3ኛ ትምህርት : የእግዚአብሔር ፍቅር እና ፍትሕ - እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት
ฝัง
- เผยแพร่เมื่อ 6 ก.พ. 2025
- ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡- ሉቃ 15፡11-32፣ ሶፎ. 3፡ 17፣ ኤፌ. 5፡25-28፣ ኢሳ. 43፡4፣ ሮሜ. 8፡1፣ ሮሜ. 5:8፣ ማር. 9:17-29።
የመታሰቢያ ጥቅስ፡ አምላክሽ እግዚአብሔር በመካከልሽ ታዳጊ ኃያል ነው፤ በደስታ በአንቺ ደስ ይለዋል፥ በፍቅሩም ያርፋል፥ በእልልታም በአንቺ ደስ ይለዋል” (ሶፎ. 3፡17)።
እስቲ የሚከተለውን ሁኔታ ያስቡ፡- የአምስት ዓመት ልጅ በአባቶች ቀን በደንብ ያልተጠቀለለ ስጦታ ይዞ ወደ አባቱ ይመጣል። በደስታ ስጦታውን ለአባቱ ይሰጠዋል። አባትየው “ልጄ፣ ስለ ስጦታህ ግድ የለኝም። እንዲያውም እኔን የሚያስደስት ምንም ነገር ልትሰጠኝ አትችልም። ልትሰጠኝ የምትችለው ሁሉ፣ ራሴ እገዛዋለሁ፣ የምትሰጠኝ ማንኛውም ነገር በገንዘቤ የተገዛ ወይም ከከፈልኩባቸው ቁሳቁሶች የተሰራ ነው። ስለዚህ ስጦታህ ለራስህ ይሁንልህ።
አያስልፈልገኝም። ለማንኛውም ግን እወድሃለሁ” እንዳለው ያስቡ። እህ!
የዚህ አባት ምላሽ ምን ይመስልዎታል? “ጨካኝ”፣ “ቀዝቃዛ” እና “ስሜት- የለሽ” የሚሉት ቃላት ወደ አእምሯችን ይመጣሉ። እግዚአብሔር እንደዚህ ነው ለእኛ ምላሽ የሚሰጠን? በእርግጥ እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት እንችላለን? ለመገመት አስቸጋሪ ቢሆንም - የወደቅን፣ በኃጢአት የተጨማለቅን እና ለክፋት የተጋለጥን ብንሆንም እንኳን - አዎን እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት እንችላለን! በሌላ አነጋገር፣ እግዚአብሔር እኛን ወይም የምናመጣቸውን ስጦታዎቻችንን እንደዚያ አባት አይመለከታቸውም። በተቃራኒው፣ በክርስቶስ ብቻ እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት እንችላለን።