ከአለማዊ ሕይወት እስከ ረጅም አመት ገዳም ሙልኩስና ኑሮ የዲያቢሎስ ፈተና

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 18 ก.ย. 2024
  • " በላዬ በመተባበር ጠላቶቼ ሁሉ ይሾካሾኩብኛል፥ በእኔ ላይም ክፋትን ያስባሉ።" (መዝሙረ ዳዊት 41፥7) አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ወደ ሕሊናቸው በጽሞና በሚያዳምጡበት ጊዜ፤ ከውስጥ በኩል ግራ የሚያጋባ ብዙ ሰው ጭንቅላታቸው ውስጥ እንደሚያወራ አይነት ሹክሹክታ ይሰማሉ፡፡ በተለያየ የስምሪት አሰላለፍና የጥፋት አሠራር የተሰየሙ አጥፊ መንፈሶች አንድ ላይ በመሆን ከውስጥ በኩል የሚያሰሙት የሕሊና ትርምስ ድምፅ የአዙሪት ሹክሹክታ ይበላል፡፡
    የአዙሪት ሹክሹክታ፤ የራስ የአእምሮ ድምፅ የሚመስል ከውስጥ በኩል ከእኛ ወደ እኛ የሚደርስ መልእክት ሲሆን፤ ልንሄድበት ካሰብነው መንገድ ወይም መድረሻ ላይ መሰናክል በመሆን አሳብን አዙሮ በማስለወጥ፤ ወዳላሰብነው አቅጣጫ በዝግታ አሊያም በፍጥነት የአካሄድ ጉዞን የማስለወጥ የመናፍስት አሠራር ነው፡፡
    በዚህም የተለያየ መንገድ እና የጉዞ መስመርን የጀመሩ የተለያዩ መንፈሶች፤ እርስ በእርስና ከተዋረሱት ግለሰብ ጋር በሚጋጩበት ጊዜ፤ ሰውየው በአንድ ጊዜ የብዙ ስሜቶች መግለጫ የሆነ የግጭት ማዕበል ከውስጡ የሚያናውጠው ሰው በመሆን፤ በአመልም፣ በጠባይም፣ በአስተሳሰብም፣ በምግባርም፣ በእቅድም ቶሎ ቶሎ የሚለዋወጥ ይሆንና ወጥ የሆነ የአኗኗር ጎዳና የሌለው፤ ሁሉንም ቦታ በአንዴ የሚረግጥ ነገር ግን በአንዱም ሥፍራ ላይ የማይረጋ ተቅበዥባዥ ፍጡር ይሆናል፡፡
    መናፍስት እርስ በእርስ ሲጋጩ እና እርስ በእርስ የሚጣሉ መናፍስት ከዳፈጡበት ግለሰብ ጋር ሲጋጩ፤ ትልቁ ልዩነት ምንድነው፤ እርስ በእርስ የሚቃረኑ መንፈሶች ከሰውየው ጋር ሲፋለሙ፤ ሰውየው በልቦናው የሚያውቀው በውስጡ የሚፈጠር የተለያዩ አሳቦች፣ ስሜቶችና ባሕሪያት ግጭት ይስተናገዳል፡፡ መናፍስቱ ብቻ እርስ በእርስ የሚጋጩ ከሆነ፤ ሰውየው በልቦናው የውስጡን መዘበራረቅ ሳያውቀው እንዲሁ ከውጪ ባለው ገጽታ ላይ ብቻ የባሕሪይ መነዋወጥ፣ የአመል መለዋወጥ፣ የስሜት መተራመስ፣ የአስተሳሰብ መዋዠቅ፣ የእቅድ መዛባትና መነሻ መሠረቱ ያልተለየ ጭንቀት ይስተናገድበታል፡፡
    Subscribe, Share, Like, Comment እያደረጋችሁ ላልሰሙት አሰሙ ላልነቁ አንቁ! መንፈሳዊነት ይብለጥ! የማዳመጥ ጊዜ ላይ ነን!!!

ความคิดเห็น • 248