“የሐኪም ወርቅነህ እሸቴ ቤት የዓለም አቀፍ ታሪካችን ሙዚዬም ነው”- ሱራፌል ወንድሙ | Hakim Workneh Eshete | Surafel Wondimu

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 12 ก.ย. 2024
  • በአሁኑ ወቅት በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በሚገኘው ግሎባል ስተዲስ ዩኒቨርስቲ፤ በአፍሪካ ጥናት ተቋም መምህር የሆነው ሱራፌል ወንድሙ፤ ከሰሞኑ እንዲፈርሱ ውሳኔ የተላለፈባቸው የሐኪም ወቅርነህ እሸቴ ቤቶች “የዓለም አቀፍ ታሪካችን ሙዚዬም” በመሆናቸው ጉዳዩ በጥሞና ሊታይ እንደሚገባ ያሳስባል።
    ሐኪም ወርቅነህ “በኢትዮጵያ የጸረ ቅኝ ግዛት ትግል ታሪክ ዓለም አቀፋዊ መድረክ ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ ያላቸው” መሆናቸውም የሚጠቅሰው ሱራፌል፤ ጉዳዩን “ከቅርስ ባሻገር የነጻነት ጥያቄ አድርጎ” ማየት እንደሚገባ ያሳስባል። “የሐኪም ወርቅነህ እሸቴ ህይወት የተቋጨባቸው መኖሪያ ቤቶቻቸው፤ የኢትዮጵያን የዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ፣ የአባይ ግድብና የባህር በር ታሪክ፣ የፀረ ባርነትና የፀረ ቅኝ ግዛት ትግልና የትምህርት ማስፋፋት ታሪኮችን አትመው ማቆየት የሚያስችሉ ሙዚዬሞች ሊሆኑ ይገባቸዋል” ሲልም ይከራከራል።
    “ይህ ሰዓት በስብርባሪ ታሪክ ፊት ቆሞ እማኝነት መስጠትን ግድ ይላል። ከዘልማዱ የታሪክ አጻጻፍ በተለየ ሁኔታ፤ ጊዜ አልፎ ሁኔታዎች ‘ታሪክ’ እስኪሆኑ ከመጠበቅ ተላቅቀን፤ ዛሬን ከትላንት ጋር ማስተሳሰር ያሻናል። ታሪክ የትላንት ድርብርብ ጊዜያትና ስፍራዎች እየታመቁባት እንደ እሳተ ገሞራ በየእግራችን ስር በመፈንዳት፤ በእለት ህይወታችን ላይ እየቀለጠች የምትፈስ የዛሬ ጉዳይ ነች” ይላል ሱራፌል።
    በኢትዮጵያ የዘመናዊነት አካሄድ ላይ ጥናት ያደረገው ሱራፌል፤ “ስለ ማህበራዊ፣ ባህላዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እውነት ለመነጋገር” እና “ውሳኔዎችንም በጋራ ያማረ ለማድረግ” ያግዝ ዘንድ በሚል ይህን ዘለግ ያለ ሀተታ አጠናቅሯል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
    ---------------------------------------------------------------------------------------------------------
    የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ትኩስ ዜናዎችን እና ወቅታዊ ዘገባዎችን ለመከታተል፦
    ድረ ገጽ ፦ ethiopiainsider...​
    ፌስቡክ ፦ / ethiopiainsider
    ትዊተር (ኤክስ) ፦ / ethiopiainsider
    ቴሌግራም፦ t.me/EthiopiaI...
    ቲክቶክ፦ / ethiopiainsider

ความคิดเห็น • 65