እንደ ልጅም አስብ ነበር፥ እንደ ልጅም እቈጥር ነበር፤ ጎልማሳ ሆኜ ግን የልጅነትን ጠባይ ሽሬአለሁ።
    ዛሬስ በመስተዋት በድንግዝግዝ እንደምናይ ነን በዚያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን፤ ዛሬስ ከእውቀት ከፍዬ አውቃለሁ በዚያን ጊዜ ግን እኔ ደግሞ እንደ ታወቅሁ አውቃለሁ።
    እንዲህም ከሆነ፥ እምነት ተስፋ ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ፤ ከእነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው።"
    3. የአምልኮ ተሃድሶ :-
    ዮሐንስ 4፥20-24
    "አባቶቻችን በዚህ ተራራ ሰገዱ፤ እናንተም፦ ‘ሰው ሊሰግድበት የሚገባው ስፍራ በኢየሩሳሌም ነው፡’ ትላላችሁ፡” አለችው። ኢየሱስም እንዲህ አላት፦ “አንቺ ሴት፥ እመኚኝ፥ በዚህ ተራራ ወይም በኢየሩሳሌም ለአብ የማትሰግዱበት ጊዜ ይመጣል። እናንተስ ለማታውቁት ትሰግዳላችሁ፤ እኛ መዳን ከአይሁድ ነውና ለምናውቀው እንሰግዳለን ነገር ግን በእውነት የሚሰግዱ ለአብ በመንፈስና በእውነት የሚሰግዱበት ጊዜ ይመጣል አሁንም ሆኖአል፤ አብ ሊሰግዱለት እንደ እነዚህ ያሉትን ይሻልና፤ እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል።” ፣ ነገር ግን ጊዜው እየመጣ ነው፤ እንዲያውም መጥቶአል፤ የተጠራችሁበት ምንም የማይሆንበትና የምትሰግዱበትም ቦታ ምንም አይሆንም። "በእግዚአብሔር ፊት የሚቆጠረው ማንነታችሁና አኗኗራችሁ ነው። አምልኮታችሁ እውነትን በመከታተል መንፈሳችሁን ማሳተፍ ይኖርበታል። አብ የሚፈልጋቸውን እነዚህን ሰዎች በፊቱ በቅንነት እና በቅንነት በገዛ ፍቃዳቸው የሚያቀርቡትን ነው።"
    - እኛ ቅዱሳን ምን እናድርግ ?
    1 ቆሮንቶስ 16 : 13:
    " ንቁ፥ በሃይማኖት ቁሙ፥ ጎልምሱ ጠንክሩ። በእናንተ ዘንድ ሁሉ በፍቅር ይሁን።"
    1ቆሮ 16፡ 13
    " ንቁ፤ በእምነት ጽኑ፤ በርቱ፤ ጠንክሩ፤ የምታደርጉትን ሁሉ በፍቅር አድርጉ።" ( አዲሱ ትርጉም)
    እግዚአብሔር ይባርካችሁ!

ความคิดเห็น •