የበዓሉ ግርማ አሟሟት ላይ የተደረገ ውይይት ክፍል 3 Endalegeta Kebede about Bealu Girma

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 26 พ.ย. 2024
  • Ethiopia: የበዓሉ ግርማ አሟሟት ላይ የተደረገ ውይይት ክፍል 3
    የደራሲ በዓሉ ግርማ ህይወት፣ ስራዎች እና አሟሟት ላይ ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ የሰጠው አስተያየት
    መጽሐፉን እንዴት እንደጻፈው፣ በበዓሉ አሟሟት ላይ እጃቸው አለበት ስለሚባሉ ሰዎች እና ሌሎችም
    Endalegeta Kebede about Bealu Girma
    Subscribe for more videos | Ethiopia

ความคิดเห็น • 13

  • @seyfudada9641
    @seyfudada9641 2 ปีที่แล้ว +2

    ድንቅ ነው መፅሀፋ! እንዳለ ጌታ ትልቅ ስራ ነው የሰራው ሀበሻ አመሉ ነው ድሮም ዳር ተገትሮ ይጠብቅና ሰው የሰራውን መተቸት!!!

  • @ethiocomment1707
    @ethiocomment1707 2 ปีที่แล้ว +2

    20:40 እንዴት መጽሐፋን ሳያነቡ ይህን ፕሮግራም ለማዘጋጀት ይስባሉ?
    አበራ ለማ ምንም ይበል ምን ፣ እንደ ጠያቂ እንዳለ የጻፈውን መጽሐፍ አንብባችሁ ማመሳከር እና መጠየቅ ነው እንጂ ....

  • @hailemeko5928
    @hailemeko5928 3 ปีที่แล้ว +2

    ወይይታችሁ ተመለከትኩት ግን አወያዮቹ መጽሐፍቱን በደንብ ሳታነቡ የሌላ መርህ እያነሳችሁ መከረከር አጥጋቢ አይደለም፡፡ ክርክሩ መሆን የነበረበት አንብባችሁ ገጽ ጠቅሳችሁ ፣ ይህንን ማስረጃ ከየት አመጣከው መባል ሲገባ መንም ያልጻፈውን ደራሲ አበራ ለማ እንዲህ አለ ብሎ መከራከር የሚያረካ አይደለም ፣ አበራ ለማ ብቸኛው ተጠያቂ ያደረገው ማነው? የኃይለመለኮት አግዘው ክርክር ሳይሆን ትምህርት ልታስተምረን መሞከር ማወቅክን ብቻ ልትነግረን የፈለክ ነው የሚመስለው በቃለ መጠየቅ ሥነሥርዓት ውስጥ የሚደገፍ አይደለም፡፡ ድራሲው እሱ በደረሰበት በሰበሰበው መረጃ የደረስኩበት መደምደሚያ ይህ ነው ካለ መብቱ አይደለም ወይ!!! ኃይለመለኮት መሞገት ያለብክ ማስረጃ አምጥተክ በእገሌ ጽሁፍ፣ ማስረጃ እንደዚህ አይደለም ማለት ሲገባ የአበራ አስተያየት ላይ ነው የተመረኮዝኩት ብሎ መጠየቅ ማቅረብ ተገቢነት የለውም፡፡ ማናችንም ብንሆን እውነት ፍለጋ እንጂ የማንም ደጋፊ እንዳልሆንን የሚያነብ ሰው የሚያውቀው ሀሳብ ነው፡፡ የአበራ ኢሹ…….. 433 ገጽ ላይ መነጋገር አንችልም ይባላል እሱ ሲጽፍ አልከበደው፣ 433 ገጽ ላይ መነጋገር ካልተቻለ ከ ገጽ ----- እስከ ገጽ ድረስ እንወያየለን ማለት ይቻላል፣ ባላነበብከው መጽሐፍ ላይ በድፍረት ለውይይት መቀመጥ እራሱ ድረፍረት ነው፡፡ ሌላው ስለ በዓሉ ግርማ አሞሞት ካላፈ ስንት ጊዜው ነው ህግ እራሱን የቻለ የይርጋ ጊዜ አለው አሁን ገዳይ ቢገኘ የህግ ውጤት የለውም፣ እስከ ዛሬ እነርሱ ስላላነሱት በተለያየ የት/ት ዘርፍ ሊነሳ አይቻልም ተብሎ መሞገት አንተ እራስክ ከተማርከው የታሪክ ት/ት አንጻር የሚጋጭ ነው፡፡ የአንድ ሰው ታሪክ በተለያየ ዘርፍ ሊጠና እንደሚችል ማወቅ ከአንድ ባለሙያ የሚጠበቅ ትንሹ እውቀት ነው፡፡ ግን እነዚህ ባለመረዳትክ አዝኛለው፡፡ የእኔ ምልከታ ደራሲው ለምን ተሞገተ አይደለም የማያነብብ ወይም ያላነበበ ሰው መሞገት የለበትም፡፡ እንደ ጆሮ ጠገብ ጋዜጠኛ አንድ ሰው ያለውን ሐሳብ በማስረጃ ሳያነጥሩ የአበራ ሀሳብ በየትኞቹ መጽሀፍት፣ ጽሁፍ፣ ወይም በዘመኑ የነበሩ ሰዎች እንደሚደገፉ ሳይገልጽ እንዳለጌታ የሚያቀርባቸውን ሀሳቦችን የሚደግፉትን ማስረጃ እየጠቀሰ ሳለ…….… አይ አይደለም ብሎ ሙግት ማቅረብ ፣ አወያይ መሆን የማይገባ ተግባር ነው፡፡ ለሌላው ጊዜ መጽሐፍቱን አንብባችሁ ማስረጃ ይዛችሁ ስትሞግቱት ማየት እናፍቃለው፡፡

