አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ምስክርነት / Abune Echege Yohannes Gedam

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 30 พ.ย. 2024
  • አድራሻ፦ ሰሜን ሸዋ በደብረ ብርሃን መስመር መንዝ ዘብር ቅዱስ ገብርኤል፣ አርባሃራ መድሃኒዓለም፣ እመጓ ቅድስ ኡራኤል፣ይገም ቅዱስ ሚካኤል፤እሳቷ ጽዬን ማርያም፣ዳስ አባ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና 12ሃዋርያት ገዳም መሄጃ ከአዲስ አበባ 195ኪሜ እንደተጓዙ "መዘዞ ከተማ"እንደደረሱ ከመዘዞ ከተማ የ1ሰዓት የእግር መንገድ ጠገሮ ባዕለወልድ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ገዳም።
    ------------------------------------------------------------------------------------------------
    እጅግ በጣም ብዙ የእግዚአብሔርን ስራ ማየት ትችላላችሁ ወይም ምስክርነቱን ከታች ባስቀመጥኩት የፌስቡክ አድራሻ ማየት ትችላላችሁ፡፡
    በ3ወር ውስጥ የዳኑ.............ከካንርሰ 657ሰው ፤ስኳርና ደምብዛት1771ሰው፤ የደም መፍሰስ፤(የወር አበባቸው የተስተካከልላቸው በ3ወር ውስጥ፦......... 1አመት 3,4,5,6,7,8,9,ወር ሙሉ የሚፈሳውቸ 2566 ሴቶች ድነዋል)
    229ሴቶች መሃን የሆኑ አርግዘዋል፤ስራ ሰጡን ያሉ 3066፤ዴስክ በሽታ 1003ሰው፤የመሃጸን እጢ 1172ሰው ድነዋል ፤HIV 202ሰው፤ኩላሊትዲያለስስ የሚያደርጉ22ሰው ድነዋል፤ከኩላሊት በሽታ798ሰው፤እራስምትታ ጨጓራ የእግር የወገብ ህመም 2903ሰው ድነዋል፡፡
    ይህ የቤተ ክርስቲያኑ አሰሪ ኮሚቴ ስልክ ነው፡፡ ሁሉንም መረጃ በዚህ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
    ዮሐንስ - 0911 19 02 12 , 0911 48 13 88 , 0979 98 69 69
    / johnny.aleme.5
    ------------------------------------------------------------------------------------------------
    አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ *
    አባታችን የተወለዱት በኢየሩሳሌም አውራጃ ልዩ ስሙ ሳሬራ በሚባል የካቲት 28 ተፀንሰው በወራሀ ህዳር 28 ለ29 ሌሊት ተወለዱ - ህዳር29 ተወለዱ ፣የአባታቸው ስም ዲላሶር ሲባል የእናታቸው ስም ደግሞ እምነ ፅዩን ይባላል። ወላጆቻቸው እግዚአብሔርን የሚፈሩ ደጋግ ፃድቃኖች ናቸው ፃድቁ አባታችን ገና በአምስት አመታቸው ሳሉ ወላጆቻቸው ወደ እግዚአብሔር ቤት ይዘዋቸው ሲሄዱ ፍቅሩ ወልዳ ስለ ማርያም ተመልክተው መሳቅ ጀመሩ እመቤታችን ድንግል ማርያም ከምስሉ ወጥታ በምን አውቀህኝ ነው ብላ አቅፋ ሳመችሁ ከእንግዲ በኃላ የልጄ አገልጋይ ትሆናለህ ኑሮህም እንደ መላዕክት ይሆናል በአንተ ምክንያት ብዙ ሰዎች ይድናሉ በምድር ላይም 500 ትኖራለህ ብላ ባርካው ተሰወረች። ከዚያችም ቀን ጀምሮ አባ ዩሐንስ ለክርስቶስ ተላልፎ ተሰጠ 50 ዓመትም በበረሃ ሲጋደል