13ኛ ትምህርት : የማርቆስ መጽሐፍ - የተነሣው ጌታ
ฝัง
- เผยแพร่เมื่อ 6 ก.พ. 2025
- ለዚህ ሳምንት ትምህርት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ:- : ማር. 15:42-47፤ ማር. 16፣ ቆላ. 2:10-12፣ 1 ቆሮ. 15:1-8፣ ዳን. 9:24-27፣ ዮሐ. 20:11-18።
የመታሰቢያ ጥቅስ: “እርሱ ግን፦ አትደንግጡ፤ የተሰቀለውን የናዝሬቱን ኢየሱስን ትፈልጋላችሁ፤ ተነሥቶአል፥ በዚህ የለም፤ እነሆ እርሱን ያኖሩበት ስፍራ” አለ (ማር. 16:6)።
የኢየሱስ መሰቀል ለደቀ መዛሙርቱ እምነትና ተስፋ መሞት ማረጋገጫ ነበር። ይህ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ከጌታቸው መሞት ጋር የታገሉበት ጊዜ ብቻ ሳይሆን ለራሳቸው ሕይወትም እጅግ የፈሩበት ጊዜ ስለነበር ጨለማ የሆነ የሳምንቱ የመጨረሻ ጊዜ ነበር (ዮሐ. 20፡19)። የማርቆስ መጽሐፍ የመጨረሻው ምዕራፍ በሆነው ማርቆስ ምዕራፍ 16 ውስጥ ሞቱን ተከትሎ ስለሆነው ነገር እንመለከታለን።
በመጀመሪያ፣ የኢየሱስ ከሙታን መነሳት ጊዜውን ጠብቆ ስለመሆኑና ሴቶቹ ለምን ወደ መቃብሩ እሁድ ጧት እንደመጡ እንመለከታለን። የእሁድን ቅድስና በሚደግፍ መልኩ በተሳሳተ መልክ ጥቅም ላይ ከመዋሉ የተነሣ አድቬንቲስቶች አንዳንድ ጊዜ የትንሣኤ ማለዳን ይደብቃሉ። እንደ አለመታደል ሆኖ ከዚህ የትንሣኤ ቀን የተነሳ የተሳሳተ የሥነ-መለኮት ትምህርት ቢኖርም እንኳን በእሁድ ትንሣኤ እንዴት መደሰት እንደምንችል እንመለከታለን።
ሁለተኛ፣ ትምህርቱ እነዚህን ቃላት በመላው መጽሐፍ ውስጥ ካለው ዋና ሀሳብ ጋር በማገናኘት የማርቆስ 16ን የመጀመሪያ ቁጥሮች ያብራራል። ሰኞ እና ማክሰኞ ላይ የምናደርጋቸው ጥናቶቻችን እነዚህን ጽንሰ ሀሳቦች ይመለከታሉ።
ሶስተኛ፣ ሳምንቱን ስንዘጋ፣ ረቡዕ እና ሀሙስ የማርቆስ ምዕራፍ 16ን ቀሪ ክፍል በመመርመር በፊታችን የሚያስቀምጠውን ተልዕኮ ይመለከታል።