2ኛ ትምህርት : የዮሐንስ ወንጌል ዋና ዋና ሐሳቦች - የመለኮት ምልክቶች

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 6 ก.พ. 2025
  • ለዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚተከሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ዮሐ. 6፡1-15፣ ኢሳ. 53:4-6፣ 1ኛ ቆሮ. 5:7፣ ዮሐ. 6:26-36፣ ዮሐ. 9:1-41፣ 1ኛ ቆሮ. 1:26-29፣ ዮሐ. 11።
    የመታሰቢያ ጥቅስ፡ “ኢየሱስም፡- ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤ሕያው የሆነም የሚያምንብኝም ሁሉ ለዘላለም አይሞትም፤ ይህን ታምኚያለሽን? አላት” (ዮሐ. 11:25-26)።
    ኢየሱስ ክርስቶስ ከአብ ጋር አንድ የሆነ፣ ከሌላ ያልተገኘና ያልተፈጠረ ዘላለማዊ ልጅ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያስተምራል። የተፈጠረውን ሁሉ የፈጠረው ኢየሱስ ነው (ዮሐ. 1፡1፣ 3)። ስለዚህም ኢየሱስ ሁልጊዜ አለ፤ እርሱ ያልነበረበት ጊዜ አልነበረም። ኢየሱስ ወደዚህ ዓለም መጥቶ ሰብዓዊ ማንነታችንን ቢለብስም፣ መለኮታዊነቱን ጠብቆአል፣ እናም አንዳንድ ጊዜ ኢየሱስ ይህን መለኮታዊነቱን የሚገልጡ ነገሮችን ተናግሮአል፣ አድርጓልም።
    ይህ እውነት ለዮሐንስ አስፈላጊ ነበር፣ ለዚህም ነው፣ ዮሐንስ አንዳንድ የኢየሱስን ተአምራት ሲናገር፣ የክርስቶስን አምላክነት ለማመልከት የተጠቀመባቸው። ኢየሱስ መለኮታዊነቱን የሚገልጡ ነገሮችን ብቻ ሳይሆን የተናገረው ነገር ግን አምላክነቱን በመግለጥ የተናገራቸውን ንግግሮች የሚደግፉ ሥራዎችንም ሰርቷል።

ความคิดเห็น •