Sheger Cafe - Abdu Ali Higera With Meaza Birru በወንጀል ተግባር የተገኘ ገንዘብን የማስመለስ ረቂቅ አዋጅ ላይ !

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 4 พ.ย. 2024

ความคิดเห็น •

  • @tkh4049
    @tkh4049 4 หลายเดือนก่อน +1

    Exactly! He explained the situation correctly and helpful for the people and the government.

  • @Man-y2k
    @Man-y2k 4 หลายเดือนก่อน +30

    መዓዛ የብልጽግና ወንጀሎችን እየሸፈንሽ እስከመቼ ?

  • @eskenderlessanu66
    @eskenderlessanu66 4 หลายเดือนก่อน +37

    አብዱ በመንግስት ፈንታ ህዝቡን መውቀሱ እና በሰው ቁስል ጨው ነስንስበት አካሄድ በጣም አስገርሞኛል።ይሄንን ሚዛናዊነት ለማለት ይከብደኛል።

    • @elaaes
      @elaaes 4 หลายเดือนก่อน +3

      ወሬ ዝም በል

    • @JimmaaJimmaa-hf1mq
      @JimmaaJimmaa-hf1mq 4 หลายเดือนก่อน +1

      አረዳድ ይለህል

    • @tegenesisay8543
      @tegenesisay8543 4 หลายเดือนก่อน +1

      ጓድ አብዱ ሙያዊ ትንተና ስለሆነ የሰጠው... ወቀሳውም እንዲሁ ሙያዊ ሆኖ ነው መቅረብ ያለበት.. ጀሮህ መስማት የፈለገውን ስላልነገረህ ዝም ብለው ማናተቡ ተገቢ አይደለም

  • @info7034
    @info7034 4 หลายเดือนก่อน +3

    Thank you!!!

  • @semenawihabesha8283
    @semenawihabesha8283 4 หลายเดือนก่อน +7

    Ay sheger. Aleklaki

  • @solomonmichael1582
    @solomonmichael1582 4 หลายเดือนก่อน +1

    Best program with informative discussion.

  • @asegidabayneh7350
    @asegidabayneh7350 4 หลายเดือนก่อน +1

    እናመሰግናለን

  • @tinsaebelete958
    @tinsaebelete958 4 หลายเดือนก่อน +7

    ጥርት ብሎ ያልቀረበና ያላስረዳ የተላዘዘ ውይይት አነዚህ ብልጽግና ናቸው አንዴ???

  • @dejenegetahun629
    @dejenegetahun629 4 หลายเดือนก่อน +3

    አይ መዓዛ እና አብዱ ነገረስራችሁ ሁሉ ብልፅግናናን መከላከል መሰለ። ደህና ሰዉ ....

  • @HABESHAINSIDER
    @HABESHAINSIDER 4 หลายเดือนก่อน +5

    የራሱን የቻለ lecture ነው ፣ ምርጥ ጋዜጠኛ መሀል ፣ respect

  • @mohammedahmed6727
    @mohammedahmed6727 4 หลายเดือนก่อน +3

    በጣም እናመሰግናለን , ጓድ አብዱ

    • @mulugetaseleshi7422
      @mulugetaseleshi7422 4 หลายเดือนก่อน

      ጛድ ? ስትል ሠማሁህ ልበል !

  • @Weyni-lm1hv
    @Weyni-lm1hv 3 หลายเดือนก่อน

    ❤የወንጀለኞች ሚድያ ነው ብልፅግና ይወገዳል እንስንተ ወደ ቃሊቲ በቅርቡ 100%❤

  • @tadesselegese4236
    @tadesselegese4236 4 หลายเดือนก่อน +4

    ከገለልተኛ ወገን ህጋዊ ማብራሪያ እንዲሰጥበት ማድረግ ማህበረሰቡ ተገቢ ግንዛቤ እንዲያገኝ ማድረጉ እውነተኛ እና ነፃ የህዝብ ሚዲያ ተግባር መሆኑን በዚህ በሚቀርቡ የተለያዩ ዘገባዎች ብዙ ግንዛቤ እያገኘን ነው።

  • @GebreHerego
    @GebreHerego 4 หลายเดือนก่อน

    Wonderful analysis !!!
    Thank you !!!

  • @DanDan-ti6ds
    @DanDan-ti6ds 4 หลายเดือนก่อน

    Thank you Mr Abdu l know 🙏 him very well when he comes to Methara sugar factory as a Gust

  • @tesfayeshume2450
    @tesfayeshume2450 3 หลายเดือนก่อน

    I love you maze

  • @Unknown85948
    @Unknown85948 4 หลายเดือนก่อน +2

    የህግ ባለሙያ አይደለሁም ግን በ Common Sense,
    መንግስት ወታደሮቹን ተጠቅሞ ሚሊየኖችን እየገደለ ለ አለም አቀፉ ማግበረሰብ ስለ ሰባዊ መብት አያያዝ RIPORT አደርጋለሁ ብሎ ያላፈረ፣
    ለዚ ለዚ ሲሆን ማሰቡ አስገራሚ ነው።
    ግልጽ ነው ህዝብ የመንግስትን ሙስና የትም ሄዶ መክሰስም ማስመለስም አይችልም። ማህበረሰብ ሁሌም ተጎጂ ነው።
    የማህበረሰቡ የ ሃብት ምንጭ ይጠየቃል እንጂ የ ድህነት ምንጭ ማንም አይጠይቅም!
    እድሜው የገፋ ሰው በሚዛናዊነት ቢያስብ መልካም ነበር። At least ጸጥ ቢል!

