DEDUCTIBLE EXPENSE 2 ተቀናሽ የሚደረጉ ወጪዎች ኪሣራ, የእርጅና ተቀናሽ

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 5 มิ.ย. 2024
  • ኪሣራ, የእርጅና ተቀናሽ
    ኪሳራ ለማሸጋገርና በወጪነት ለመያዝ የሚፈቀደውም ለ2 የግብር አመታት ብቻ የደረሰ ኪሳራ ነው (ኮቪድ ወረርሽኝ )
    ኪሳራ ለማሸጋገር የሚቻለው ኪሳረው ከደረሰበት ዓመት ቀጥሎ ላሉት 5 ዓመታት ነው (በማዕድን/በነዳጅ ስራዎች እስከ 10 አመታት (አዋጅ 38/3))
    ኪሳራ ሊሸጋገር የሚችለው የሂሳብ መዝገብ ኦዲት የተደረገ እና በባለስልጣኑ ተቀባይነት ያገኘ ከሆነ ብቻ ነው (ደንብ 42/2) ነገር ግን የቀጣዩ የግብር አመት የታክስ ማስታወቂያ ማቅረቢያ ጊዜ ከመድረሱ በፊት የታክስ ባለስልጣኑ የግብር ከፋዩን የሂሳብ መዝገብ ኦዲት ማድረግ ያልቻለ እንደሆነ ኪሳራውን ሊያሸጋግር ይችላል (ደንብ 3/ለ)
    የሚሸጋገር ኪሳራ ከአንድ የግብር አመት በላይ ያጋጠመው ከሆነ ግብር ከፋዩ መጀመሪያ የገጠመው ኪሳራ በቅድሚያ ይቀነስለታል (ደንብ 42/1)
    ለረጅም ጊዜ የሚቆዩ ውሎች
    ከረጅም ጊዜ ውል ጋር ተያይዞ የሚያጋጥም ኪሳራ ተካክሶ እስከሚያልቅ ድረስ ወደኃላ ሊሸጋገር ይችላል (ደንብ 43)
    ለረጅም ጊዜ ከተደረገ ውል ጋር ተያይዞ በውሉ የመጨረሻ ዓመት ኪሳራ የደረሰበት እና ኪሳራውን እንዲያሸጋግር የተፈቀደለት ቢሆንም ኪሳራውን ማሸጋገር ያልቻለ ሆኖ በውሉ ዘመን መጨረሻ በኢትዮጲያ የንግድ ስራ መስራት ያቆመ እንደሆነ ይህ ግብር ከፋይ የደረሰበት ኪሳራ ወደ ኃላ ተመልሶ በዓምናው/አቻምናው የግብር ዓመት በተቀናሽነት እንዲያዝለት ይደረጋል
    የእርጅና ተቀናሽ
    ዋጋቸው የሚቀንስ ሃብቶች (tangible assets) እና ግዙፋዊ ሀልዎት ለሌላቸው ሀብቶች (intangible assets) የእርጅና ቅናሽ የሚደረግባቸዋል
    ከአንድ አመት በላይ የሚያገለግል
    ማንኛውም የንግድ ስራ ሀብት የተናጥል ዋጋ ከብር 2000 በታች ከሆነ በአንድ ጊዜ በወጪነት መያዝ አለበት
    በእርጅና /ጊዜው በማለፉ ምክንያት ዋጋው የሚቀንስ
    በከፊል/በሙሉ ገቢን ለማስገኘት ጥቅም ላይ የሚውል
    የእርጅና ቅናሽ የሚጀምረው ሀብቱ ገቢን ለማስገኘት ዝግጁ/አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት ቀን ነው
    ህንፃው በግብር ከፋዩ የተገነባ ከሆነ ለአገልግሎት ዝግጁ ከሆነበትና አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት ቀን አንስቶ ሲሆን ተቆጣጣሪ ባለስልጣኑ የህንፃ ግንባታው ስለመጠናቀቁ የምስክር ወረቀት ከተሰጠው በኃላ ነው
