DEDUCTABLE EXPENSE Part 1/ተቀናሽ የሚደረጉ/ የተፈቀዱ ወጪዎች ክፍል 1, ከሠንጠረዥ ለ እና ሐ ገቢዎች ላይ የሚቀነሱ ወጪዎች

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 27 พ.ค. 2024
  • ለበጎ አድራጎት ዓላማAllowable expenses ተቀናሽ የሚደረጉ የተፈቀዱ ወጪዎች
    ለስራ አስፈላጊ የሆኑ ወጪዎች
    ማንኛውም ወጪ
    በግብር ከፋዩ ገቢ ውስጥ የተካተቱትን ገቢዎች ለማግኘት
    ለስራው ዋስትና ለመስጠትና
    ስራውን ለማስቀጠል
    ወጪዎቹ ከሚያስገኙት ገቢ፣ ለስራው ከሚሰጡት ዋስትና እና ቀጣይነት ጋር ሲነፃፀሩ ያልተጋነኑ መሆን አለባቸው
    የንግድ ስራ እንቅስቃሴው በተቋረጠበት በተወሰነ ጊዜ ውስጥ /ስራ ባላገኘበት ጊዜ ያወጣው የማይቀሩ ወጪዎች fixed costs(የቤት ኪራይ ፣የሰራተኛ ደመወዝ፣ መብራት፣ውሃ፣ስልክ፣…) ገቢ ያላስገኙ ወጪዎች
    ለማዘጋጃ ቤት አገልግሎት የተከፈለ ክፍያ
    EXCISE TAX
    የተመዘገበ TOT
    ተመላሽ ያልተደረገ/በጊዜው ባለመቅረቡ ተመላሽ የማይደረግ VAT
    ከተከፋይ ሒሳብ ተቀንሶ የሚከፈል ግብር (ከተቀጣሪ የስራ ግብር እና በእቃ/አገልግሎት ግዢ ወቅት ከተከፋይ የሚቀነስ ግብር) ቀንሶ ገቢ ያላደረገ ቢሆንም ወጪ መውጣቱ ከተረጋገጠ ሊከፈል የሚገባው ግብር፣ ወለድና ቅጣት ከፍሎ ወጪው ተቀናሽ የደረጋል
    የንግድ ስራውን የሚከውንበት ህንፃ በነፃ የተፈቀደለት/በተከራየው ህንፃ በባለቤቱ ስም የተከፈለ የመብራት፣ የውሃ/የስልክ ነገር ግን ግብር ከፋዩ የመክፈል ኃላፊነት እንዳለበት ከተዋዋለ እና ኦርጅናል ደረሰኝ ካቀረበ
    ለንግድ ድርጅት እና መኖሪያ ቤት በአንድ የመብራት/የስልክ/የውሃ ቆጣሪ የሚጠቀም ከሆነ የወጪ 75%
    አንድ ወጪ ከአንድ በላይ የሆኑ የገቢ አይነቶችን ለማስገኘት የዋለ እንደሆነ የወጪ ክፍፍል የሚወሰነው ወጪው ጥቅም ላይ በዋለበት ጊዜ ከእያንዳንዱ የገቢ አይነት በተገኘ የገቢ ድርሻ ልክ ይሆናል
    አንድ ወጪ አንድን ገቢ ለማግኘት እና ሌሎች አላማዎች የዋለ ከሆነ የወጪው ክፍፍል የሚወሰነው የወጪዎቹ አንፃራዊ ባህሪና መጠን ግምት ውስጥ በማስገባት ገቢ ለማግኘት የዋለበት መጠን ብቻ በመውሰድ ይሆናል
    ግለሰብ ነጋዴ ከመደበኛ የሥራ ቦታው ከ25 km በላይ በመሄድ የንግድ ስራውን ለማከናወን ሲንቀሳቀስ ለሚያወጣቸው ወጪዎች ለምግብ እና ለመኝታ በቀን እስከ 1000 ብር በተጨማሪም ለትራንስፖርት ያወጣው ወጪ በስራ ላይ ባለው የአየር፣ የውሃ እና የየብስ የትራንስፖርት ዋጋ በማስረጃ
    ጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅት በስራ ላይ ላሰማራው አባሉ የሚከፍለው የደመወዝ ወጪ