  • @muluteffera6754
    @muluteffera6754 4 หลายเดือนก่อน

    I was asking where is Abdu Ali please give short explanation about every day to day rule.

  • @WesenAlemu-pj6jt
    @WesenAlemu-pj6jt 4 หลายเดือนก่อน +1

    የዚህ ፕሮግራም ስህተት ከርዕሱ ይጀምራል። ረቂቁን ትቶ የሕግ አወጣጥ ላይ ነው ያተኮረው። ትንታኔውም ላይ ከተጠቀሰው ረቂቅ ይልቅ ሌሎች ሕጎች ናቸው የተብራሩበት። ትኩረቱ የሕግ አወጣጥ ከሆነ እና ሌሎች ሕጎች ላይ የምታተኩሩ ከሆነ ይህን ረቂቅ የርዕሱ አካል ማድረግ ለምን አስፈለገ? እንደምትተቹት የሚጮህ ርዕስ አይነት ለመፍጠር ነውን?
    አብዱ በትንታኔህ ጥፋተኛ ያደረግኸው ሕዝቡን ነው። ሕዝቡ ስለሚወጡ ሕጎች መቼ አውቆ ነው እንዲቃወም የምትጠይቀው? እንኳን ተራው ሕዝብ የሕግ ባለሙያው እንኳን ረቂቅን ቀርቶ የወጣ ሕግን እንኳን ለማግኘት ፍዳ በሚያይበት ሀገር ለምን ረቂቅን አልተቻችሁም ብለህ ትወቅሳለህ? ከተቸህም መተቸት ያለብህ የሕግ ባለሙያን ነው እንጂ እንዴት ሕዝቡን በጠቅላላ ትወቅሳለህ? ደግሞስ ከማኅበራዊ ሚዲያ ውጪ መጮሂያ ልሳን በተነፈገበት ሕዝቡን ምን አድርጉ ነው የምትለው? አህያውን ፈርቶ ዳውላውን ይሉታል ይህ ነው።
    መንግሥት የወቅቱን ፖለቲካ ታሳቢ ማድረግ ነበረበት የሚል ጉዳይ አንስተሀል። በነካ እጅህ ሕጉ አንዱን ሕዝብ ከሌላው በላይ ኢላማ አድርጓል ወይስ አላደረገም የሚለውን መጠየቅ ለምን አልፈለግህም? የወንጀል ሕጉ የጠሉትን ለማንገላታትና ለማጥፋት፣ የወደዱትን ለማበልጸግ ጥቅም ላይ እየዋለ መሆኑ ለምን አላሳሰበህም? ትላልቅ ሙስናዎች ሳይሆኑ ትናንሾቹ ሙስናዎችን ነው መታገል ያለባችሁ የሚል መመሪያ ከባለስልጣናት ሲሰጥ ኧረ በሕግ ያላልከው ለምንድን ነው? ሕግ ሁሉም ላይ የማይፈጸም ከሆነና አንድን ሰው ወይም ቡድን ለማጥቃት ከወጣ የሕገመንግሥቱን አንቀጽ 25 እንደሚቃረን ጠፍቶህ ነውን? ሁሉንም ችግር ማንሳት ነበረብህ ከሚል ሳይሆን የሀገሪቱ ቁልፍ ችግር ቡድነኝነት የተጠናወተው በመሆኑ ነው ይህንን ትችት ማቅረቤ።
    ጭራሽ ከዚህ በፊት የነበሩ ስህተቶች ናቸውና የተፈጸሙት አሁን መቃወማችሁ ስህተት ነው የሚመስል ወቀሳ አዝንበሀል። ከዚህ በፊት የነበረ ስህተትን መድገምን እንደትክክል አድርገህ ማቅረብ አያስተዛዝብም?
    ሕጉ ከበፊቶቹ መቼ ይለይና የሚልም ሀሳብ የምታነሳ ይመስላል። ይመስላል የምለው ሀተታህ በሙሉ superficialነት ስለሚያጠቃውና ግልጽ ባለ መልኩ ስለማትናገር ነው። ረቂቁ ግን ከዚህ በፊት ከነበሩት ሕግጋት እጅግ በጣም ቁልፍ በሆኑ ጉዳዮች የተለየ ነው። የረቂቁ ትልቁ አጨቃጫቂ ጉዳይ ሁሉም ሰው ደረሰኝ መያዝ ነበረበት የሚል ግዴታ መጣሉ ነው። ባለፉት 10 አመታት ለተገኘው ገቢ ደረሰኝ ወይም ሌላ ማስረጃ ካላመጣችሁ በቀር ገንዘቡ በሕገወጥ መንገድ የተገኘ ነው ማለት ንብረታችሁን አምጡ ከማለት በምን ይለያል? በወቅቱ ያልተያዘ ደረሰኝ ወይም ሌላ ማስረጃ አሁን ከየት እንዲመጣ አስቦ ነው ሕጉ የወጣው። ይህ ድንጋጌስ ከቀደሙት ሕግጋት የትኛው ጋር ነበር? አዋጅ ቁጥር 780/2005ን መሠረት አድርጎ ሀብትን ለመውረስ አመንጪ ወንጀሉ መረጋገጥ አለበት። የአሁኑ ሕግ ግን ወንጀሉ ባይረጋገጥም ሀብቱ የሚወረስበትን ሥርዐት ዘርግቷል። ወንጀል ሳይረጋገጥ ሀብትን መውረስ ኡኡ ቢያስብል ምን ይደንቅሀል? ምንጩ ያልታወቀ ሀብት ባለቤት መሆን ተጠያቂ ያደርግ የነበረው የመንግሥት ወይም የሕዝብ ድርጅት ሠራተኛን ነበር። አዲሱ ረቂቅ ግን በየትኛውም ሰው ላይ ተፈፃሚ የሚሆን ነው። ይህ ሁሉ ሕዝብን ቢያንጫጫ ምን ያስደምምሀል?