  • @kumelachewamare3787
    @kumelachewamare3787 6 ปีที่แล้ว

    You have to read the book when you suggestion

  • @bobjaha4623
    @bobjaha4623 6 ปีที่แล้ว

    ያመለጠን ነገር ማለት ነው

  • @yerusalemokube4352
    @yerusalemokube4352 2 ปีที่แล้ว

    ENANTE AWEYAYOCH GAZETNGOCH SERACHU YEMIREBA AYDELEM
    ENDALE GETA GROUM SERTOTAL
    ENANTE AWEYAYOCH BALEGEWOCH BEHULETUM KERANE LEMEFETER NEW
    HEWEKET LEMEFETER NEW YETENESACHU BALEGEWOCH NACHU
    ENDALEGETA BEALU MAN ENDEGEDELEW FENTEW ARGO
    ASZYTONAL

  • @zewduayele624
    @zewduayele624 2 ปีที่แล้ว

    Great discussion. You look as if you were in heaven and talking in free spirits. First appreciate Endale Geta for his tiresome efforts to materialize discovering the facts.
    Who killed him? Likely answer is found.
    But where was he buried? Help Endalegeta to reach on the final body placement let us erect him some memorial statue ( tangible and intangible).
    Yet it is clear that as we adhore Bealu Girma, there are a bunch of people who hate him. So the killing team are: his friends, Dergu, Generals, TPLF and EPLF. All have got the brutal intentions to erase Bealu Girma. They did it this way or that way. Unfortunately we are on the same time/mindset zones where we were 40 years ago ( Yekatit 1970 EC).
    In terms of ignorance and cruelty all systems in Ethiopia ( HIM=Dergu=EPRDF/TPLF =EPP) are the same. Same boqollo.

  • @divoraolive722
    @divoraolive722 6 ปีที่แล้ว

    Botawn gelexekew benor yanie tru neber lemn segah tawkleh yemiketatelwn sew wey ligdlut endemiefelgu tadya mn asefah!

  • @bobjaha4623
    @bobjaha4623 6 ปีที่แล้ว

    እሮማይ ማለት ኣመለጠ ነገር ማለት ነው

  • @woldemariambekele4085
    @woldemariambekele4085 6 ปีที่แล้ว

    Endale are u defending Mulugeta Lule or are you trying to find out caused him to get killed?i used to respect endale but you seem by defending Mulugeta Lule and others u don't deserve respect. You are money chaser