    የእርጅና ቅናሽ የሚሰላበት መሰረት ህንፃው የተሰራበት/የተገዛበት ዋጋየሚገልፅ ሰነድ በግብር ከፋዩ ማቅረብ ካልቻለ ባለስልጣኑ የተገዛበትን/የተሰራበትን የገበያ ዋጋ 70 በመቶ ለእርጅና መሰረት አድርጎ ይወስዳል
    ሀብቱ ለሌላ አላማ እስካልዋለ ድረስ ለኪራይ አገልግሎት ዝግጁ ያደረገ ከሆነ ሀብቱ ባይከራይም ለኪራይ አገልግሎት ጥቅም ላይ እንደዋለ ተቆጥሮ ከኪራይ በተገኘ ገቢ ላይ ግብር በሚሰላበት ጊዠ እንደወጪ ተቀናሽ ይደረግለታል
    በአይነት የካፒታል መዋጮ እና በውርስ የተገኘ ሀብት የእርጅና ቅናሽ የሚሰላው በሚተላለፍበት ጊዜ በነበረው የተጣራ የመዝገብ ዋጋ ነው
    በባል /በሚስት ስም የተመዘገበ ህንፃ ለግለሰብ ንግድ ስራ የዋለ እንደሆነ የእርጅና ተቀናሽ ሊፈቀድና የሚችለው ህንፃው ለንግድ ስራው አገልግሎት እንዲውል የእርጅና ተቀናሽ እንዲጠየቅበትና ህንፃው ሲሸጥ ተገቢውን ግብር እና ታክስ እንዲከፈልበት የባልና የሚስት የስምምነት ሰነድ ሲቀርብ ነው
    ሀብቱ የተገዛበት/የተሰራበት ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስ የግብአት ታክስ ተካክሶ ከነበረ እርጅና ከሚሰላበት ዋጋ ውስጥ አይካተትም
    በታክስ ከፋዩ ስም ያልተመዘገበ ሀብት ተቀናሽ አይፈቀድም
    ሀብቱ ከፊል ለሆነ የአመቱ ጊዜ አገልግሎት ላይ ከዋለ የእርጅና ቅናሽ የሚታሰበው አገልግሎት ለሰጠበት ጊዜ ብቻ ነው
    በከፊል ገቢን ለማስገኘት በከፊል ለሌላ አገልግሎት የዋለ ሀብት የእርጅና ቅናሽ የሚሰላው ገቢውን ለማግኘት በዋለው መጠን ብቻ
    በከፊል ገቢን ለማስገኘት የሚጠቀምበትን ሀብት የእርጅና ተቀናሽ የሚሰላው ከጠቅላላው የህንፃ ስፋትና ዋጋ ለንግድ ስራው ጥቅም ላይ የዋለው መጠን ዋጋ ተለይቶ ካልቀረበ በወለሉ ስፋት መቶኛ በማስላት ዋጋው ተለይቶ መቅረብ አለበት (ለኪራይ ገቢ ግብርም ተፈፃሚ ይሆናል)
    ግብር ከፋዩ ለየቶ ካላቀረበ ከጠቅላላ የህንፃ ዋጋ ለንግድ ስራው የዋለውን የህንፃ ስፋት መጠን በማስላት ባለስልጣኑ በራሱ ወስኖ ተቀናሽ ያደርጋል
    በከፊል ገቢን ለማስገኘት የሚጠቀምበትን ሀብት ቢሸጠው ትርፍና ኪሳራው የሚሰላው ለገቢው አስተዋጾኦ ባደረገው ክፍፍል ይሆናል
    ተከራይ ከአከራዩ ጋርz ከገባው ውል ውጪ በገዛ ፈቃዱ የተከራየውን የንግድ ስራ ሀብት በራሱ ወጪ የሚያድስ፣ የሚጠግን/የሚያሻሽል ተከራይ ለእድሳት፣ ወጪ ከንግድ ስራ ገቢው ላይ ተቀናሽ ይደረግለታል (ደንብ)