    • @tegenesisay8543
      @tegenesisay8543 4 หลายเดือนก่อน

      ምንጩን ማረጋገጥ! is, I think, the key wordings... ማለትም ይኸን "ምንጩን ማረጋገጥ" ሁናቴ "ለህጋዊነት" ግዴታ አድርጎ የሚቆጥረው በስራ ላይ ያለው ህግ ... በሌላኛው ገፅታ "ምንጩን አለማረጋገጥ" ወይንም የሀቡቱ "ምንጩ አለመታወቁን" ህገ ወጥ ቢያደርግ (by implication) ለምን ስህተት ይሆናል? ... or else, if this new law is considered "Curative" to the existing?

    • @WesenAlemu-pj6jt
      @WesenAlemu-pj6jt 3 หลายเดือนก่อน

      @@tegenesisay8543 መጀመሪያ ወንጀል በimplication አይፈጠርም። አንድ ድርጊት በወንጀል ለማስቀጣት ክልከላው ቀጥተኛ መሆን አለበት እንጂ በimplication ወንጀልን ማቋቋም አይቻልም። 2ኛ ከዚህ ሕግ በፊት ሀብትህ በሕጋዊ መንገድ የተገኘ መሆኑን የማረጋገጥ ግዴታ የለብህም። ያ ግዴታ የነበረው ሌላ ወንጀል መፈጸምህ ከተረጋገጠ ብቻ ነበር። ይህኛው ሕግ እኮ literally እያለ ያለው ይሄን ሕግ እንደማወጣ ከ10 አመት በፊት በጥንቆላም ሆነ በትንቢት ማወቅ ነበረብህ ነው። ምክንያቱም ወደኋላ 10 አመት ተመልሼ ደረሰኝ ካላመጣህ ንብረትህን እወርሳለሁ እያለ ነው። በስጦታም ብታገኘው፣ ለምነህም ብታገኘው ያን ማስረዳት እስካልቻልክ ድረስ ንብረቱ ይወረሳል እያለ ነው። እርግጥ በዚህ ወቅት ይህ ሕግ ኖረም አልኖረም ለውጥ የለውም እኔ የታዘብኩት እነአብዱን ነው እንጂ። ሕጉ ባይኖርም ቢኖርም የድሀ ጌጣጌጥ ሳይቀር በውድቅት ለሊት በፖሊስ እየተዘረፈ ባለበት ሀገር ሕግ ቅንጦት ነው። አብዱ ግን የማይሆን የሕግ ትንታኔ ለመስጠት ሲውተረተር ብታዘብ ነው ኮመንቴን ማስቀመጤ።

  • @kenfeab
    @kenfeab 4 หลายเดือนก่อน

    aye guwad Abdu!! when you talk law it feels like you are narriating a bed time story.Kudos to you,sir.

  • @ahmed-em8nt
    @ahmed-em8nt 4 หลายเดือนก่อน +1

    አብዱ አሁን አሳተወስኩት በደርግ የመጨረሻ አመታት አካባቢ በሬዲዮ ስለ ህግ ይትነትን ነበር ።

    • @lulsegedtamene7495
      @lulsegedtamene7495 4 หลายเดือนก่อน +1

      😊😊

    • @AlMi-kl4cl
      @AlMi-kl4cl 4 หลายเดือนก่อน

      አሁን ዋና ባንዳ ሆኗል

  • @AlMi-kl4cl
    @AlMi-kl4cl 4 หลายเดือนก่อน +6

    አብዱና መአዛ ዋና የዚህ አገዛዝ አለቅላቂዎች ናቸው።

    • @abdulkerimjemal7855
      @abdulkerimjemal7855 4 หลายเดือนก่อน

      ሀቀኛ እነ ባለ እወቀት ናቸው ደደብ ስለሆንከ አፍህን ከፈትክሳ

    • @AlMi-kl4cl
      @AlMi-kl4cl 4 หลายเดือนก่อน

      @@abdulkerimjemal7855 አንተ ቆሻሻ በንጹሃን ደም ቀላጅ ባንዳ እደግምልሃሁ ባንዳዎች ናቸው።

  • @alemlemessa3869
    @alemlemessa3869 4 หลายเดือนก่อน +2

    በዚህ አዋጅ ወስጥ ወንጀል የሚባል ነገር የለም ለምን ለውይይቱ ይሄን ርእስ ሰጣችሁት? አብዱም አጭርና ግልፅ በሆነ መንገድ ሃሳብህን ለመግለፅ ሞክር ::

