+ ወልደነጎድጓድ ዮሐንሥ መዝሙር | WELDENEGODGUAD YOHANIS MEZMUR
ฝัง
- เผยแพร่เมื่อ 25 ม.ค. 2025
- ወልደነጎድጓድ ዮሐንሥ መዝሙር | WELDENEGODGUAD YOHANIS MEZMUR
ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ዘብዴዎስ፣ ወልደ ነጎድጓድ፣ ፍቁረ እግዚእ፣ ነባቤ መለኮት/ታኦሎጎስ/፣ቁጽረ ገጽ በመባል ይታወቃል። ወንጌላዊው ቅዱስ ዩሐንስ ከ12ቱ ሐዋርያት አንዱ ሲሆን የመጀመሪያው ወጣት የመጨረሻው ሽማግሌ ሐዋርያ እሱ ነበር፡፡ ቅዱስ ዩሐንስ የተወለደው በገሊላ አውራጀ በቤተ ሳይዳ ነው፣ አባቱ ዘብዴዎስ ይባላል፡፡
ቅዱስ ዩሐንስ ገና በወጣትነቱ ዘመን ከወንድሙ ከያዕቆብ ጋር ለሐዋርያነት ከተጠራበት ጊዜ ጀምሮ የጌታውን እግር ተከትሎ አድጓል፡፡ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ የጌታ ደቀ መዝሙር ከመሆኑ በፊት የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር ከነበሩት ደቀ መዛሙርት አንዱ ነው፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ ለጌታውና ለፈጣሪው ለመድኃኔዓለም ክርስቶስ ባሳየው ልዩ ቀረቤታና ፍቅር ምክንያት “ፍቁረ እግዚእ” የሚል ስያሜ አግኝቷል፡፡ ፍቅሩንና ታማኝነቱንም ጌታ በተሰቀለ ጊዜ “እሱን ያገኘ ያገኘኛል፡፡” ብሎ ሳይፈራ ከእግረ መስቀሉ በመዋል በጽኑ እምነት አስመስክሮአል፡፡ በመሆኑም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቀራንዮ በመጨረሻዋ ሰዓት ቅዱስ ዮሐንስን ከእመቤታችን ጋር ከእግረ መስቀሉ ባየው ጊዜ እመቤታችን
ቅድስት ድንግል ማርያምን “እነሆ ልጅሽ ይርዳሽ፣ ያጽናናሽ”፤ ብሏታል፡፡ ደቀ መዝሙሩ ቅዱስ ዮሐንስም “እነኋት እናትህ ታጽናናህ” ብሎታል፡፡ ዩሐ. 19፥26፡፡
ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “እነሆ ልጅሽ ይርዳሽ ያጽናናሽ” ማለቱ እኛን ለቀረነው ክርስቲያኖች በቅዱስ ዮሐንስ አማካኝነት ለእመቤታችን መስጠቱን፣ ደቀ መዝሙሩን ቅዱስ ዮሐንስ “እነኋት እናትህ ታጽናናህ” ማለቱ እኛን እመቤታችሁ እናታችሁ ቅድስት ድንግል ማርያም ናትና ታጽናናችሁ፣ ተስፋ አለኝታ ትሁናችሁ ማለቱ እንደሆነ በግልጽ እንረዳለን፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ እንደ ጌታው ቃል እመቤታችንን ወደ ቤቱ ይዟት
