ไม่สามารถเล่นวิดีโอนี้
ขออภัยในความไม่สะดวก

በአማራ ክልል የኢንተርኔት አገልግሎት መልሶ ለማስጀመር “ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተነጋገረ መሆኑን” ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 9 ก.ค. 2024
  • መንግስታዊው የቴሌኮም አቅራቢ ተቋም ኢትዮ ቴሌኮም፤ በአማራ ክልል የተቋረጠውን የኢንተርኔት አገልግሎት ለሁሉም ደንበኞች መልሶ ለማስጀመር፤ ከክልሉ መንግስት እና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተነጋገረ መሆኑን አስታወቀ። በክልሉ ያሉ የተለያዩ ተቋማት የኢንተርኔት አገልግሎት በአሁኑ ወቅት ማግኘት መጀመራቸውን ተቋሙ ገልጿል።
    ኢትዮ ቴሌኮም ይህን የገለጸው ባለፈው ሳምንት መጨረሻ የተጠናቀቀውን 2016 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸምን በተመለከተ ዛሬ ረቡዕ ሐምሌ 3፤ 2016 በአዲስ አበባው ስካይ ላይት ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው። የዛሬውን መግለጫ ለሰጡት የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ከቀረቡላቸው ጥያቄዎች መካከል፤ “በጸጥታ መደፍረስ ምክንያት የኢንተርኔት አገልግሎት የተቋረጠበትን” የአማራ ክልል የተመለከቱት ይገኙበታል።
    በአማራ ክልል የኢንተርኔት አገልግሎት በመቋረጡ ምክንያት ተቋሙ ያጣው ገቢ ምን ያህል እንደሆነ ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ተጠይቀዋል። በዋነኛነት በአማራ ክልል ተግባራዊ ሲደረግ የቆየው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የጊዜ ገደብ በመጠናቀቁ፤ በክልሉ ተቋርጦ የቆየው የኢንተርኔት አገልግሎት “የሚመለስበት ዕድል አለ ወይ?” የሚል ጥያቄም ቀርቦላቸዋል።(ኢትዮጲያ ኢንሳይደር)
    ተጨማሪውን ለማንበብ ይሄን ሊንክ ይጫኑ ethiopiainside...
    -------------------------------------------------------------------------------------------
    የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ትኩስ ዜናዎችን እና ወቅታዊ ዘገባዎችን ለመከታተል፦
    ድረ ገጽ ፦ ethiopiainsider...​
    ፌስቡክ ፦ / ethiopiainsider
    ትዊተር (ኤክስ) ፦ / ethiopiainsider
    ቴሌግራም፦ t.me/EthiopiaI...
    ቲክቶክ፦ / ethiopiainsider

ความคิดเห็น • 6

  • @MsKarima-yl7eq
    @MsKarima-yl7eq หลายเดือนก่อน

    ያረብ እዉነትያድርግልን

  • @ToyibaassenAssen
    @ToyibaassenAssen หลายเดือนก่อน

    ያአላህ እውነት ያርገው❤

  • @user-xg5lr7ue6z
    @user-xg5lr7ue6z หลายเดือนก่อน

    እውነት ያ ርግልን ያረብ

  • @mintamir4333
    @mintamir4333 หลายเดือนก่อน

    ሰላም ለናት ይሁን እረ አማራ አስጀምሩልኝ በርቱልኝ

  • @AbdMehd
    @AbdMehd หลายเดือนก่อน +1

    850 ሺ ብር በአንድ ቀን አዳር አጥቻለሁ በኢንተርኔት መቋረጥ ብቻ እባካቹ ልቀቁልን ብዙ ስራ ተበላሽቶብናል በአላህ እንለምናቹ

  • @matthewassefa1925
    @matthewassefa1925 หลายเดือนก่อน +1

    WODESH NEWU !!! DILL LE AMHARA FANOO