  • @tamiratbefikadu4542
    @tamiratbefikadu4542 3 หลายเดือนก่อน

    ሰላም ሸገሮች እባካችሁ እኔም ገንዘብ ተወስዶብኝ ማስመለስ አልቻልኩም ብትረዱኝ ማስረጃወች አሉኝ

  • @Solomonletta
    @Solomonletta 4 หลายเดือนก่อน +1

    አቶ አብዱ አሊ ሕግ የተማረ ብቻ ሳይሆን ሕግን የበላ ሰው ነው ሲተነትን እያዋዛ ነው ::ወ/ሮ ማአዛ ይህ ሰው ድካም ሳይጫጫነው በፊት confuse የሚያረጉ የሃገራቺን ሕጎችን አስተንትኝልን ::

  • @eliaskiflemariam8422
    @eliaskiflemariam8422 4 หลายเดือนก่อน

    ማብራሪያው ትምህርታዊ ነው።ስለ ንብረት ማስመለስ ግን ሲወራ ርዕሱ ቀድሞ የተዘረፈ ወይም የተቀማ ንብረትን የማስመለስ ሂደት ይመስላል። 10 አመት ወደ ኋላ ሄዶ መተገበር አለበት ወይ ለሚለው ግን ማብራሪያ ቢሰጥበት?

