ไม่สามารถเล่นวิดีโอนี้
ขออภัยในความไม่สะดวก

“በሀገር በቀል ነጋዴ ስም፤ ሚሊዮኖችን የጎዳ የንግድ ስርዓት ይዘን መቀጠል የለብንም” -ዶ/ር እዮብ ፤የኢትዮጲያ የዕዳ ክፍያ እፎይታ በድጋሚ ይራዘማል ተባለ

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 24 มิ.ย. 2024
  • የኢትዮጵያ መንግስት የንግድ ስርዓቱን ለገበያ ክፍት የማድረግ አቅጣጫ መያዙ፤ “በጣም ወሳኝ ጉዳይ ነው” ሲሉ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታው ዶ/ር እዮብ ተካልኝ ተናገሩ። “በሀገር በቀል ነጋዴ ስም፤ ሚሊዮኖችን የጎዳ የንግድ ስርዓት ይዘን መቀጠል የለብንም” ሲሉም ሚኒስትር ዴኤታው አጽንኦት ሰጥተዋል።
    ዶ/ር እዮብ ይህን ያሉት በ2017 የፌደራል መንግስት በጀት ላይ ለመወያየት፤ የፓርላማው የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዛሬ ሰኞ ሰኔ 16፤ 2016 በጠራው ስብሰባ ላይ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው። ሚኒስትር ዲኤታው በዚሁ ማብራሪያቸው የኢትዮጵያ መንግስት የዋጋ ግሽበትን ለማረጋጋት እና ከሀገር ውስጥ የሚሰበስበውን ገቢ ለማሳደግ እየወሰዳቸው ያሉ እርምጃዎችን ዘርዝረዋል።
    “የንግድ ስርዓታችን ይዞት የሚመጣው ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ጭማሪ እያየን ነው። ይሄንን ማስቀጠል የለብንም” ሲሉ የተደመጡት ዶ/ር እዮብ፤ ይህን ችግር ለመፍታት መንግስት በመፍትሔነት ያስቀመጠው ውድድር እንዲኖር ማድረግ መሆኑን ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ከዚህ ቀደም ለሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ተከልለው የነበሩ የወጪ፣ የገቢ፣ የጅምላ እና የችርቻሮ የንግድ ዘርፎችን፤ አቅሙ ላላቸው የውጭ ባለሃብቶች እንዲከፈቱ የሚያስችል መመሪያ ባለፈው መጋቢት ወር ማውጣቱ ይታወሳል።(ኢትዮጲያ ኢንሳይደር)
    ተጨማሪውን ለማንበብ ይሄን ሊንክ ይጫኑ ethiopiainside...
    -------------------------------------------------------------------------------------------
    የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ትኩስ ዜናዎችን እና ወቅታዊ ዘገባዎችን ለመከታተል፦
    ድረ ገጽ ፦ ethiopiainsider...​
    ፌስቡክ ፦ / ethiopiainsider
    ትዊተር (ኤክስ) ፦ / ethiopiainsider
    ቴሌግራም፦ t.me/EthiopiaI...
    ቲክቶክ፦ / ethiopiainsider

ความคิดเห็น • 2