ไม่สามารถเล่นวิดีโอนี้
ขออภัยในความไม่สะดวก

ህወሓት “በልዩ ሁኔታ” እንዲመዘገብ፤ የፍትሕ ሚኒስቴር ለምርጫ ቦርድ ጥያቄ አቀረበ

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 26 มิ.ย. 2024
  • ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በፓለቲካ ፓርቲነት “በልዩ ሁኔታ” መመዝገብ እንዲችል ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥያቄ ቀረበ። ምርጫ ቦርድ ጥያቄው ከፍትሕ ሚኒስቴር እንደቀረበለት ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አረጋግጧል።
    ብሔራዊው ምርጫ ቦርድ፤ ህወሓት “ኃይልን መሠረት ያደረገ የአመጻ ተግባር ላይ መሳተፉን” እንዳረጋገጠ በመጥቀስ የፖለቲካ ፓርቲውን “ህጋዊ ሰውነት” የሰረዘው በጥር 2013 ዓ.ም ነበር። ቦርዱ በወቅቱ ባስተላለፈው ውሳኔ፤ የህወሓት ኃላፊዎች “በፓርቲው ስም መንቀሳቀስ እንደማይችሉ” እገዳ መጣሉም ይታወሳል።
    የህወሓት ተወካዮች ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ጋር በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የግጭት ማቆም ስምምነት በጥቅምት 2015 ከተፈራረሙ ከመንፈቅ በኋላ፤ ቦርዱ ያስተላለፈውን ውሳኔ እንዲያነሳ ፓርቲው በደብዳቤ ጥያቄ አቅርቦ ነበር። ምርጫ ቦርድ፤ ህወሓት ያቀረበው የህጋዊ ሰውነት የማስመለስ ጉዳይ “በህግ የተደገፈ ሆኖ አለመገኘቱን” በመጥቀስ ጥያቄውን “አለመቀበሉን” በግንቦት 2015 በይፋ አስታውቋል። (ኢትዮጲያ ኢንሳይደር)
    ተጨማሪውን ለማንበብ ይሄን ሊንክ ይጫኑ ethiopiainside...
    -------------------------------------------------------------------------------------------
    የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ትኩስ ዜናዎችን እና ወቅታዊ ዘገባዎችን ለመከታተል፦
    ድረ ገጽ ፦ ethiopiainsider...​
    ፌስቡክ ፦ / ethiopiainsider
    ትዊተር (ኤክስ) ፦ / ethiopiainsider
    ቴሌግራም፦ t.me/EthiopiaI...
    ቲክቶክ፦ / ethiopiainsider

ความคิดเห็น •