3ኛ ትምህርት : የማርቆስ መጽሐፍ - ተቃርኖዎች
ฝัง
- เผยแพร่เมื่อ 30 ม.ค. 2025
- ለዚህ ሳምንት ትምህርት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ:- ማር. 2:1-3:6፣ ሚክያስ 6:6-8፣ 1ኛ ሣሙ. 21:1-6፣ ማር. 3:20-35፣ ሉቃስ 12:53፣ ሉቃስ 14:26።
የመታሰቢያ ጥቅስ:- “ደግሞ፦ ሰንበት ስለ ሰው ተፈጥሮአል እንጂ ሰው ስለ ሰንበት አልተፈጠረም፤ እንዲሁም የሰው ልጅ ለሰንበት እንኳ ጌታዋ ነው አላቸው።” (ማር. 2:27፣ 28)።
ማርቆስ 2:1-3:6 የኃይማኖት መሪዎች ከሚያስተምሩት ትምህርት ጋር በማነጻጸር የኢየሱስን ትምህርት የሚገልጹ ታሪኮችን ይዟል። እያንዳንዱ ቀጣይ ታሪክ አስቀድሞ ከነበረው ታሪክ ጋር ግንኙነት እንዲኖረው ተደርጎ በተለየ ሁኔታ ርዕስ ባለው ንጽጽር ቀርቧል።