በተለመደው ሁኔታ ያልተለመደ ነገር ይሆናል | ቄስ ዶክተር አያሌው ተሰማ |

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 29 ส.ค. 2024
  • የዮሐንስ ወንጌል 5፡ 1-9
    “ ከዚህ በኋላ የአይሁድ በዓል ነበረ፥ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ። በኢየሩሳሌምም በበጎች በር አጠገብ በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ የምትባል አንዲት መጠመቂያ ነበረች፤ አምስትም መመላለሻ ነበረባት። በእነዚህ ውስጥ የውኃውን መንቀሳቀስ እየጠበቁ በሽተኞችና ዕውሮች አንካሶችም ሰውነታቸውም የሰለለ ብዙ ሕዝብ ይተኙ ነበር። አንዳንድ ጊዜ የጌታ መልአክ ወደ መጠመቂያይቱ ወርዶ ውኃውን ያናውጥ ነበርና፤ እንግዲህ ከውኃው መናወጥ በኋላ በመጀመሪያ የገባ ከማናቸው ካለበት ደዌ ጤናማ ይሆን ነበር። በዚያም ከሠላሳ ስምንት ዓመት ጀምሮ የታመመ አንድ ሰው ነበረ፤ ኢየሱስ ይህን ሰው ተኝቶ ባየ ጊዜ፥ እስከ አሁን ብዙ ዘመን እንዲሁ እንደ ነበረ አውቆ፦ ልትድን ትወዳለህን? አለው። ድውዩም፦ ጌታ ሆይ፥ ውኃው በተናወጠ ጊዜ በመጠመቂያይቱ ውስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም ነገር ግን እኔ ስመጣ ሳለሁ ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል ብሎ መለሰለት። ኢየሱስ፦ ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለው። ወዲያውም ሰውዬው ዳነ አልጋውንም ተሸክሞ ሄደ።”
    ኢየሱስ በተለመደ ሁኔታ ውስጥ እጅግ ብዙ ያልተለመደ ነገር አድርጓል
    ዮሐንስ 2
    1 በሦስተኛውም ቀን በገሊላ ቃና ሰርግ ነበረ፥ የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች፤
    11 ኢየሱስ ይህን የምልክቶች መጀመሪያ በገሊላ ቃና አደረገ፤ ክብሩንም ገለጠ፥ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ።
    ዮሐንስ 4
    ⁴ በሰማርያም ሊያልፍ ግድ ሆነበት።
    ⁵ ስለዚህ ያዕቆብ ለልጁ ለዮሴፍ በሰጠው ስፍራ አጠገብ ወደምትሆን ሲካር ወደምትባል የሰማርያ ከተማ መጣ፤
    ²¹ ኢየሱስም እንዲህ አላት፦ አንቺ ሴት፥ እመኚኝ፥ በዚህ ተራራ ወይም በኢየሩሳሌም ለአብ የማትሰግዱበት ጊዜ ይመጣል።
    ²⁴ እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል።
    ዮሐንስ 4
    ⁴⁶ ኢየሱስም ውኃውን የወይን ጠጅ ወዳደረገባት ወደ ገሊላ ቃና ዳግመኛ መጣ። በቅፍርናሆምም ልጁ የታመመበት ከንጉሥ ቤት አንድ ሹም ነበረ።
    ⁵⁰ ኢየሱስም፦ ሂድ፤ ልጅህ በሕይወት አለ አለው። ሰውዬውም ኢየሱስ የነገረውን ቃል አምኖ ሄደ።
    ⁵³ አባቱም ኢየሱስ፦ ልጅህ በሕይወት አለ ባለው በዚያ ሰዓት እንደ ሆነ አወቀ፤ እርሱም ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር አመነ።
    ኢየሱስ በተለመደ ቦታ በቤተሳይዳ በመገኘት ያልተለመደ ነገር አደረገ
    - እንደተለመደው ውሀው በተናወጠ ጊዜ በመጠመቂያዪቱ ውስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለም ሌላውም ይቀድመኛል እያለ በተለመደ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ኢየሱሰ ያልተለመደ ነገር ሊያደርግ መጣለት
    ኢየሱስ ተነሳና ተመላለስ ካለው በሗላ የሆነለት ፦
    1. አዲስ መረዳት / እውቀት/
    2. አዲስ አቅም
    3. አዲስ ምእራፍ
    ኢየሱስ በተለመደ ሁኔታችን ውስጥ ያልተለመደ ነገር ያደርጋል
    እግዚአብሔር ይባርካችሁ

ความคิดเห็น •