How to calculate OVERTIME/የትርፍ ሥራ ሰዓት የOT አከፋፈል የትርፍ ሰዓት ሥራ የሚፈቀድባቸው ሁኔታዎች

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 8 พ.ค. 2024
  • ሀ) ከንጋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት ለሚሠራ የትርፍ ሰዓት ሥራ ለመደበኛ ሥራ በሰዓት የሚከፈለው ደመወዝ በ1.5 ተባዝቶ፤
    ለ) ከምሽቱ 4 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት ለሚሠራ የትርፍ ሰዓት ሥራ ለመደበኛ ሥራው በሰዓት የሚከፈለው ደመወዝ በ1.75 ተባዝቶ፤
    ሐ) በሳምንት የዕረፍት ቀን የሚሠራ የትርፍ ሰዓት ሥራ ለመደበኛው ሥራው በሰዓት የሚከፈለው ደመወዝ በ2 ተባዝቶ፣
    መ) በሕዝብ በዓላት ቀን ለሚሠራ የትርፍ ሰዓት ሥራ ለመደበኛ ሥራው በሰዓት የሚከፈለው ደመወዝ በሁለት ተኩል ተባዝቶ፣
    ሠራተኛው በሕዝብ በዓል ቀን ከሠራ በሰዓት የሚያገኘው ክፍያ በ2 ጊዜ ተባዝቶ በበዓሉ ቀን ለሠራበት ለእያንዳንዱ ሰዓት ይከፈለዋል (አንቀጽ 75)፡፡ የሥራ ሰዓት ጣሪያ
    የማንኛውም ሠራተኛ መደበኛ የሥራ ሰዓት በቀን ከ8 ወይም በሣምንት ከ48 ሰዓት አይበልጥም፡፡
    3 አይነት መደበኛ የስራ ሰዓታት አሉ፡-
    ከሰኞ - አርብ 8*5*4 =160 ሰዓታት
    ከሰኞ - አርብ እና ቅዳሜ ግማሽ 8*5+4*4 =176 ሰዓታት
    ከሰኞ - ቅዳሜ 8*6*4 =192 ሰዓታት
    የትርፍ ሰዓት ሥራ የሚፈቀድባቸው ሁኔታዎች
    ማንኛውም ሠራተኛ የትርፍ ሰዓት ሥራ እንዲሠራ አይገደድም፡፡ ሆኖም አሠሪው ሌላ አማራጭ መንገድ ሊኖረው አይችልም ተብሎ ሲገመት፤ እና:-
    ሀ) አደጋ ሲደርስ /የሚደርስ መሆኑ ሲያሰጋ፤
    ለ) ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ ሲያጋጥም፤
    ሐ) በአስቸኳይ መሰራት ያለበት ሥራ ሲያጋጥም፤
    መ) በማያቋርጥና ተከታታይ ሥራ ላይ ከሥራ የቀሩ ሠራተኞችን ለመተካት፤
    በአስቸኳይ የሚሠራ ሥራ ሲያጋጥም የሚሰራው የትርፍ ሰዓት ሥራ በቀን ከ4፣ በሳምንት ከ12 ሰዓት መብለጥ የለበትም፡፡
    የOT አከፋፈል
    በአዋጅ “ወጣት ሠራተኛ” ማለት ዕድሜው 15 ዓመት የሞላውና 18 ዓመት ያልበለጠው ግለሰብ ነው፡፡
    እድሜያቸው ከ15 ዓመት በታች የሆኑትን መቅጠር ክልክል ነው፡፡
    የወጣት ሠራተኞች መደበኛ የሥራ ሰዓት በቀን ከ7 ሰዓት መብለጥ የለበትም፡፡
    91. የሌሊትና የትርፍ ሥራ ሰዓት
    ማንኛውንም ወጣት ሠራተኛ:-
    ከምሽቱ 4 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት በሚሰራ ሥራ ላይ፤
    በትርፍ ሰዓት ሥራ ላይ፤
    በሳምንት የዕረፍት ቀን፤ ወይም
    በሕዝብ በዓላት ቀን ማሠራት ክልክል ነው፡፡
    ነፍሰጡር የሆነች ሠራተኛን ከምሽቱ 4 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት ባለው ጊዜ እንዲሁም የትርፍ ሰዓት ማሰራት የተከለከለ ነው፡፡
    OT
    Necessary information to calculate OT
    Basic salary
    OT hours
    Rate (normal day, weekend & holyday)
    Working hours
    Normal working hours (3) according to memorandum of association of the company
    1. Monday - Friday
    8*5=40
    40*4=160
    2. Monday - Friday & Saturday 1/2
    8*5+4=44
    44*4=176
    3. Monday - Saturday
    8*6=48
    48*4=192
    Bruk Salary…… 30,000
    Work hour 2:30 - 6:30 & 7:30 - 11:30 and Saturday 1/2
    Formula: - rate*basic salary*OT hours
    Working hours
    A. 8/5/2024 ….11:30 - 8:00 ………………….. (OT hours=2.5)
    1.5*30,000*2.5 = 639.20
    176
    B. 28/5/2024….. 2:30 - 6:30 (weekend) (OT hours=4)
    2*30,000*4 = 1,363.64
    176
    C. 29/5/2024……7:30 - 1:30 (holyday) (OT hours=6)
    c1. 7:30 - 11:30 (OT hours=4)
    2*30,000*4 = 1,363.64
    176
    c2. 11:30 - 1:30 (OT hours=2)
    2.5*30,000*2 = 852.27
    176
    Total OT = 639.20+1,363.64+1,363.64+852.27 = 4,218.75
    Tax calculation
    Taxable income= 30,000+4,218.75
    = 34,218.75
    Tax=34,218.75*.35-1,500
    =10,476.56
    Net income=34,218.75-10,476.56
    =23,742.19

ความคิดเห็น • 5

  • @ashenafikassa5366
    @ashenafikassa5366 2 หลายเดือนก่อน +1

    ጎበዝ

    • @BekoTube-BM
      @BekoTube-BM  2 หลายเดือนก่อน

      Thank u Ashu

  • @Diamond21192
    @Diamond21192 2 หลายเดือนก่อน

    ጥያቄ አለኝ ??? ለምሳሌ ደሞዙ 7000 ትራንስፖርት አበል 2200/600 ቢሆን ጠቅላላ ደሞዙ ስንት ነው።። የስራ ልምድ ሲፃፍ በየትኛው ነው የሚፃፈው??

    • @BekoTube-BM
      @BekoTube-BM  2 หลายเดือนก่อน

      በህጉ መሰረት ደመወዝ የሚባለው መደበኛ ክፍያ ነው (አንቀጽ 53/1)። ነገር ግን አሰሪው ፈቃደኛ ከሆነ ሊጽፍ ይችላል። የትራንስፖርት እና ሌሎች ክፍያዎች ደመወዝ ዉሰጥ አይካተቱም በአንቀጽ 53/2 መሠሰት

    • @Diamond21192
      @Diamond21192 2 หลายเดือนก่อน

      @@BekoTube-BM 🙏🙏🙏🙏🙏 አመሠግናለሁ እህቴ።።😍😍