🛑አኑሮኛል ቸርነትህ ዘማሪ ዲ/ን ፅጌ አስተርአየ(ባለሻሹ)anurognal cherneth mezmur cover by zemari diakon tsege asteraye

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 10 ก.ย. 2024
  • ዚቅ ሚድያ ZIQ MEDIA
    @ZIKMEDIA
    ይህ ቻናል በቤተክርስቲያናችን እጅግ ድንቅ ፀጋ የተሰጣቸው ልጆችን በማበረታታት እና በፀጋቸው እንዲያገለግሉ እድሉን በመፍጠር እና በተለያዩ አለማዊ ህይወት ለተዋጥነዉ የቤተክርስቲያናችን ድንቅ ወጣቶች የተለያየ የዝማሬ ፀጋቸዉን ወደ እናንተ የምናደርሰበት ቻናል ነው
    ቻናላችንን ሰብስክራይብ በማድረግ አጋርነታችሁን አሳዩን
    እናመሰግናለን
    አኑሮኛል ቸርነትህ
    ልክ የሌለው ደግነትህ
    እንዳንተ አይነት ከዬት ይገኛል
    ሁሉም ነገር ትዝ ይለኛል
    ያቺ ፈዋሽ አዳኝ እጅህ
    ዛሬም ለኔ ተዘርግታ
    በሐጢያት እርቄ እንዳልጓዝ
    አስረህኛል በውለታ
    ደግሞስ ህይወት ምርጫ ቢሆን
    ካንተ ወደማን ይኬዳል
    አባቴ ፍቅርህ እኮ
    ጌታዬ ፍቅርህ እኮ
    አለምን ያስክዳል
    ሞቸ ነበር ተቀብሬ
    ጌታ ወደ እኔ ባትመጣ
    አንተ ሞቴን ባትሞትልኝ
    ወዴት ነበር የእኔ እጣ
    ከንቱ ነበር ማንነቴ
    ተሽናፊ ለዚች ዓለም
    ግን አንተ የያዝከው
    አባቴ የያዝከው
    ይኖራል ዘላለም
    መቅደስህን ተጠግቼ
    አይቻለሁ ብዙ ነገር
    በልቤ ውስጥ ያስቀመጥኩት
    እንዲህ ለሰው ማይነገር
    ግን የሆነው ሁሉም
    ሆኖ የለም ዛሬ ያላረፈ
    የመከራው እሳት
    የፈተናው እሳት
    ባንተ እየታለፈ
    አይጠፋኝም ያ ፈገግታ
    ልጅ ብለህ ያሳየህኝ
    አመፅኛ መጥፎም ሆኜ
    በትክሻህ ላይ ያኖርከኝ
    እንዲህም አይነት ወዳጅ አለ
    እየጠሉት የሚያፈቅር
    ስሙም ኢየሱስ ነው
    የፅድቃችን ሚስጥር
    ስነፈርቅ ሳለቅስብህ እሺ
    እያልከኝ ሁሉም ሆነ
    ማይሆንለት ነገር የለም
    ለካስ ባንተ የታመነ
    መቸኮሌ መጣደፌ
    አምላኬ ሆይ በከንቱ ነው
    መፈፅሙ ላይቀር
    ጌታዬ አንተ ያልከው

ความคิดเห็น • 430