ስለሄደ እመቤታችን በቤተ ዮሐንስ አስራ አምስት አመት ተቀምጣለች፡፡ከዚህም ኃይለ ቃል የምንማረው እመቤታችን በቤተ ዮሐንስ እንደኖረች ሁሉ በልበ ምእመናንም አድራ በሃይማኖት የምታጸና፣ ምግባረ ሃይማኖትን፣ ሕገ ትሩፋትን የምታሰራ፣ ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ክርስቶስ ድኀነተ ስጋንና ድኀነተ ነፍስን፣ በረከተ ስጋንና በረከተ ነፍስን የምታሰጠን መሆንዋን ነው፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ የጌታ ትንሣኤ በተነገረ ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስን ቀድሞ ከመቃብረ ክርስቶስ ከጎልጎታ እንዲገኝ ያደረገው የፍቅሩ ጽናት ነበር፡፡ የቅዱስ ዮሐንስ የድንግልና ሕይወትም ረቂቁን
ምስጢረ መለኮት /ምስጢረ ሥላሴ/ ለማየት አስችሎታል፡፡ ምስጢረ ሥጋዌን አስተካክሎ አደላድሎ በመጻፍ አምልቶ አስፍቶ አስተምሯል፡፡ የፍቅረ እግዚአብሔርን እና የፍቅረ ቢጽን ጠቃሚነት በስፋት የጻፈ ቅዱስ ዮሐንስ ነው፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ ረቂቁን ምስጢር አጉልቶ አምልቶ አስፍቶ ያስተማረ በመሆኑም ቤተክርስቲያን እንዲህ እያለች ታወድሰዋለች፡፡
ባሕረ ጥበባት፣
አበ ልሳናት፣
ንስር ሠራሪ
ልዑለ ስብከት፡፡
ዮሐንስ ወንጌላዊ ረአዩ ኀቡአት፡፡
ነገሩኒ ቅሱም በፄወ መለኮት፡፡
ሰባኬ ወንጌል
መጋቤ ሃይማኖት፡፡
ቀዋሚሃ ለቤተክርስቲያን፣
ኮከብ ስርግው፣
ውስተ ሕፅነ ገጽ ዘተሐፅነ፣
ዘኀቡአ ይኔጽር ምስጢረ መለኮት
ዘመንክረ ይገብር አምሳለ መላእክት
ዮሐንስ ድንግል ባሕረ ጥበባት የጥበባት ባሕር፣ የልሳኖች አባት፣
ሰማያትን ሰንጥቆ የሚበር ንስር፣ ልዑለ ስብከት፣ ኀቡአትን / ምሥጢራትን/ የሚያይ ወንጌላዊ ዮሐንስ፣ ነገሩ ሁሉ በምስጢረ
መለኮት የጣፈጠ /የተቀመመ/ ነው፡፡
መምህረ ወንጌል የሃይማኖት መጋቢ ነው፡፡
የቤተክርስቲያን አለኝታዋ፣ የተሸለመ ኮከብ ነው፡፡ ነደ እሳት በሆነ በሕፅነ መለኮት በንጽሕና የታቀፈ፣ ረቂቁን ምሥጢረ መለኮት የሚያይ የሚመረምር የጥበባት ባሕር ድንግሉ ቅዱስ ዮሐንስ እንደ መላእክት ድንቅ ሥራን ይሠራ፡፡ ትለዋለች፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ፡- በስሙ የሚጠራውን አራተኛውን ወንጌለ ክርስቶስ፣ ሕዝብንና አሕዛብን፣ ፍጡርንና ፈጣሪን በብቃት ያገለገለ ታላቅ ሐዋርያ ነው፡፡ ስለ ስጋዊ ሕይወቱ ፍጻሜ ጌታ “እስክመጣ ድረስ ይኖር ዘንድ ብወድስ ምን አግዶህ” ብሎ ለቅዱስ ጴጥሮስ በነገረው መሠረት አልሞተም በክብር ከቅዱሳን ጋር በአንድነት አለ እንጂ፡፡ ዮሐ 21፥22፡፡መታሰቢውም ወር በገባ በ አራት ነው።
ቅዱስ ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌሉ እንደነገረን በመንግስተ ሰማያት ታላቁ ሰው ወንጌላዊው ዮሐንስ ነው:: ቅዱሱ ሐዋርያ ከዘብዴዎስና ከማርያም ባውፍልያ ተወልዶ: በገሊላ አካባቢ አድጐ: ገና በወጣትነቱ መድኃኔ ዓለምን ተከትሎታል::
