ไม่สามารถเล่นวิดีโอนี้
ขออภัยในความไม่สะดวก

ዓመታዊ “የስራ ክንውን ሪፖርት አላቀረቡም” የተባሉ 205 የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ፈረሱ

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 18 ส.ค. 2024
  • ለሶስት ተከታታይ ዓመት የስራ ክንውን እና የኦዲት ሪፖርት ያላቀረቡ 205 የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች መፍረሳቸውን እነርሱን የመከታተል እና የመቆጣጠር ስልጣን የተሰጠው ባለስልጣን መስሪያ ቤት አስታወቀ። ከፈረሱት ድርጅቶች መካከል የኢትዮጵያ ጠበቆች ማህበር፣ የኢትዮጵያ የግሉ ዘርፍ ሃኪሞች ማህበር፣ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ሬድዮ ጣቢያዎች ማህበር እና ሚዩዜክ ሜይ ዴይ ኢትዮጵያ ይገኙበታል።
    የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ስራቸውን በህግ አግባብ ማከናወናቸውን ለማረጋገጥ፤ አስፈላጊውን ክትትል እና ቁጥጥር የማድረግ ስልጣን በአዋጅ የተሰጠው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ነው። ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን ዓመታዊ የስራ እና የገንዘብ እንቅስቃሴ ሪፖርት የመመርመር ስልጣንም በ2011 ዓ.ም. በተሻሻለው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ተሰጥቶታል።
    በዚሁ አዋጅ መሰረት፤ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የእያንዳንዱን በጀት ዓመት ዋና ዋና ክንዋኔዎችን የሚያሳይ ሪፖርት “የበጀት ዓመቱ ባለቀ በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ” ለባለስልጣኑ ማቅረብ አለባቸው። ድርጅቶቹ በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ ውስጥ ሪፖርት ካላቀረቡ፤ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የድርጅቶቹን ህልውና ለማረጋገጥ በጋዜጣ ጥሪ እንደሚያደርግም በአዋጁ ላይ ተቀምጧል። (ኢትዮጲያ ኢንሳይደር)
    🔴 ተጨማሪውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ:- ethiopiainside...
    -------------------------------------------------------------------------------------------
    የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ትኩስ ዜናዎችን እና ወቅታዊ ዘገባዎችን ለመከታተል፦
    ድረ ገጽ ፦ ethiopiainsider...​
    ፌስቡክ ፦ / ethiopiainsider
    ትዊተር (ኤክስ) ፦ / ethiopiainsider
    ቴሌግራም፦ t.me/EthiopiaI...
    ቲክቶክ፦ / ethiopiainsider

ความคิดเห็น •