  • @Furgosefer
    @Furgosefer 4 หลายเดือนก่อน

    እንዴት ሰነበትሽ መዓዚ

  • @WesenAlemu-pj6jt
    @WesenAlemu-pj6jt 4 หลายเดือนก่อน

    ባለፈው 1 አመት የሰማኋቸው ከአብዱ ጋር የሚደረጉ ውይይቶች በሙሉ ዋናውን ጉዳይ (Crust of the matter) ከመዳሰስ ይልቅ ላይ ላዩን የሚነካኩ ናቸው። ሌላው የዝግጅቶቹ መለያ የብልጽግናን ከባድ ወንጀሎች ከማንሳት መቆጠብና ድርጊቶቹን መሸፋፈናቸው ነው። መአዛ አልፎ አልፎም ቢሆን የቻልሽውን ያህል ለመጠየቅ እንደምትሞክሪ ብመለከትም አብዱ ግን ዋናውን ጉዳይ ትተህ ብልጽግናን በማይወቅስ መልኩ ነው ስታነሳ የኖርከው። እውቀት ብቻውን ዋጋ የለውም አብዱ። እውቀትህን ለሀገር መድሀኒት ለመሥራት ካልተጠቀምክበት ጥቅም የለውም። ቀድሞውኑ መንግሥት ከሕግ በላይ በሆነበት ስለሕግ መወያየት በራሱ እርባና ቢስ ነው። መንግሥትን የሚደግፍ ሰልፍ እየተፈቀደ ብቻ ሳይሆን እስፖንሰር እየተደረገ መንግሥትን የሚቃወም ሰልፍ ግን አዋሽ 40 ሲያስወረውር የሕግ የበላይነት አፈር ድሜ ጋጠ ማለት ነው። ይህን ስታዩ መንግሥት ከሕግ በላይ ስለሆነ ሕዝቡ መብቱን በሕግ ማስከበር ካልቻለ በጉልበቱ ያስከብር ብላችሁ መወትወት የነበረባችሁ እናንተ ናችሁ። ለዚህ የምትፈሩ ከሆነ ደግሞ ቢያንስ ብልጽግናን ከሚደግፉ ነገሮች መቆጠብ ነበረባችሁ። ሕዝብ እናንተን ቢሰማ ኖሮ እኮ ህልውናውን ለማስጠበቅ ከገባበት ትግል በቦዘነ ነበር።
    አማራዎች በየመንገዱ ታግተው በሚሊየን ሲጠየቁ እና ሲታረዱ ምን የሕግ መፍትሄ አቀረባችሁ? ዘወትር ታላዝኑበት በነበረው የሚዲያ ነጻነት ጉዳይ ጋዜጠኞች በገፍ ዘብጥያ ሲወረወሩ ፊት ለፊት መንግሥትን መውቀስ ለምን ተሳናችሁ? አሳዬ ደርቤ ለምን እውነትን ተናገርክ ተብሎ የ9 አመት እስር ሲበየንበት ስላልሰማችሁ ነው ወይስ ጊዜ ስታገኙ ልታነሱት አቅዳችሁ ነው ያላነሳችሁት? አብይ አህመድ አስመራጭም ተመራጭም በሆነበት ሕገወጥ የፓርቲ ምርጫ ላይ ምን አላችሁ? የፓርቲው ምርጫ ሕገወጥ ከሆነ ፓርቲው መታገድ ነበረበትና ምርጫውም ላይ መሳተፍ አይችልም ነበር። በዚህ ጉዳይ ምን አላችሁ? በለጠ ሞላ ስልጣኔን አለቅም ሲል ምርጫ ቦርድ ትእዛዙ ባለመፈጸሙ ምን አይነት እርምጃ መውሰድ አለበት ብላችሁ ተወያይታችኋል? ህውሀት በመቶ ሺዎቹ ታጣቂዎችና ከባድ መሳሪያዎችን እንደያዘ፣ ወረራውንም እንደቀጠለ ሕጋዊ ይሁን የሚል ጥያቄ ሲቀርብ ሀገር ይያዝ የማትሉት ለምንድን ነው? ጥቂት ግለሰቦችን ወይም አንድ ቡድን በሕግ ያጣውን ፍላጎቱን ሌላ ሕግ በማውጣት እንዲያሳካ ማድረግ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን ይግባኝ ሰሚ ማድረግ ሆኖ እንደምን ሳይታያችሁ ቀረ? እንዲህ አይነት መንግሥትን እና ዘር አጥፊዎችን እርቃናቸውን እንዲቀሩ የሚያደርጉ ጉዳዮችንማ ባላየ ታልፋላችሁ። ታዲያ ኧረ በሕግ የምትሉት ሕዝብን ብቻ መሆኑ ነው? በሕዝብ ላይማ ማን ይሰንፋል?
    ሌላው የዝግጅቶቻችሁ ወጥ ባህሪያት ለአገዛዙ ሀጢያቶች ሕዝብን እና ተቃዋሚዎችን መወንጀላቸው ነው። የአማራ ልዩ ሀይል ሲፈርስ ልዩ ሀይል ሕገመንግሥታዊ ስላለመሆኑ ስንጮህ ነበር ብላችሁ የአማራ ልዩ ሀይል መፍረስን ሕጋዊነት ስታንባርቁብን ነበር። ዋናው ጉዳይ ግን ልዩ ሀይል ሕገመንግሥታዊ ነው ወይስ አይደለም አልነበረም። የአማራ ልዩ ሀይል ፈርሶ ሌላው ልዩ ሀይል አለመፍረሱ ሕጋዊ ነው ወይ ነበር ጉዳዩ። ህውሀት በመቶ ሺዎቹ ጦር ባዘጋጀበት የአማራ ልዩ ሀይል መፍረሱ ሕጋዊ ነው ወይ ነበር ጥያቄው? መንግሥት የሕዝብን ደህንነት ማስጠበቅ ባልቻለበትና አማራ በያለበት በሚታረድበት የአማራ ልዩ ሀይል መፍረሱ ሕጋዊ ነው ወይ ብቻ ሳይሆን የዘር ማጥፋትን ወንጀል የሚያስፈጽም አይደለም ወይ ነበር ጥያቄው። በመንግሥት መግለጫ በግልጽ የኦሮሚያ ልዩ ሀይል ቀስ ብሎ ይፈርሳል እየተባለ የአማራ ልዩ ሀይልን ማፍረሱ በ2 ሕዝብ መሀል ያለውን እኩልነት ገደል የሚሰድ አይደለም ወይ የሚል ነበር። ሁሉም ሰው በሕግ ፊት እኩል ነው የሚለው ቡድኖችንም አይመለከትም ወይ የሚል ነበር። የአማራ ክልል በምክር ቤቱ ሕግ አውጥቶ ያቋቋመውን ልዩ ሀይል ራሱ ምክር ቤቱ ያፈርሳል እንጂ ለሕጎቼ ተገዛልኝ ብሎ ያቋቋመው አስፈጻሚ ያፈርሳል ወይ ነበር ጉዳዩ። ሕገመንግሥቱን የሚጻረር ሕግ ቢወጣ እንኳን አስፈጻሚው ከምክር ቤቱ ጋር ይከራከራል እንጂ ራሱ በማናለብኝነት ያፈርሳል ወይ ነበር ነጥቡ። ሁሉም የጸጥታ ተቋማት በኦሮሞዎች በተሞሉበት የአማራ ሕዝብ ህልውናውን የሚያስጠብቅለት ልዩ ሀይልን ማፍረሱ ከተፈጥሮ ሕግ (natural law) ጋር አይጋጭም ወይ ነበር ሙግቱ። ልዩ ሀይልን ማፍረስ የራሱን ውይይት እና ሂደት አይፈልግም ወይ ነበር ክርክሩ። በአደባባይ ማርከህ ታጠቅ የተባለ ሰው ትጥቅህን አምጣ ሲባል ወንጀል አይደለም ወይ ነበር የእምቢተኝነቱ ማጠንጠኛ። ህይወቱን አስይዞ የማረከውን ትጥቅ አትወስድም ማለት ህይወትህን በነጻ ልሰዋ ማለት አይደለም ወይ ነበር ብስጭቱ። ይህ ሁሉ እያለ የብልጽግናን እርምጃ ሕጋዊ ለማስመሰል ስለ ልዩ ሀይል ኢሕገመንግሥታዊነት ስታትቱ ቆይታችሁ ነበር።
    በጥቅሉ አድር ባዮች ከመሆን ወጥታችሁ ፊት ለፊት ተጋፈጡ። መጋፈጥ ካቃታችሁ ደግሞ መሀል ሰፋሪ ሆናችሁ መንግሥትን በስሱ ሕዝብን ደግሞ በሀይል አትውቀሱ። መንግሥት የሚለካው በጥቅሉ እንጂ በአንዲት ነጠላ ጉዳይ አይደለም። ሕዝቡን መኖሪያ አሳጥቶ ሲያበቃ መኖሪያ ያለውን ደግሞ በሌላው ሀገር የንብረት ታክስ ስላለ ለኔም አይቅርብኝ ቢል ጉዳዩን መመዘን ያለባችሁ ከሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ አንጻር እንጂ ከሌሎች ሀገራት አንጻር መሆን አይኖርበትም። እባካችሁ አድር ባይ አትሁኑ!