+ቅዱስ ዮሐንስ ከሐዋርያት ቀድሞ ጌታን ከመከተሉ ባሻገር በምንም ምክንያት ከጐኑ አይጠፋም ነበር:: ስለ ንጽሕናውና በጐ የፍቅር ሕሊናው ሕጻን ሳለ በወንድሞቹ ሐዋርያት ዘንድ ሞገሱ ከፍ ያለ ነው:: ጌታችንን እስከ እግረ መስቀሉ ድረስ በመከተሉ ድንግል እመቤታችንን ተቀብሏል::
+ከእርሷ ጋር ለ15 ዓመታት ቢቀመጥ መዝገበ ምሥጢር ሆነ:: ስንኩዋን ከሰው ልጆች ይቅርና ከልዑላኑ መላዕክትም ማዕረጉ ከፍ አለ:: ሰው ቢበቃ መላእክትን ሊያይ ይቻለዋል:: ቅዱስ ዮሐንስን ግን መላእክት ሊያዩት ይከብዳቸዋል:: ከፍጥረት ወገን ከእመ ብርሃን ቀጥሎ ክቡር እርሱ ነው::
+ቅዱስ ዮሐንስ በታናሽ እስያ ለ7ቱ አብያተ ክርስቲያናት መስበኩ ይታሰባል:: ቅዱሱ ከጌታችን ዕርገት በሁዋላ ለ70 ዓመታት በዚህ ምድር ሲኖር አብዛኛውን ጊዜውን ያሳለፈው በኤፌሶን አካባቢ ነው:: ሕዝቡን ወደ ክርስትና ለማምጣት በአፍም በመጽሐፍም ደክሟል::
+3 መልዕክታት: ራዕዩንና ወንጌልን ጽፎላቸዋል:: ሕይወትን ስለ ሰበከላቸው በፈንታው ብዙ አሰቃይተውታል:: ከእሳት እስከ ስለት: እስከ መጋዝም በስተእርጅና ደርሶበታል:: እርሱ ግን በትእግስቱ ገንዘብ አድርጉዋቸዋል::
እንኳን. አብሩ. አደረሰን. አሜን. አሜን. አሜን❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
አሜን አሜን አሜን ዚማር መልክት ያስማልን ❤❤❤❤❤🎉🎉🎉🎉🎉
Ameen Ameen Ameen ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉
እልልልልል 🙏🙏🙏❤️❤️❤️🎉🎉🎉
እንኳን አደረሳችሁ❤❤❤❤❤❤🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
Amen amen amen ❤❤❤❤❤❤🎉🎉🎉❤❤❤❤❤
Amen Amen Amen ❤❤❤
Amen 🙏 elllllllele 🙏 Amen 🙏
እኳን አደርሳችሁ 🎉🎉🎉❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤🎉🎉🎉🎉
❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤wow
ሰላም.ናቹ.ዛሬ.ፀሎት.የለም.በሰላም.ነው.
እልእንዃንአደረስን
እልልልልልልል
❤❤❤❤❤❤
Ellllllllllllllleeeeeee
❤🎉❤❤🤲👏👏
❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
❤❤❤❤🎉🎉🎉🎉🎉🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
❤❤❤🎉🎉🎉🎉
❤❤❤❤❤❤❤❤❤🎉🎉🎉🎉
እልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልል❤❤❤👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏ዝማሬመላአክትያሰማልን
😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
🙏🙏🙏🙏🙏👏👏👏👏✋💚❤💙🌾🌾👏👏🎉🎉🎉🎉🎉
❤❤❤❤❤❤❤
❤❤❤❤❤❤🎉🎉🎉🎉🎉🎉
አሜን❤አሜን❤አሜን❤❤እንኳንአብሮአደረሰን🙏🙏🙏🙏❤❤❤❤❤❤❤❤❤