ገንዘብ ሚኒስቴርና ተጣሪ ተቋማቱ በደቡብ ክልል ቃጫቢራ ወረዳ አዋዬ ቀበሌ ችግኝ ተከሉ
ฝัง
- เผยแพร่เมื่อ 23 ธ.ค. 2024
- የገንዘብ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት ሰራተኞች በደቡብ ክልል ቃጫቢራ ወረዳ አዋዬ ቀበሌ አረንጓዴ አሻራቸውን ለማሳረፍ ችግኝ ተክለዋል፡፡ በችግኝ ተከላው ላይ የተገኙት የገንዘብ ሚንስትር አቶ አህመድ ሽዴ አንደተናገሩት የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ለመንግስት ከፍተኛ ወጭ የሚቀንስ በበጀት እንስራው ብንል ኖሮ መወጣት የምንችለው ስራ አልነበረም ብለው፤ የሕዝቡን ጉልበትና ዕውቀት አስተባብረን አደረጃጀቶችን ተጠቅመን መስራታችን ለሌሎችም ተምሳሌት የሚሆን ውጤት አምጥቷል ብለዋል፡፡ ከአረንጓዴ አሻራ ጎን ለጎንም በሺኒሺቾ ከተማ የአቅመ ደካሞችን ቤት ለማደስ በገንዘብ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት ስራ መጀመሩን አቶ አህመድ ሽዴ ተናግረው፤ በአካባቢው ያለውን ዕምቅ የመልማት አቅም ጥቅም ላይ ለማዋልም ከህብረተሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