    ግብር ከፋይ በአንድ የግብር አመት በሀብቱ ላይ ላደረግው የጥገና/ማሻሸያ ወጪ በግብር አመቱ የወጪ ተቀናሽ ይፈቀድለታል (ደንብ)፡፡ ነገር ግን የንግድ ሀብቱ በግብር አመቱ መጨረሻ ካለው የተጣራ የመዝገብ ዋጋ 20% ሊበልጥ አይችልም
    በአንድ የግብር አመት ዋጋው በሚቀንስ ሀብት ላይ የተደረገ የጥገና/የማሻሸያ ወጪ ከሀብቱ የተጣራ የመዝገብ ዋጋ 20% የሚበልጥ ከሆነ የጥገና/የማሻሸያው ሙሉ ወጪ በሃብቱ የተጣራ የመዝገብ ዋጋ ላይ ይጨመራል
    ግብር ከፋዩ ግንኙነት ካለው ሰው ላገኘው እና በአስተላላፊው ሙሉ የእርጅና ቅናሽ ለተደረገበት ሀብት የእርጅና ቅናሽ ማድረግ አይችልም
    ግንኙነት ላላቸው ሰዎች የእርጅና ቅናሽ ያልጨረሰ ሀብት የተላለፈበት ዋጋ ከተጣራ የመዝገብ ዋጋ የሚበልጥ ከሆን እርጅና የሚሰላው በተጣራ የመዝገብ ዋጋ ነው
    በታክስ የተፈቀዱ ዘዴዎች
    ቀጥተኛ የእርጅና ቅናሽ ዘዴ (straight line)
    ዋጋው እየቀነሰ የሚሄድ የእርጅና ቅናሽ ዘዴ (diminishing/declining)
    ቀጥተኛ የእርጅና ቅናሽ ዘዴ
    ምሳሌ የግሪንሀወስ ዋጋ 20 000 000
    20 000 000*0.1
    የእርግና ተቀናሽ (depreciation exp.)=2 000 000
    ለከፊል አመት አገልግሎት
    ጥቅምት30 ፣ 8ወራት አገልግሎናል
    8/12*20 000 000*0.1
    =1 333 333.33
    ዋጋው እየቀነሰ የሚሄድ የእርጅና ቅናሽ ዘዴ
    ዋጋው እየቀነሰ በሚሄድ የእርጅና ቅናሽ ዘዴ መሰረት የእርጅና ቅናሽ ምጣኔው በአመቱ መጀመሪያ ባለው የሀብቱ የተጣራ የመዝገብ ዋጋ ይሰላል (ደንብ)
    ቀሪው ዋጋ ከ2000 ብር የማይበልጥ ከሆነ በአንድ ጊዜ ወጪ ይያዛል (ደንብ)
    ምሳሌ ኮምቲውተር ዋጋው 200 000
    የመጀመሪያ አመት
    የእርጅና ተቀናሽ (depreciation exp.) 200 000*.25 = 50 000
    BV 200 000 - 50 000=150 000
    ሁለተኛ አመት
    የእርጅና ተቀናሽ (depreciation exp.) 150 000*.25= 37 500
    BV 150 000 - 37 500 =112 500
    ምንጮች
    የታክስ አስተዳደር አዋጅ 983/2008/አንቀጽ4/3ና4
    የገቢ ግብር አዋጅ 979/2008
    የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ 410/2009
    የገንዘብ ሚኒስተር መመሪያ 5/2011
    የኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ በታክስ ከፋዩ የስራ እንቅስቃሴ ላይ የደረሰውን ጫና ለመቀነስ የወጣ መመሪያ ቁጥር 65/2012

ความคิดเห็น •