Ye Qirqos Lije

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 11 ก.พ. 2025
  • ወንድማችን፡ ፀጋየ፡ ኃይለ ሚካኤል፡ በታኅሣሥ ወር ፳፻፰ ዓ.ም የጨርቆስ ልጅ እና ሌሎችም ብለህ የደረስከውን መጽሐፍ ገዝተን አነበብነው፡፡ እግዚአብሔር ይስጥልን፡፡ በመግቢያህ ላይ እንደገለጽከው ሁላችንም ሕይወት በመራችን ጎዳና እተበታተንን እንገኛለን፡፡ . . . ከዛሬ ሃያ ዓመት በኋላ ቂርቆስ የምትባል አንዲት ፍቅር የሰፈነባት የአዲስ አበባ መንደር ነበረች፡፡ . . . ተብሎ እንዳይቀር . . . በያለንበት ሆነን መረጃ የምንለዋወጥበት፡ የምንተባበርበት፡ የምንረዳዳበት፡ በተወሰነ ጊዜ የምንገናኝበትን መድረክ መፍጠር እንደሚቻል እንገነዘባለን፡፡ እኛም በመጽሐፍህ ከጠቀስካቸው የቂርቆስ ልጆች መካከል የንቡረ እድ ኤርምያስ ከበደን ማንነትና የጻፏቸውን መጻሕፍት በስዕላዊ መጽሔት(ቪድዮ) የተቀረጸ ስላገኘን ከዚህ በታች አባሪ አድርገነዋል፡፡
    በሚቀጥሉት ጊዜያት በመጽሐፍህ የተጠቀሱትን የቂርቆስ ሰበካ ሰዎች እያፈላለግን በስዕላዊ መጽሔት(ቪድዮ) የተደገፈ መረጃ ለማቅረብ እንሞክራለን፡፡ እግዚአብሔር ሥራችንን ይባርክልን፡፡

ความคิดเห็น • 1