ኖሮ ከ50 ዓመት በኃላ በደመና ተጭኖ በመላዕኩ ቅዱስ ገብርኤል መሪነት ወደ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ መጡ። ፃድቁ አባታችን በአቡነ ተክለሃይማኖት ዘመን መጨረሻ የመጡ ሲሆን ምንኩስና ከደብረ ሊባኖስ ገዳም ተቀብለው ለ50 ዓመት በፆምና ፀሎት በተጋደሉ ቆይተዋል። አባ ዩሐንስ ወደ ተዘጋቸላቸው ምድር በቅዱስ ገብርኤል አሳሳቢነት ወደ ጠገሮ መጡ። ይህ ገዳማቸው የሚገኘው በሰሜን ሸዋ በመንዝናይፋት ክልል መዘዞ በሚባል ቦታ ሲደርሱ በእግር 1 ሰዓት ከተጓዙ በኃላ የሚገኝ ሲሆን አስደናቂ የፃድቁ የእጬጌ ዩሐንስ ገዳም ነው።አባታችን ተጋድሏቸው ሳሉ ሰዎች በክፋት ተነሱባቸው ሰይጣን በእነርሱ አድሯልና እንዴት እንደሚያጠፋቸው ይማከሩ ጀመር ሊገድሏቸው ፈልገው ቅድስናቸው በሁሉ ዘንድ የታወቀ ነውና ፈሩ ለምን ከምንደራችን ከወንድ ያረገዘች ሴት ፈልገን በሐሰት እንክሰሳቸው ብለው ወርቅና ብር ለሴቷ ሰጥተው በአሰት ከእርሱ አርግዣለሁ ብላ እንድትናገር አደረጎት አባታችንን በሕዝብ ፊት በአሰት ተከሰሱ ፃድቁም አንቺ ሴት ከእኔ ነው ያረገሽው አሏት እርሷም አዎ ከአንተ ነው ልትክድ ነው እንዴ አለችሁ አባታችንም አዝነው በአንቺና በእኔ መካከል እግዚአብሔር ይፍረድ ሲሉ ወዲያው ለሁለት ተሰንጥቃ ሞተች የአገሩ ሰዎች ፈሩ ፃድቁም ምድሯን እረገሟት የተዘራው ዘር አይብቀልብሽ የተተከለው አይፅደቅ ብርድና ውርጭ ይፈራረቅብሽ ብለው ረግመዋት በደመና ተጭነው ወደ ሰሜን ጎንደር እስቴ ጉንደ ተክለተሃማኖት ሄዱ። አባ ዩሐንስ በመላው ኢትዮጰያ ዞረው ያስተማሩ ሲሆን ከቅድስናቸው የተነሳ በፀሐይ ላይ 50 ዓመት በጨረቃ ላይ 50 ዓመት በደመና ላይ 50 እንዲሁም አለም በክንፎ በመዞር በደመና ላይ 50 የኖሩ አባትም ናቸው ከሰው ተወልደው ከመላዕክት ተደምረዋልና በይፋት ጠግሮ ባለወልድ ፣በአፋር አዘሎ፣በመንዝ ፍርኩታ ኪዳነምሕረት፣በደብረ ሊባኖስ፣ በጉንደ ተክለሃይማኖት በሌሎችም ስፍራ በመዘዋወር በታላቅ ተጋድሎ በፆምና ፀሎት ቆይተዋል። ከሰማይ መስቀል የወረደላቸው ሲሆን ዛሬም በገዳማቸው የሄደ ሰው በወረደው በእጃቸው መስቀል እየተዳበሰ ቆመው በፀለዩበት ባሕር በፀበላቸው ይጠመቃል በተጨማሪም ይዞሀት በነበረው መቋሚያ ጀርባችንን እንዳበስበታለን ማየት ማመን ነውና ከምስሉ ተመልከቱ መጥታችሁ ገደሙን ማየት ነው ።
    ቆመው ከፀለዩበት ባሕር ውስጥ ደረቅ አሸዋ ይወጣል በገዳማቸው አባ ዩሐንስ 500ዓመት ከኖሩ በኃላ እረፍተ ዘመናቸው ደረሰ መዳኒዓለምም ከ15 ነቢያት ከ12 ሐዋሪያት ሄሮድስ ያስፈጃቸው ከአርባ አራት ሺው ሕፃናትን አብርሃም ይሳዕቅ ያዕቆብን ሁሉንም ነገደ መላዕክትን ነበያት ሃዋርያትን ጻድቃን ሰማዕታትን አስከትሎ መጣ ለአባ ዩሐንስ ቃልኪዳን ሰጣቸው ስምህን የጠራ ገዳምህን የረገጠ፣መባ የሰጠ፣ቤተክርስትያንህን የሰራ ያሰራ የረዳ፣ ገድልን የሰማ ያሰማ ያስተረጎመ፣ መታሰቢያን ያደረገ፣ እስከ10 ትውልድ እምርልሀለው ንስሀ ሳይገባ አይሞትም ልጅ መውለድ ባይችል ማህን ቢሆን እኔ ልጅ እሰጠዋለሁ የክርስትያን ማደርያ በሆነች ገነት - ደብረ ፂዮን - በብርሃን ቦታ አስቀምጠዋለሁ ብሎ ቃል ኪዳን ሰጣቸው ገድላቸው በጥቂቱ ነው እንዲሁም ገድልህን በቤትህ ያስቀመጠ እርኩስ መንፈስ አይነካውም፣ክፉ አጋንት አይነካውም፣ቸነፈርና ወባ አይነካውም፣መላኢከ ጽልመት አይነካውም።በገዳምህ መነኩሴ ቢቀበር በሰማይ ክንፍ አበቅልለታለሁ፣አይሁድም አረማዊም ያላመነ ያልተጠመቀ በገዳምህ መጥቶ ቢያርፍ ይቅር እልለሃለሁ እንደ መቃብሬ ጉልጎታ እንደተቀበረ አድርጌ እቆጥርልሃለሁ። የነገርኳችሁ ከዚህ በኃላ ወደ ሰማይ አረገ አባ ዩሐንስ ሐምሌ 29 ቀን አረፉ።
