#labourlaw

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 14 ต.ค. 2024
  • አዋጁ የማይሸፍናቸው, የስራ ውል የሚቆይበት ጊዜ, የሙከራ ጊዜ, ደመወዝ, የአሰሪ ግዴታዎች, ሴት እና, ወጣት ሰራተኞች, ውል የሚረጥበት ጊዜ, የስራ ክርክር
    የአሰሪና ሰራተኛ ህግ ለሰራተኛው ያደላ ነው
    ሰራተኛው ቢስማማም በአዋጁ የተሰጡትን መብቶች አያሳጣውም
    ለምሳሌ፡- የአመት ፈቃድ 16-20፣25…
    በቀን 8-7፣6፣5፣4…
    በሳምንት 48-40፣30፣20…
    በሳምንት 1ቀን እረፍት፣2፣3…
    ሰራተኛው ከስራው ከህግ ውጪ ሲባረር ወደ ስራው ለመመለስ የመጠየቅ መብቱ እስከ 3ወር ድርስ ብቻ ነው አንቀጽ 63/2
    ክፍያ (ደመወዝ፣ የአመት ፈቃድ፣ የትርፍሰዐት ክፍያ፣ የአገልግሎት ክፍያ፣ ካሳ፣ አሰሪው መክፈል ያለበት ቅጣት…) በ6ወር ጊዜ ውስጥ አንቀጽ 63/3
    የስራ ልምድ እስከ 10አመት
    በአዋጁ የማይሸፈኑ(3)
    ለአስተዳደግ ሲባል፣ ለሕክምና /ከሕመም ለመዳን /እንደገና ለመቋቋም ሲሆን፤
    ሠራተኛው የሥራ መሪ (ፖሊሲዎችን የማውጣትና የማስፈፀም ሥልጣን ያለው ወይም ሠራተኛን የመቅጠር፣ የማዘዋወር፣ የማገድ፣ የማሰናበት /የመመደብ፣ የመወሰን ሥልጣን ያለው ግለሰብ ሲሆን፣ የሕግ አገልግሎት ኃላፊን)፤ (የሰራተኛ ማህበር) 350ታክስ
    የግል አገልግሎት ቅጥር (ምግብ ዝግጅት፣ ጽዳት፣ ሞግዚትነት፣ የጥበቃ ሥራ፣ ሹፌርነት፣ አትክልተኝነት)፤
    በልዩ ሕግ የሚተዳደሩ (ጦር ኃይል፣ ፖሊስ፣ የመንግሥት አስተዳደር ሠራተኞች፣ የፍርድ ቤት ዳኞች፣ ዐቃቢያነ ሕግ)፤
    የውጭ ዲኘሎማቲክ ሚስዮኖች ወይም ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ከኢትዮጵያዊያን ጋር በሚመሰርቱት የሥራግንኙነቶች
    የሃይማኖት /የበጎ አድራጎት ድርጅቶች በሚመሠርቱት የሥራ ግንኙነቶች
    የሥራ ውል የሚቆይበት ጊዜ
    በአንቀጽ 10 ከተገለጹት በስተቀር ማንኛውም የሥራ ውል ላልተወሰነ ጊዜ እንደተደረገ ይቆጠራል
    ለተወሰነ ጊዜ /ለተወሰነ ሥራ የሚደረግ የሥራ ውል (አንቀጽ 10)
    11 የሙከራ ጊዜ
    በሥራ ቦታ ተስማሚ መሆኑን ለመመዘን ለሙከራ ጊዜ መቅጠር ይቻላል
    ሠራተኛው ቀድሞ ይሠራው በነበረ ሥራ እንደገና በአሠሪው ቢቀጠር ለሙከራ ጊዜ ሊቀጠር አይችልም
    የሙከራ ጊዜ እንዲኖር ተዋዋይ ወገኖች ሲስማሙ ውሉ በጽሑፍ መደረግ አለበት
    የሙከራ ጊዜውም ሥራ ከጀመረበት ቀን አንስቶ ከ60 የሥራ ቀናት ሊበልጥ አይችልም