    የውክልና /የኃላፊነት ወጪ የግብር ከፋዩ ሰራተኛ የንግድ ስራውን ለማስተዋወቅ እና ለማሳደግ እንግዶችን ከንግድ ስራ ቦታው ውጪ ለመቀበል የሚያወጣው የመስተንግዶ ወጪ ነው (ደንብ 27)፡፡ የውክልና /የኃላፊነት ወጪ ተቀጣሪው በመቀጠር ከሚያገኘው ገቢ እስከ 10% ድረስ እንዲሁም የንግድ ስራውን የማስተዋወቅ እና የማሳደግ ስራ በኃላፊነት ለሚሰራ ሰራተኛ/ የስራ መሪ
    ቀጣሪ ለተቀጣሪ የሚከፍለው የጤና መድን አርቦን እና ለሠራተኛው የሕክምና ወጪ (ደንብ 29)
    በኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆነ ድርጅት በኢትዮጵያ ውስጥ ላለው በቋሚነት ለሚሰራ ድርጅቱ ጥቅም ያደረገውን ወጪ ለመተካት ለተገቢ ወጪ
    ገቢ ለማግኛ፣ ዋስትና ለማሰጠትና፣
    በቋሚነት በሚሰራ ው ድርጅት ሊሰራ የማይችል ሲሆን ብቻ
    በዲዛይን ለውጥ ምክንያት ህንጻ ፈርሶ ሲገነባ የፈረሰው ህንፃ የመዝገብ ዋጋ በውጪ ተቀናሽ ይያዛል፡፡ (comp)
    የተበላሸ እቃ፣ የአገልግሎት ጊዜ ያለፈባቸውና የተወገዱ እቃዎች እንደዚሁም ለማስወገድ የወጣ ወጪ
    የተሸከርካሪ ጎማ የሚሰጠው አገልግሎት ከ1 ዓመት ያነሰ እንደሆነ እንደ አላቂ ዕቃ ተቆጥሮ በተቀናሽ ወጪ የሚያዝ ይሆናል፡፡
    የወለድ ወጪ
    ብድሩ የንግድ ስራ እንቅስቃሴ ከዋለ፤
    ብድሩ ን ለሌላ አላማ ካዋለ/ለሌላ ተግባር ያበደረ እንደሆነ ተቀናሽ የሚደረገው ወለድ ለሌላ ጉዳይ የዋለው ከተቀነሰ በኃላ ነው
    በዱቤ ለሚገዛው ዕቃ /አገልግሎት ዋጋውን እስኪከፍል ድረስ ወለድ እንደሚከፈልበት ውል የገባ ከሆነ
    ብድሩ ለህንፃ ግንባታ የዋለ እንደሆነ ግንባታው እስኪያልቅ የተከፈለው ወለድ በእርጅና ተቀናሽ ይደረጋልል፣ ህንፃው ከተጠናቀቀ በኃላ የተከፈው ወለድ በወጪ ተቀናሽ ይደረጋል
    ለውጭ ሀገር አበዳሪ የተከፈለ ወለድ ተቀናሽ የሚደረገው አበዳሪው ብድር ለመስጠት ከኢትዮጲያ ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ ያገኘበትን ሰነድ ቅጂ ተበዳሪው ለባለስልጣኑ ካቀረበ ብቻ ነው
    የምርት ብክነት ወጪ
    በምርት ዝግጅትና አቅርቦት ሂደት (በብጣሪ፣ በትነት፣ በማቅለጥ፣ በሽርፍራፊ፣ በጊዜ ቆይታ ወዘተ) የሚባክን ምርት የእቃ መጠን በሚመለከተው የመንግስት አካል በቀረበ ጥናት መሰረት እንደ ወጪ ይያዛል
    የተሙአላ ጥናት ማግኘት ካልተቻለ በለስልጣኑ ከግል ተቁቀማት፣ ከግብር ከፋዮች፣ አግባብነት ያለው አካል /ወይም ባለስልጣኑ በሚያደርገው ጥናት መሰረት ወጪ የሚያዝበትን መጠን ሊወስን ይችላል
    የማይሰበሰቡ እዳዎች
    ሊሙአሉ የሚገቡ ሁኔታዎች
    ከማይሰበሰብ እዳ ጋር ተመጣጣኝ የገንዘብ መጠን ቀደም ሲል የግብር ከፋዩ የንግድ ስራ ገቢ ሆኖ ተይዞ ከሆነ
    እዳው/የእዳው የተወሰን የገንዘብ መጠን ከግብር ከፋዩ የግብር አመት የሂሳብ መዝገብ ላይ ሲሰረዝ
    ተቀናሽ የሚደረገው የገንዘብ መጠን በግብር ከፋዩ የሂሳብ መዝገብ ከተሰረዘው እዳ መጠን መብለጥ የለበትም
    እዳውን ለማስመለስ የህግ እርምጃ ተወስዶ እቃው ሳይመለስ ሲቀር
    የመዝናኛ ወጪ