  • @kumatariku6352
    @kumatariku6352 4 หลายเดือนก่อน

    ህጉ መውጣቱ ሳይሆን የተወሰኑ ሰዎችን መርጦ ለፖለቲካ ጠቀሜታ እንዳይጠቀሙበት ነው ለምን ቢባል እያየን ነው በህግ ሽፍን ሰዎች እየተገላቱ ነው።

  • @Japy-dj6uq
    @Japy-dj6uq 4 หลายเดือนก่อน

    ♥️🙏💫

  • @hailutadesse3386
    @hailutadesse3386 3 หลายเดือนก่อน

    ኧረ አብዱ
    ኧረ በሕግ! በል
    ሒጅራ Higera ተብሎልሃል 😮

  • @mekuriagize7514
    @mekuriagize7514 4 หลายเดือนก่อน

    አቤዱል
    ንብረት ማስመለስ ክስ ስትመሰርት ባለ ንብረት መሆንህን መረጃ ማቅረብ የለብህም? እኔ ንብረቴ መሆኑን የሚያሳይ ካርታ አለኝ። በምን ሂሳብ ሰው ያለመረጃ ንብረቴ ነው ሊለኝ ይችላል? ለመንግሥትም ቢሆን አመንክዮው ይሠራል።

  • @selamfenta1883
    @selamfenta1883 4 หลายเดือนก่อน +1

    Turiii Nafa Mengestat mejemeria zegochu beselam wetew endigebu yadreg ....keza kerasw guada bemusena & seltan bemetekem ke Hezb guroro neteko yemizerfew Baleseltan tebeyewecu ga yejemer

  • @bisratzewdie9081
    @bisratzewdie9081 4 หลายเดือนก่อน

    ጠዋት አዳምጨዋለው 10qu

  • @MegersaBulcha
    @MegersaBulcha 4 หลายเดือนก่อน +1

    ሸገር F.M 102.1 እወዳችኋለሁ ።

  • @legantegkidan8989
    @legantegkidan8989 4 หลายเดือนก่อน

    ከባለስልጢኖቹ ዘርፈው ካካበቱት ንብረት ማስመለስ አለበት።

  • @Iamexalted
    @Iamexalted 4 หลายเดือนก่อน

    የህዝቡ የድህነት እና የሞት ምንጭ ማን እንደሆነ ይጣራ እና ለህግ ይቅረብ !!!!!!!
    ህግ እኮ technical word (Jargon) ማብዛት አይደለም። Common Senseም ጭምር ነው።
    ሰው እንዴት አርጅቶም እስከ እለተ ሞቱ ለሚዛናዊነት ለመቆም አይቻለውም?

  • @MohamedIsmaiel-c5e
    @MohamedIsmaiel-c5e 4 หลายเดือนก่อน +1

    More.like.share.shager.kafe.

  • @marukebede4433
    @marukebede4433 4 หลายเดือนก่อน

    የአማራን ሃብት ለመዝረፍ ፣አማራን ቤቱን ሁሉ ቀምቶ በረንዳ አዳሪ ለማድረግ የታሰበ የዘረፋ ህግ ነው ።

  • @Simon_45470
    @Simon_45470 4 หลายเดือนก่อน

    ጋሽ አሊ እንወድሀለን!!!

    • @lanteTV1
      @lanteTV1 4 หลายเดือนก่อน +1

      ጋሽ አሊ አይባልም!
      ጓድ አሊ ነው የሚባለው።
      አመሰግናለሁ ጓድ Simon 🫡

    • @Simon_45470
      @Simon_45470 4 หลายเดือนก่อน

      @@lanteTV1 thanks for the correction!!
      it’s coz I love him I said ጋሽ

  • @addisketema5742
    @addisketema5742 4 หลายเดือนก่อน

    ኧረ እባካችሁ፣ ብልፅግና ስንት የምናከብራቸውን የአገር ሃብት የሆኑ ምሁራንን ያሳጣን አንሶ እኛምአስተዋፅዎ አናድርግ። በሃሳባቸውና በሚሰጡት አስተያየት ላንስማማ ብንችል እንኳ የቀሩንን ጥቂት የዕውቀትና የሙያ ሰዎቻችንን ጨርሰን እንዳናጣ ከማይገባ አስተያየት መቆጠብ የሚሻል ይመስለኛል። ስህተት እንኳን ቢኖር ነገ አገር ሠላም ሲሆን መወቃቀስ ይቻላል። ለመአዛና ጋሽ አብዱ ትልቅ ከበሬታ ነው ያለኝ።