    ሠራተኛው ለሥራው ተስማሚ አለመሆኑ ሲረጋገጥ አሠሪው ያለ ማስጠንቀቂያ፤ የሥራ ስንብት ክፍያና ካሣ መክፈልም ሳይገደድ የሥራ ውሉን ሊያቋርጥ ይችላል
    በሙከራ ላይ ያለን ሰራተኛ ማባረር የሚቻለው ስራው ተገምግሞ ዝቅተኛ ውጤት ካስመዘገበና ለቦታው ብቁ ካልሆነ ነው፡፡ ያለግምገማ ማባረር አይቻልም (ላላለቀው የሙከራ ጊዜ ካሳ ይከፍለዋል)
    በሙከራ ላይ ያለ ሠራተኛ ያለማስጠንቀቂያ ሥራውን ሊለቅ ይችላል፡፡
    የተወሰነ ሥራ እስከሚያልቅበት ጊዜ ድረስ፤
    በፈቃድ፣ በሕመም /በሌላ ማናቸውም ምክንያት ለጊዜው ቀሪ የሆነ ሠራተኛን ለመተካት፤
    የሥራ ብዛት በሚያጋጥምበት ጊዜ ሥራን ለማቃለል፤
    በሕይወት ላይ አደጋ /በንብረት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ለመከላከል አጣዳፊ ሥራዎችን ለመሥራት፣
    በንብረት ላይ የደረሰውን ጉድለትና ብልሽት ለማደስ፤
    አልፎ አልፎ የሚሰራ ሥራ፤
    የወቅት ሥራ ለመሥራት ፤
    የውሉ ጊዜ አልቆ ስራው ካላለቀ የስራ ውሉ አይቋረጥም
    ደመወዝ
    ዝቅተኛ ደመወዝ የሚወስን የደመወዝ ቦርድ (የመንግሥት፤ የአሠሪና ሠራተኛ ተወካዮች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት) የሃገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት፤ የሥራ ገበያ ሁኔታ እያስጠና አንቀጽ 55/2
    የደመወዝ ቦርድ ስለሚቋቋምበትና ስለተግባርና ኃላፊነቱ ስለሚወሰንበት ሁኔታ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ይደነገጋል
    ደመወዝ በአይነት ሊከፈል ይችላል (30% አንቀጽ 55) ድረስ ብቻ አሰሪውና ሰራተኛው ከተስማሙ
    ሠራተኛው በጽሁፍ ስምምነቱን ካልገለጸ በቀር በአንድ ጊዜ ከሠራተኛው ደመወዝ ላይ በአጠቃላይ ሊቆረጥ የሚችለው የገንዘብ መጠን በምንም አኳኋን ከወር ደመወዙ 1/3 መብለጥ የለበትም፡፡
    12 የአሠሪ ግዴታዎች
    ለሠራተኛው በሥራ ውሉ መሠረት ሥራ የመስጠት
    ሠራተኛው ከደመወዙ የተወሰነ መቶኛ እየተቀነሰ ለሠራተኛ ማኅበር መዋጮ ገቢ እንዲደረግለት በጽሁፍ ሲያመለክት
    የሥራ ውል በሚቋረጥበት /ሠራተኛው በሚጠይቅበት በማናቸውም ጊዜ ሠራተኛው
    ሲሰራ የነበረውን የሥራ ዓይነት፣
    የአገልግሎት ዘመኑንና
    ሲከፈለው የነበረውን ደመወዝ የሚያሳይ የምስክር ወረቀት ለሠራተኛው ያለክፍያ የመስጠት፤
    ሴት ሰራተኞች 87