    የማዕድን ማውጣት እና ፍለጋ፤ የማኑፋክቸሪንግ፣ የግብርናና ሆርቲካልቸር ስራ ላይ የተሰማራ ቀጣሪ ለተቀጣሪው በነፃ የሚያቀርበው የምግብ እና መጠጥ ዋጋ በወጪ የሚያዘው በ1 ወር የሚያወጣው ወጪ በወሩ ለተቀጣሪዎቹ ካወጣው አጠቃላይ የደመወዝ ወጪ ከ30% ባልበለጠ መጠን ብቻ ነው፡፡
    ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች ወይም ሌሎች የምግብ አገልግሎት የሚያቀርቡ ተቋማት ውስጥ ለተሰማሩ ሰራተኞች ለተቀጣሪዎች የሚያቀርቡት የምግብ እና መጠጥ ወጪ ተቀናሽ የሚያደርገው በ1 ወር የወጣው ወጪ በወሩ ለተቀጣሪዎቹ ከወጣው አጠቃላይ የደመወዝ ወጪ 20% ያልበለጠ መጠን ብቻ ነው፡፡
    የሚፈቀደው የመጠጥ ወጪ የአልኮልን ይዘት ያላውን አይጨምርም
    የምግብ አገልግሎቱ የሚቀርበው በድርጅቱ ከሆነ የግብዓት ወጪዎች በደረሰኝ/በግዢ ማስረጃ መሆን አለበት
    የምግብ አገልግሎቱ የሚቀርበው በአቅራቢዎች ከሆነ፤ ውል ሊኖር ይገባል፤አገልግሎቱ ስለመገኘቱ ማረጋገጫ ሊቀርብ ያስፈልጋል፤ እንዲሁም የተከፈለበት ደረሰኝ ሊቀርብ ይገባል
    የማዕድን ማውጣት እና ፍለጋ፤ የማኑፋክቸሪንግ፣ የግብርናና ሆርቲካልቸር ስራ ላይ የተሰማራ ቀጣሪ ከከተማ ርቆ(ቢያንስ 20ሺ ነዋሪ ካለው የከተማ ወሰን 30ኪ.ሜርቆ የሚገኝ የስራ ስፍራ) በሚገኝ ቦታ ለተመደበው ተቀጣሪ በነፃ ለሚያቀርበው የማረፍያ ቤት ያወጣው ወጪም ይቀነስለታል
    የማስታወቂያ ወጪ
    የንግድ ምርቱን /አገልግሎቱን ለማስተዋወቅ በተለያዩ ዝግጅቶች ላይ የሚያደርገው የማስተዋወቅ ስራ በገንዘብ /በምርት /በአገልግሎት የሚፈጽመው ክፍያ በወጪ ተቀናሽ የሚያዘው ከጠቅላላ ገቢው 3% ባልበለጠ መጠን ብቻ ነው፡፡
    ለመገናኛ ብዙሀን /ለማስታወቂያ ድርጅት የሚከፍለው ክፍያ ሙሉ በሙሉ በወጪ ተቀናሽነት ይያዛል
    ለበጎ አድራጎት ዓላማ
    ለኢትየጲያ በጎ አድራጎት ድርጅት/ማህበራት (አዋጅ 24/1/ሀ)
    ለመንግስት (ፌደራል፣ክልል፣ አዲሰ አበባና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር) ለልማት፣ሉዓላዊነት፣ ሰው ሰራሽ/የተፈጥሮ አደጋ/ወረርሽኝ የሚውል (አዋጅ 24/1/ለ)
    ግብር ከፋዩ ራሱ ለሚያካሂደው የበጎ አድራጎት ተግባር ለሚያወጣው ውጪ ተፈፃሚ ይሆናል (ደንብ 33/1)
    ከታክስ ከፋይ ሠራተኞ ውጪ ለሌሎች ተረጂዎች የሚሰጥ የትምህርት፣ የጤና፣ የአካባቢ ጥበቃ ወይም ለሌላ ሰብዓዊ እርዳታ (ደንብ 33/3)
    ለበጎ አድራጎት ዓላማ የተደረገ ስጦታ ግብር የሚከፈልበት ገቢው 10% ባልበለጠ
    ምንጮች
    የገቢ ግብር አዋጅ 979/2008/አንቀጽ22፣
    23የወለድ ወጪ፣
    24 ለበጎ አድራጎት አላማ የሚደረጉ ስጦታዎች፣
    የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 410/2009
    ስለተቀናሽ ወጪዎች መመሪያ ቁጥር 5/2011

ความคิดเห็น •