  • @fisehaadamseged4208
    @fisehaadamseged4208 4 หลายเดือนก่อน

    አብዱ ዝም ብሎ ይቀባዥራል
    to the point የሚባል ነገር አለ
    ጥያቄው ህጉ ከአላማው ውጭ ዜጎችን በአመለካከታቸው ፣በማንነታቸው ማጥቂያ መሳሪያ እንዳይሆን ምን ይደረግ ነው

  • @retasa7652
    @retasa7652 4 หลายเดือนก่อน

    Ethiopian weshetamnetawan kalakomechi sekaywan tabezalchi betamm Ayn yawta weshet weshet weshet kelay eske tachi eskemeche yhe dirama 😢😢😢😢

  • @Man-y2k
    @Man-y2k 4 หลายเดือนก่อน +2

    የህዝብ ሮሮ እንጉርጉሮ ወይም አቧራ ነው ላንቺ ልክ ነሽ ካንቺ ቤተሰብ የተነካ የለም አብዶ የተባለ እብድ በሱ ልሳን እየተናገርሽ ያልሽው አንቺ ነሽ ብዙ ታግሰንሻል ሁሌ ብልጽግናን ወንጀሎች በመሸፋፈን ላይ ነው የተጠመድሽው የብልጽግናን የውብድና አዋጆችን ጀስቲፋይ ለማድረግ ብዙ ተጉዘሻል

    • @addisabebaethiopia9103
      @addisabebaethiopia9103 4 หลายเดือนก่อน

      ሁለቱም ኦሮሞ መሆናቸውን አትርሱ ግም ለግም አይደል የሚባለው ።

  • @fisehaadamseged4208
    @fisehaadamseged4208 4 หลายเดือนก่อน

    ጥያቄው ህጉ ከአላማው ውጭ ዜጎችን በህግ ሽፋን የማጥቂያ መሳሪያ እንዳይሆን ምን ይደረግ ነው
    ወይስ እናንተም ተከፋይ የመንግስት ፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ሆናችሁ

  • @AbayGorj
    @AbayGorj 4 หลายเดือนก่อน +2

    ይህ ሰዉ በደርግ ግዜ የህግ ማብራሪያ ይሰጥ የነበረው ጉድ አብዱ ነዉ ልበል/?

    • @shemseseid3791
      @shemseseid3791 4 หลายเดือนก่อน +1

      ደርግ የትኛው የFM ጣብያ ነው

    • @ahmed-em8nt
      @ahmed-em8nt 4 หลายเดือนก่อน

      ልክ ነህ እኔም አሁን አሳታወስኩት ከድምጹ የተነሳ ።

  • @Weynfekede051
    @Weynfekede051 4 หลายเดือนก่อน

    Shegeroch esti indew yihen hid titachu beyemesriyabetu yetenserafawun musina guday ansuna teweyayu. Mengist yihin yetenserafa musina ayawuqim wey? Be meret astedader, Mebrat hail, gebiwoch, wereda, denb askebari, menged transport ina lelochim mesriya betoch betam yemizegenin musina wenjel yifetsemal ina silesu bizu mawrat tichlalachu. Ye newariwun hiwot yakebedew mengist yemiyawetaw hig bicha sayhon yalagbab yemiteyeqew deresegn yelelew gubo ina musina naw. Hulum Ethiopiawi betigatu ina be sira tiratu yemiyawqew Wulina masreja inkuan zare zare be musina wenjel tezefkewal. Ina ibakachu ye tiwlid halafinetachun tewetu. Ye muya sinemigbarachu bemiyazew meseret ye hizbun dimts asemu.

  • @binizmelekot2911
    @binizmelekot2911 4 หลายเดือนก่อน +1

    እቺ ሴትዮ በወያኔ ግዜ በአይን አውጣ የምታደርቀንን ሚሚ ስብሃቱን እየመሰለች መጣች ዘንድርስ::

  • @kassahunabite
    @kassahunabite 4 หลายเดือนก่อน

    ይሄን ህግ መፍራትና መቃወም ያለበት ሰርቆ ያሃፈተመ ብቻ ነው አጀንዳ ማስቀየር አይቻልም

  • @dagnachewoda5794
    @dagnachewoda5794 4 หลายเดือนก่อน

    ሰው ባንዳ ካልሆነ እውነትን ከተናገረ ባንዳ ነው መቼ ነው ወደ ቀልባችሁ የምትመለሱት መአዛም ሆነች አብዱ ጠንካራ ኢትዮጵያዊ ሀገር ወዳድ ናቸው የግብፅ ተላላኪ አይደሉም በርቱ ባንዳ ሆን ብለው ነው

  • @Goshu-uo9iw
    @Goshu-uo9iw 4 หลายเดือนก่อน

    ጥሩ ግምገማ

  • @thomasger982
    @thomasger982 4 หลายเดือนก่อน

    አቶ አብዱ አሊ እንደ ዘመኑ ምሁራን በጣም ወርዶብኛል።ለቀድሞ ስርአት ለመተቸት የነበረህ ሞራል አሁን የለህም

  • @melateaddis2112
    @melateaddis2112 4 หลายเดือนก่อน

    ጎድ አብዶ ናቸው እንዴ?

