በቤት ኪራይ ውድነት የተቸገሩ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ መምህራን፤ በተማሪዎች ዶርም “በጊዜያዊነት” እየኖሩ ነው

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 22 มิ.ย. 2024
  • በትግራይ ክልል በሚገኘው መቐለ ዩኒቨርሲቲ የሚያስተምሩ የተወሰኑ መምህራን “ቤት ተከራይቶ መኖር እንደከበዳቸው” ለተቋሙ ማመልከታቸውን ተከትሎ፤ በተማሪዎች ማደሪያ ዶርም “በጊዜያዊነት” እንዲቆዩ ተፈቅዶላቸው እየኖሩ መሆኑን ገለጹ። የዩኒቨርስቲው መምህራን በክልሉ በነበረው ጦርነት ሳቢያ የ17 ወር ደመወዝ ያልተከፈላቸው መሆኑ፤ በአስር ሺህዎች የሚቆጠር ውዝፍ የቤት ኪራይ እንዲከማችባችው አድርጓል።
    በ1992 ዓ.ም በወጣ ደንብ የተቋቋመው መቐለ ዩኒቨርሲቲ፤ በአሁኑ ወቅት ከስምንት ሺህ በላይ ሰራተኞች ያሉት ሲሆን ከእነርሱ ውስጥ ሁለት ሺህ ገደማ የሚሆኑት መምህራን መሆናቸውን ከተቋሙ የተገኘው መረጃ ያመለክታል። በዩኒቨርሲቲው ስር ባሉት ሰባት ካምፓሶች ከሚያስተምሩት ከእነዚህ መምህራን ውስጥ አብዛኞቹ በግል ቤት ተከራይተው የሚኖሩ ናቸው።
    የዩኒቨርሲቲው መምህራን “የቤት ኪራይ መክፈል አቅቶናል” የሚሉ ማመልከቻዎችን ለተቋሙ ማስገባት የጀመሩት ከ2014 ዓ.ም. ጀምሮ ቢሆንም፤ ካለፈው ሶስት ወር ወዲህ ግን በርካታ መምህራን ተመሳሳይ ጥያቄዎች ለተቋሙ ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንት ቢሮ ማቅረባቸው ተነግሯል። መምህራኑ ለዩኒቨርሲቲው ጥያቄ እንዲያቀርቡ የተገደዱት፤ በጦርነት ወቅት ሳይከፍሉ የቀሩትን “ውዝፍ የቤት ኪራይ” አሁን እንዲያመጡ እየተጠየቁ በመሆኑ እና በክልሉ ባለው የኑሮ ውድነት ምክንያት መሆኑን “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ያነጋገረቻቸው መምህራን ያስረዳሉ። (ኢትዮጲያ ኢንሳይደር)
    ተጨማሪውን ለማንበብ ይሄን ሊንክ ይጫኑ ethiopiainside...
    -------------------------------------------------------------------------------------------
    የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ትኩስ ዜናዎችን እና ወቅታዊ ዘገባዎችን ለመከታተል፦
    ድረ ገጽ ፦ ethiopiainsider...​
    ፌስቡክ ፦ / ethiopiainsider
    ትዊተር (ኤክስ) ፦ / ethiopiainsider
    ቴሌግራም፦ t.me/EthiopiaI...
    ቲክቶክ፦ / ethiopiainsider

ความคิดเห็น •