ไม่สามารถเล่นวิดีโอนี้
ขออภัยในความไม่สะดวก

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሁለት ምርጫ ጣቢያዎች ትናንት ሊደረግ የነበረው “ቀሪ ምርጫ” ለዛሬ ተላለፈ

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 23 มิ.ย. 2024
  • የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሚገኙ ሁለት የምርጫ ጣቢያዎች በትናንትናው ዕለት ሊካሄድ የነበረውን የ“ቀሪ ምርጫ” ሂደት ለዛሬ ማስተላለፉን አስታወቀ። ቦርዱ “አንሻ ገብርኤል እና ገንገን” በተባሉ ምርጫ ጣቢያዎች ምርጫውን ማካሄድ ያልቻለው የምርጫ ቁሳቁሶች በጊዜ ባለመድረሳቸው መሆኑን ገልጿል።
    ብሔራዊው የምርጫ ቦርድ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት፤ ስድስተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ በተካሄደበት ወቅት ሂደቱ ሳይከናወን በቀረባቸው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ አፋር፣ ሶማሌ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ላይ ትናንት እሁድ ሰኔ 16፤ 2016 ሲካሄድ ውሏል። የትናንቱ የቦርዱ መርሃ ግብር፤ ድጋሚ ምርጫ የሚከናወንባቸው ቦታዎችንም ያካተተ ነበር።
    ምርጫ ቦርድ “ቀሪ እና ድጋሚ ምርጫ” ለማድረግ አቅዶ የነበረው በ1,258 የምርጫ ጣቢያዎች ቢሆንም፤ የትናንቱ የድምጽ መስጠት ሂደት የተከናወነው በ1,218 ምርጫ ጣቢያዎች መሆኑን የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ሜላተወርቅ ኃይሉ ትናንት ምሽት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ በተወሰኑ የምርጫ ጣቢያዎች፤ የጽምጽ መስጠት ሂደቱ እስከ ምሽቱ ሁለት ሰዓት ድረስ የቀጠለ እንደነበርም ተገልጿል። (ኢትዮጲያ ኢንሳይደር)
    ተጨማሪውን ለማንበብ ይሄን ሊንክ ይጫኑ ethiopiainside...
    -------------------------------------------------------------------------------------------
    የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ትኩስ ዜናዎችን እና ወቅታዊ ዘገባዎችን ለመከታተል፦
    ድረ ገጽ ፦ ethiopiainsider...​
    ፌስቡክ ፦ / ethiopiainsider
    ትዊተር (ኤክስ) ፦ / ethiopiainsider
    ቴሌግራም፦ t.me/EthiopiaI...
    ቲክቶክ፦ / ethiopiainsider

ความคิดเห็น •