    በጉንደ ተክለሃይማኖትም ተቀበሩ 157ዓመት በኃላ አንድ የበቁ ባሕታዊ ወደ መንዝ ሄደው የረገሟት መሬት እንድትቀደስ የተዘራው እንዲበቅል ከስውራን አባቶች ጋር በመሆን ግማሽ አፅማቸውን ከጉንደ ተክለሃይማኖት አውጥተው አርባሐራ መዳኒዓለም አጠገብ በላይ በፍሩክታ ኪዳነምሕረት መጋቢት 18 ፍልሰተ አፅሙ አረፈ ምድሪቷም ተባረከች የዘሩትንም አበቀለች ውርጩም ብርዱም ቀነሰ ዝናብ አልዘንብ ሲል ሰብል የሚጨርስ አንበጣ ሲመጣ ታቦታቸው ወጥቶ ምዕላ ይያዛል ወድያውም መቅሰፍት ይርቃል ዝናብም ይዘንባል። ፀበላቸው ሽባ ይተረትራል ድውይ ፈዋሽ ከሰማይ የወረደላቸው መስቀልም ታምር ሰሪ ከባሕራቸው ደረቅ አሸዋ የሚወጣበት የጠገሮ ፃድቁ እጬጌ ዩሐንስ በረከት ይደርብን አሜን!!!
    ገዳሙ እንርዳ ሊፈርስ ነው፦!!ገዳሙ ሊፈርስ ነው እንድረስለት እረ የምንሰራ ከ10አንድ እኮ የእግዚአብሔር ነው እንዳንቆጭ እንድረስለት መርዳት የምትፋልጉ ገዳሙን ባንክ ብቻ አስገብ በጻድቁ ስም ለሚለመን ለሰው አትስጡ በጻድቁ ስም ማህበራትም ሆነ ጉዞ አዘጋጆች ገዳሙና ኮሜቲው ሳያውቅ ማጫረትም ሆነ በጻድቁ ስም መለመን ውግዝ ነው የተወገዘ ነው መርዳት የምትፈልጉ በገዳሙ ስም በተከፈተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ አስገቡ ፤ወይም ገዳሙ በመሂድ በማይት በምትችሉት አቅም በጉልበት በሙያ እና በመስርያ ዕቃ እርዱ ፤ለማንም ሰው በጻድቁ ስም ለሚለምን ሰው አትስጡ አደራ እላለሁ፦
    Account No-1000199224054
    Account Name-Tegero Abune Echuge Yohannes Church - ጠገሮ
    አቡነ እጨጌ ዮሃንስ
    swift Code-CBETETAAኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - Commercial Bank of
    Ethiopia
    -------------------------------------------------
    ምንጭ - Johnny Aleme ---
    እጅግ በጣም ብዙ የእግዚአብሔርን ስራ ማየት ትችላላችሁ ወይም ምስክርነቱን ከታች ባስቀመጥኩት የፌስቡክ አድራሻ ማየት ትችላላችሁ፡፡ ከካንሰር፣ ከኩላሊት እና ከተለያዩ በሽታዎች የዳኑ አሉ፡፡
    ይህ የቤተ ክርስቲያኑ አሰሪ ኮሚቴ ስልክ ነው፡፡ ሁሉንም መረጃ በዚህ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
    ዮሐንስ - 0911 19 02 12 , 0911 48 13 88 , 0979 98 69 69
    / johnny.aleme.5

ความคิดเห็น • 2

  • @abraraiar1080
    @abraraiar1080 4 ปีที่แล้ว +1

    👍👍👍

  • @daniboy9134
    @daniboy9134 4 ปีที่แล้ว +1

    በጣም ድንቅ ታአምር ነዉ ግን የት ክፍላገር ነዉ