ไม่สามารถเล่นวิดีโอนี้
ขออภัยในความไม่สะดวก

“ማናቸውም አይነት ተጽእኖ ደርሶብን አያውቅም፤ ቢደርስብንም አንቀበልም” - ዶ/ር ዳንኤል በቀለ

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 18 ส.ค. 2024
  • የሰብአዊ መብት ተቋማት ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች ወይም አጋር ሀገራት ገንዘብ ማሰባሰባቸው፤ “ነጻነታቸውን የሚቃረን” ተደርጎ መወሰድ እንደሌለበት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ተናገሩ። እርሳቸው የሚመሩት ተቋም ከአለም አቀፍ አጋር ድርጅቶች ገንዘብ ቢያሰባስብም፤ “ማናቸውም አይነት ተጽእኖ” ደርሶበት እንደማያውቅም ገልጸዋል።
    የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ይህን ያሉት፤ የሰብአዊ መብት ተቋማትን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በትላንትናው ዕለት ለሰነዘሩት ትችት በሰጡት ምላሽ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ትላንት ሐሙስ ሰኔ 27፤ 2016 በተካሄደ የፓርላማ ስብሰባ ላይ የሰብአዊ መብት ተቋማትን እና አሰራራቸውን “መፈተሽ” እንደሚያስፈልግ ተናግረው ነበር።
    ዛሬ አርብ ሰኔ 28፤ 2016 በኢሰመኮ ዋና መስሪያ ቤት በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ፤ በሰብአዊ መብት ተቋማት ላይ ያነጣጠረው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ትችት በጋዜጠኞች ተነስቶ ነበር። ይህን መሰሉ ትችት “በመንግስት በጀት የማይተዳደሩ” የሰብአዊ መብት ተቋማት ላይ “ብዙ ጊዜ ይቀርባል” ያሉት ዶ/ር ዳንኤል፤ ጉዳዩ በሌሎች ሀገራትምም “የተለመደ እና በተደጋጋሚ የሚሰማ” እንደሆነ አመልክተዋል።
    እንደ ኢሰመኮ ሁሉ ሌሎችም የሰብአዊ መብት ተቋማት “ሃብት ማሰባሰባቸው በራሱ ስህተት አይደለም” ሲሉ ዶ/ር ዳንኤል በዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል። “የተወሰኑ መንግስታዊ ድርጅቶች ብቻ ሳይሆኑ መንግስትም፣ ከአለም አቀፍ አጋር ድርጅቶች ሀብት ያሰባስባል። ስለዚህ ከአለም አቀፍ ድርጅቶች ወይም አጋር ሀገራት፤ ሀብት እና ገንዘብ ማሰባሰብ በራሱ የተቋምን ነጻነት የሚቃረን ነገር አይደለም” ሲሉ ዋና ኮሚሽነሩ አክለዋል።
    🔴 ይህን ሊንክ ተጭነው ethiopiainside... ዝርዝር ዘገባውን በጹሁፍ ያንበቡ።
    --------------------------------------------------------------------------------------------
    የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ትኩስ ዜናዎችን እና ወቅታዊ ዘገባዎችን ለመከታተል፦
    ድረ ገጽ ፦ ethiopiainsider...​
    ፌስቡክ ፦ / ethiopiainsider
    ትዊተር (ኤክስ) ፦ / ethiopiainsider
    ቴሌግራም፦ t.me/EthiopiaI...
    ቲክቶክ፦ / ethiopiainsider

ความคิดเห็น • 5

  • @ethiopianism22
    @ethiopianism22 หลายเดือนก่อน

    Great man of strength really did his success target with innocent Ethiopian without frustration of armed mafias alongside his daily responsible duties

  • @user-dg2hy5hf1e
    @user-dg2hy5hf1e หลายเดือนก่อน

    እውነትክ ነው? the slave abiy before the agreement of pretoria

  • @hitghitg8747
    @hitghitg8747 หลายเดือนก่อน

    ዘረኛ ነህ በእናትህ፣ ጡጦ የሚገባ ልጅ እንኳን እኮ የመንግሥትን ጣልቃ ይረዳል

  • @eyobdemoz7832
    @eyobdemoz7832 หลายเดือนก่อน

    ይህ አባይ አጭበርባሪ ደግሞ ሰዉ ነዉ ብለህ ታወራለህ።