  • @hezahegntadesse2285
    @hezahegntadesse2285 6 ปีที่แล้ว

    "በጅብ ቆዳ የተለበጠን ከበሮ ቢደልቁት እንብላው... ነው ዜማው"
    ወዳጄ እንዳለ ጌታ ከበደ እንደምን አለህ? በ"አሀዱ" ሬድዮ ፕሮግራም ላየር ያዋልከውን ቃለ ምልልስ አደመጥኩ ከመናገር ባሻገር የልብህ አልደርስ ብሎ ይሆን በስውር ስምህ አጮልቀህ የመጣህበት መንገድ ቢያስገርመኝ ዘንዳ የግሌን አስተያየት ለመስጠት ተገድጃለሁ
    የብዕር ስምህን ለበጎ ነገር ብታውለው ምን ነበረበት!? ፌዘኛ ነህ! በስውር ስምህ ምናልባትም አንተ የብዕር ስሜ በምትለው ቅጥያ (ገዛኸኝ) የለጠፍከውን ጽሁፍ ተመልክቼዋለሁ አንብቤዋለሁም በድምጥህ ከተረክልን የሀሰት ተረክ ሌላ አንድም ያደገ ጉዳይ ይዘህ እንዳልመጣህ ልነግርህ እፈልጋለሁ።
    የአንደበትህን ግልባጭ ማንም በማይከለለክልህ ገጥ ላይ ሞንጭረህልናል ብዙ አትድከም ወዳጄ እንዳለጌታ "ገዛኸኝም አንተ አንተም ገዛኸኝ ነህ! " ነቅተናል።
    ጥሩ ጥሩ መጽሀፎች ጥፈህ ይሁን ዘርፈህ አስነብበኸናል ይበልም ብለን መርቀናል። ኩፈሳህ ግን በሰራኸው ሥራ ልክ ያልተሰፋ እየሆነ መምጣቱን ልጠቁምህ ወደድኩኩ...
    እንዲህ እንዳተ በለስ ቀንቶአቸው ስራዎቻቸውን ለተደራሲያን ለማድረስ ብርሀን የጨለመባቸው የምርጥ ስራዎች ባለቤት የሆኑ ወጣቶች በርካታ እንደሆኑ ታውቀው ይሆን? በነዚህ ወጣቶች ሥም የአዕምሮ ዝርፊያ መፈጸምህን ማን ይንገርህ? ይሄንን ጉድህን እንዳንተ ያለ ጋጠወጥ መሆን ቢያስችለን ኖሮ አየር ላይ ባዋልነውና ሰው በፈረደን፤ እባክህ ያልሆነ ጉዳይ ውስጥ እየገባህ አታቁስለን ሚናህ ከማንም የማይበልጥ እንደነበረ ላንዴም አስበህ አታውቅም!? አንተ የግልህ ቤት እስኪመስል እንደፈለክበት የተንቧቸህበት "የደራሲያን ማህበር" ስራ አስፈጻሚ ስለነበርክ ያሉትን አማራጮች ሁሉ ተጠቅመህ ለዚህ መድረስህ ትዝ ይሏል?
    ወዳጄ እንዳለጌታ ከበደ ዘርፈህ ለዚህ ያደረሰህን ቤት ማን እንዳደረጀው እንኳ ለማሰብ እንደማትፈልግ በሰጠኸው ቃለ ምልልስ ላይ ደጋግመህ አወሳህ በራስህ አንደበት ትዝብት ውስጥ ወድቀኻል፤ ድፍረትህ ብቻ ሳይሆን የገረመን ከአንድ ታዋቂ ሆኛለሁ ደራሲ ነኝ ከሚል ሰብ አይጠበቅም! የዘለፍካቸው በህይወት ያሉትን ደራሲዎችን ብቻም አይደለም በህይወት የሌሉትንም ስታነሳ ሰማን "ሙት ወቃሽ!" ብለንሀል፤ ማፈሪያ ነህ ደበበ ሰይፉ ባንተ ወለፈንዲ ምላስ የሚጠራም አልነበረም ስለራስህ እንኳን ባግባቡ መግለጥ የማትችል ሰው ነበርክ "ግዜ የሰጠው...." ሆኖ ነው ጉዳዩ ለሰጠኸው ቃለ ምልልስ ዘመናትን እፈርበት! ልቦና ይስጥህ ብለንም ተማጥነናል!
    በነገራችን ላይ ከሰጠኸው ቃለ ምልልስ ተነስቼ አንዳንድ ሀሳቦችን ላንሳልህ "በዓሉ ግርማና ስራዎቹ" የተሰኘው መጽሀፍህ ተጠርዞ ለህዝብ እንዲደርስ ደራሲ አበራ ለማ የነበረውን ሚና አውርደህም ቢሆን ተገደህ ለመጠቆም ሞክረሀል፤ ታድያ "መረጃዎችን ከማደርጀት አንጻር መጽሀፉ ላይ የተጠቀሱት ሰዎች ስለአሉ ግርማ አሟሟት የገለጹበት መንገድ ሰፊ ክፍተት ነበረበት እንዲህ አይነቱ ስራ መረጃዎቹ ሙሉዕ ሊሆኑ ይገባል" ስለተባልክ ታላቅ ባለውለታዬ ነበር መጽሀፌን በሀሳቦች አደርጅቶልኛል ያልከውን ሰው እንደተርብ ለመንደፍ ስትንጠራራ ምን ለማለት እንደፈለክ እንኳን ለመረዳት ተስኗል
    ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ እኔ በግሌ አደንቅሀለው በቅልጥፍናህ ማለቴ ነው...ከሰወች ጋር ተለጥፈህ የፈለከውን ከወሰድክ በኋላ ሰውየውን ለማግለል የምትከውነው ጉዳይ መች ዛሬ ብቻ ሆነና ፊቱንም እንዲህ ነህ! እኛ ስለምንተዋወቅ "ፓራሳይት" ብለንሀል! ተደጋፊ የመሆንህ ጉዳይ አልደነቀንም ወትሮም በራስህ ቆመህ አይተን አናውቅም ስለግብርህ እንድነግርህ ከፈለክ ደግሞ እነሆ... ወደሰዎች ከገባህ በኋላ ማደሪያህን እስክታደላድል ጨዋ መስለክ ያሻህን ታደርግና እግርህን ዘርግተህ መዝናናት ስትጀምር ያስጠጋህን፣ ለእውቅናህ ህልውና የሆነውን ሰው ገዝግዘህ ገዝግዘህ ለመጣል ግዜ አይወስድብህም ወደኋላ ተመልሰህ ውለታን የማስተዋል ቅንጣት ነገር አይፈጥርብህም ከዚህ በላይም ብታወራ ወርደህ እንጅ ከፍ ብለህ አይተን አናውቅም
    ላንተ ቤትህ በሆነው እንደፈለክ በወርሀዊ መዋጮ ክፍያ ሀገር ላገር እየዞርክ ታላላቆችህን ቁልቁል እያየህ እንድትዘባነን ባስቻለህ ቤትህ እድሜ "ለ ደራሲያን መሀበር" ይሄ ስፍራ በርግጥም ሆስትህ ነበር በየወሩ ባዋጣንልህ ብር እዚህ መድረስህን ልታስተውል ይቅርና ቤቱንም ሰርተው ያቆሙልህን ሰዎች ስታንቋሽሽ አታፍርም! "ከኋላ ከሌለ የለም የፊቱ" ነበር ያለው ያ ብላቴናው ዘፋኝ...
    እናም በርዕሴ ላይ እንዳስቀመጥኩት "በጅብ ቆዳ የተለበጠ ከበሮ ሲደልቁት እንብላው ...ይላል" ሆኖብኛል ጉዳይህ ደራሲ እና ጋዜጠኛ አበራ ለማ በሰጠው ቃለ ምልልስ ወደ ስቱድዮ ገብተህ በግድ "ሰውየውን ልዝለፍና ልውጣ?" አይነት አካሄድ ተጠቅመህ የሰራኸው ጥፋት በስነ ምግባርም ብቻም ሳይሆን በወንጀልም ያስጠይቅህ ነበር ስለምትናገረው የተምታታ ሀሳብ አስተውለህ ከሆነ ብዙ ያልካቸው ጉዳዮች የተጣረሱ ናቸው በህይወት የሌሉትን አንጋፋ ደራሲዎቻችንን በመረጃ አልባ ጉዳይ የውሸት ቅኝት ለማስጨበጥ የጣርክበት መንገድ አጀብ ያስብላል፤
    "ማን ያውራ የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ" ነውና ጉዳዩ ለሰፈርከው አሉባልታና ዝልፊያ ምላሽ ባይሰጥህ ኖሮ ስንቱን ጉድ ተርትረኸዋል፤ አስተዋይ ከሆንክ በደራሲ አበራ ለማ ከተሰጠህ ምላሽ ብዙ ልትማር ይገባል።
    ደራሲ አበራ ለማ የበአሉን ግምደ ታሪክ ለህዝብ ይፋ እንድታደርግ እንዳገዘህ ራስህም ነግረኸናል አንተ የጻፍክበት መንገድ "እንዲህ ቢሆን ኖሮ" ብሎ ማለት የዝህን ያክል ጩኸት እንደሚያስጮህ ባየሁ ግዜ ወትሮም ውስጥህ መልካም እንዳልነበር ተረዳሁ ደራሲውን በማመስገን ተራ ለምን ስሜ ተነሳ ብሎ ዘራፍ ማለት ስብዕናን ያሳጣል።
    እናም ወዳጄ እንዳለጌታ ከበደ (ገዛኸኝ) ይሄን እላይህ ላይ የተወጠረውን የዥብ ቆዳ ከልተህ ብትችል በከብት ቆዳ የተወጠረ ከበሮ ሁንና ቢያንስ ሲደልቁህ ቃና ያለው ዜማ ለማሰማት ሞክር! አጉል ያልሆነ ስም ሰወች ላይ ለጥፎ ሌሎች እንዲጠሉዋቸው የማድረግ ሴራህን አውልቀህ ጣል!
    ግንቦት 18-2010 ዓ/ም
    @@ግዜ ለኩሉ ነኝ@@

    • @bejainnerash
      @bejainnerash 4 ปีที่แล้ว +1

      Make it short and precise, lets grab your idea first