አዲስ አየር ማረፊያ ከሚገነባበት በቢሾፍቱ አቅራቢያ ከሚገኝ ቦታ፤ 2,500 አባወራዎች እንደሚነሱ ተገለጸ |ethiopiaairline |ethiopiainsider

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 11 ก.ย. 2024
  • የኢትዮጵያ አየር መንገድ በስድስት ቢሊዮን ዶላር አዲስ አየር ማረፊያ ከሚያስገነባበት ቦታ፤ 2,500 አባወራዎች እንደሚነሱ ዋና ስራ አስፈጻሚው አቶ መስፍን ጣሰው ተናገሩ። አየር መንገዱ ተነሺዎችን በሚያሰፍርበት ምትክ ቦታ ላይ፤ የመኖሪያ ቤት እና ለነዋሪዎቹ የሚያስፈልጓቸው “ፋሲሊቲዎች” እንደሚገነቡላቸውም ገልጸዋል።
    አቶ መስፍን ይህን የገለጹት፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢሾፍቱ ከተማ አቅራቢያ አዲስ የሚያስገነባውን የአየር ማረፊያ ንድፍ ለማሰራት፤ መቀመጫውን በዱባይ ካደረገ አማካሪ ኩባንያ ጋር ስምምነት በተፈራረመበት ወቅት ነው። ስምምነቱን ዛሬ አርብ ነሐሴ 3፤ 2016 በአዲስ አበባው ስካይ ላይት ሆቴል የተፈራረሙት፤ የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን እና የዳር አል-ሃንዳሳህ ኩባንያ የኦፕሬሽን ዳይሬክተር ታሪቅ ናጂ አል-ቃኒ ናቸው።
    ዳር አል-ሃንዳሳህ የተሰኘው ኩባንያ፤ በአሁኑ ወቅት በኦሮሚያ ክልል በመገንባት ላይ ለሚገኘው የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የማማከር ስራ በማከናወን ላይ የሚገኝ ነው። የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቱ ግንባታው ሲጠናቀቅ 100 ሜጋዋት ኃይል የማመንጨት አቅም ይኖረዋል።
    (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
    ተጨማሪውን ለማንበብ ይሄን ሊንክ ይጫኑ ethiopiainside...
    -------------------------------------------------------------------------------------------
    የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ትኩስ ዜናዎችን እና ወቅታዊ ዘገባዎችን ለመከታተል፦
    ድረ ገጽ ፦ ethiopiainsider...​
    ፌስቡክ ፦ / ethiopiainsider
    ትዊተር (ኤክስ) ፦ / ethiopiainsider
    ቴሌግራም፦ t.me/EthiopiaI...
    ቲክቶክ፦ / ethiopiainsider

ความคิดเห็น • 1