2ኛ ትምህርት : የእግዚአብሔር ፍቅር እና ፍትሕ - ኪዳናዊ ፍቅር
ฝัง
- เผยแพร่เมื่อ 6 ก.พ. 2025
- ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡- 2ጴጥ. 3:9፣ ዘዳ. 7፡6-9፣ ሮሜ. 11:22፣ 1 ዮሐ. 4:7-20፣ ዮሐ. 15:12፣ 1 ዮሐ. 3:16
የመታሰቢያ ጥቅስ፡ ኢየሱስም መለሰ አለውም:- የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል፣ ወደ እርሱም እንመጣለን በእርሱም ዘንድ መኖሪያ እናደርጋለን” ( ዮሐንስ 14፡23)።
አጋፔ የሚለው የግሪክ ቃል ልዩ የሆነውን የእግዚአብሔርን ፍቅር እንደሚያመለክት፣ እንደ ፊልዮ ያሉት ሌሎች የፍቅር ቃላት ደግሞ ከአጋፔ ያነሱ የተለያዩ የፍቅር ዓይነቶችን እንደሚያመለክቱ ብዙዎች ተምረዋል። አንዳንዶች አጋፔ የአንድ ወገን ፍቅርን፣ የሚሰጥ ብቻ እንጂ የማይቀበል፣ በሰው ምላሽ የማይወሰን ፍቅርን ያመለክታል ይላሉ።
ሆኖም በቃሉ ያለውን መለኮታዊ ፍቅር በጥንቃቄ ስናጠና፣ እነዚህ አመለካከቶች ምንም እንኳን በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት ያገኙ ቢሆኑም የተሳሳቱ መሆናቸውን ያሳያል። በመጀመሪያ፣ አጋፔ የሚለው የግሪክ ቃል የእግዚአብሔርን ፍቅር ብቻ ሳይሆን፣ የሰው ፍቅርን፣ አንዳንድ ጊዜ የተሳሳተ የሰው ፍቅርን ጭምር ያመለክታል (2ጢሞ. 4፡10)። ሁለተኛ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከአጋፔ በተጨማሪ ሌላ ብዙ ቃላት የእግዚአብሔርን ፍቅር ያመለክታሉ።
ለምሳሌ፣ ኢየሱስ ሲያስተምር “እናንት ስለወደዳችሁኝ [ፊሊዮ]፣ አብ እርሱ ራሱ ይወዳችኋል [ፊሊዮ]” ይላል (ዮሐንስ 16፡27)። እዚህ ላይ ፊሌዮ የሚለው የግሪክ ቃል የሰውን ፍቅር ብቻ ሳይሆን፣ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ያለውን ፍቅርም ለማመልከት ጥቅም ላይ ውሏል። ስለዚህ ፊልዮ ጎደሎ የሆነውን የፍቅር ዓይነት ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔርንም ፍቅር ያመለክታል። ኪዳናዊ ፍቅር
በተጨማሪ ቅዱሳት መጻህፍት የእግዚአብሔር ፍቅር የአንድ ወገን ብቻ ሳይሆን ጥልቅ ግንኙነትን የሚጠይቅ እንደሆነ፣ ፍቅሩንም ለእርሱ እና ለሌሎች መልሰው ማንጸባረቅ ወይም አለማንፀባረቃቸው ለእግዚአብሔር ትልቅ ልዩነት እንዳለው ያስተምራሉ።
ወንጌል ለዓለም ሁሉ ❤❤❤