  • @AbdJemal
    @AbdJemal 4 หลายเดือนก่อน

    ለመሆኑ እናንተ ባልፈው 10 አመት ላፈራችሁት ንብረት ደረሰኝ አላችሁ?
    .
    ደረሰኝ ባይኖረንም ህጉ እኛ ላይ ተፈጻሚ አይሆንም ነው እሳቤያችሁ

  • @samuelbizu7180
    @samuelbizu7180 4 หลายเดือนก่อน

    አጸፈጻሚ አካሉ መሰለኝ 2 መቶ ሚሊዮን ብር ጎቦ የጠየቀው ምንም መሽፋፈን አያስፈልግም ህግን የማያክብረው ማን ነው

  • @ድሬ
    @ድሬ 4 หลายเดือนก่อน

    እይ ብቃት ጋሽ እብዱእናመስግናልን

  • @Weyni-lm1hv
    @Weyni-lm1hv 4 หลายเดือนก่อน

    ❤*#ህግ ፦ ከወጣበት ቀን ለቀጣይ ይሰራል ወደሀላ ተመልሶ አይሰራም በየትም አለም አይሰራም ገጥ ወጥ የዝርፍያ የፖሎቲካ ሴራ ነው❤

  • @Only-true-
    @Only-true- 4 หลายเดือนก่อน

    አቤት ሌቦች የ ኢትዮጲያን ገንዘብ እና ሀብት ሲሰርቁ የኖሩ ዛሬ ተጨነቁ 😂😂😂😂😂😂😂😂😂 አትስረቅ ብሎ ያዘዘ ፈጣሪ አምላክ ያጋልጣቸው !!!!

  • @KassaTedla-r7n
    @KassaTedla-r7n 4 หลายเดือนก่อน

    እስከ አሁን አንድ የሚጨበጥ አልተናገረም። Verbose

  • @ninigetaneh2634
    @ninigetaneh2634 4 หลายเดือนก่อน

    አርእስቱ ራሱ ዘግናኝ ነዉ😂

  • @sebqiya5131
    @sebqiya5131 4 หลายเดือนก่อน

    ስንት ቢከፍላችሁ ነው ይሄ ሁሉ አይኔን ግምባር ያድርገው???? በስተርጅና የውርደት ያለህ አላችሁሳ!

  • @HayliDingle
    @HayliDingle 4 หลายเดือนก่อน

    weak or simple logic
    በያነ እንደዚህ ሲደረግ ኣልደነገጥን ኣውሁንም መደነገጥ የለብንም የሚል ትንተና።

  • @InnocentChefHat-kb8kk
    @InnocentChefHat-kb8kk 4 หลายเดือนก่อน

    ለምን አቧራ ያስነሳል? በፊትም ተለፍቶበት ያልተገኘ ሀብት ነዉ። አቧራዉን የሚያስነሱት ሌቦቹ ናቸዉ።

  • @ተስፋዬ-ቀ7ጠ
    @ተስፋዬ-ቀ7ጠ 4 หลายเดือนก่อน

    ዘብዛባ

  • @Adi-p7b
    @Adi-p7b 4 หลายเดือนก่อน

    Aqatari media

  • @yalabe9432
    @yalabe9432 4 หลายเดือนก่อน

    ይህ ሰውየ ድምፁም ሀሳቡም አያምርም ። ሌላ የህግ ባለሙያ እና የኢኮኖሚ ባለሙያ ብትጋብዥ የተሻለ ነው ።

    • @agazborga5225
      @agazborga5225 4 หลายเดือนก่อน

      Beka...erso..yakirbu😅

    • @agazborga5225
      @agazborga5225 4 หลายเดือนก่อน

      Kubet😅😅

  • @danielgebremariam
    @danielgebremariam 4 หลายเดือนก่อน

    Corruption ፊት.

  • @legantegkidan8989
    @legantegkidan8989 4 หลายเดือนก่อน

    ልፍደዳ!!! 😂😂😂

  • @yeromshiferaw1640
    @yeromshiferaw1640 4 หลายเดือนก่อน

    ሰው የልፋቱን ብቻ ነው ማግኘት ያለበት የሚንጫጫው ሌባ ነው ይበለው::

  • @eriyotalemayehu3603
    @eriyotalemayehu3603 4 หลายเดือนก่อน

    😅😂😂😂😂

  • @gethanezewde4992
    @gethanezewde4992 4 หลายเดือนก่อน

    Òoq¹

  • @kassahunabite
    @kassahunabite 4 หลายเดือนก่อน

    ይሄን ህግ መፍራትና መቃወም ያለበት ሰርቆ ያሃፈተመ ብቻ ነው አጀንዳ ማስቀየር አይቻልም

  • @kassahunabite
    @kassahunabite 4 หลายเดือนก่อน

    ይሄን ህግ መፍራትና መቃወም ያለበት ሰርቆ ያሃፈተመ ብቻ ነው አጀንዳ ማስቀየር አይቻልም

  • @kassahunabite
    @kassahunabite 4 หลายเดือนก่อน

    ይሄን ህግ መፍራትና መቃወም ያለበት ሰርቆ ያሃፈተመ ብቻ ነው አጀንዳ ማስቀየር አይቻልም