    ሴት ሠራተኛ በቅጥር፣ በደረጃ ዕድገት /በሌላ ማናቸውም የጥቅማ ጥቅም ውድድር ከወንድ ጋር እኩል የሆነች እንደሆነ ቅድሚያ ይሰጣታል።
    ለሴቶች ከባድ ወይም ለጤናቸው ጎጂ ናቸው ተብለው ሚኒስቴሩ በሚዘረዝራቸው ሥራዎች ላይ ሴቶችን ማሠራት የተከለከለ ነው፡፡
    ነፍሰጡር የሆነች ሠራተኛን ከምሽቱ 4 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት ባለው ጊዜ እና የትርፍ ሰዓት ማሰራት የተከለከለ ነው፡፡
    ነፍሰጡር የሆነች ሠራተኛ የምትሰራው ሥራ ለራሷም ሆነ ለጽንሱ ጤንነት አደገኛ መሆኑ በሐኪም ሲረጋገጥ ወደ ሌላ የሥራ ቦታ ተመድባ መሥራት አለባት፡፡
    ነፍሰጡር የሆነች ሠራተኛ እወልዳለሁ ብላ ከገመተችበት ቀን በፊት የ30 ተከታታይ ቀናት የቅድመ-ወሊድ ፈቃድ፣ እንዲሁም ስትወልድ ከወለደችበት ቀን ጀምሮ ለ90 ተከታታይ ቀናት የድህረ-ወሊድ ፈቃድ ከክፍያ ጋር ይሰጣታል፡፡
    ሠራተኛዋ ከመውለዷ በፊት የወሰደችው የ30 የሥራ ቀናት የቅድመ፣ ወሊድ ፈቃድ ሲያልቅ ካልወለደች እስከምትወልድበት ቀን ድረስ የህክምና እረፍት ልታገኝ ትችላለች፡፡ የ30 የሥራ ቀናት የቅድመ-ወሊድ ፈቃዷ ሳያልቅ ከወለደች 90 የሥራ ቀናት የድህረ-ወሊድ ፈቃዷ ይጀምራል፡፡
    ማንኛውንም ወጣት ሠራተኛ 89
    ከሥራው ጠባይ /ሥራው ከሚከናወንበት ሁኔታ ሕይወታቸውን /ጤንነታቸውን ለአደጋ በሚያጋልጥ ሥራ ላይ ወጣት ሠራተኞችን ማሠራት ክልክል ነው፡፡
    በትርፍ ሰዓት ሥራ
    ከምሽቱ 4 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት በሚሰራ ሥራ ላይ
    በሳምንት የዕረፍት ቀን፤
    በሕዝብ በዓላት ቀን ማሠራት ክልክል ነው፡፡
    የሥራ ግንኙነት ስለማቋረጥ
    በአሠሪው አነሳሽነት (በህግና ከህግ ውጪ) ከህግ ውጪ አንቀጽ 26/2 ሰራተኛው ከስራው ሲባረር የጡረታ ተጠቃሚ ቢሆንም ካሳ ይከፈለዋል
    በሠራተኛው አነሳሽነት
    በሕግ በተደነገገው መሠረት (ለተወሰነ ስራ የተደረገ ውል ስራው ሲያልቀ፣ በህመም፣ በሞት፣ በጡረታ፣በመክሰሩ/በሌላ ለዘለቄታው ከተዘጋ(እዳ)፣ የአካል ጉዳት ሲደርስበት) ማስጠንቀቂያ አያስፈልገውም
    በኅብረት ስምምነት /በተዋዋይ ወገኖች በሚደረግ ስምምነት ይሆናል፡፡ ማስጠንቀቂያ አያስፈልገውም
    የስራ ስንብት ክፍያ ጠቅላላው ክፍያ ከሠራተኛው የ12 ወራት ደመወዝ መብለጥ የለበትም፡፡
    ያለማስጠንቀቂያ በአንቀጽ 31ሠራተኛ የስራ ውሉን ካፈረሰ ለአሠሪው ካሣ (የ1ወር ደመወዝ) ይከፍላል፡፡
    የአንድ ድርጅት ከሌላው ጋር መቀላቀል /መከፋፈል /የባለቤትነት መብት ወደ ሌላ መተላለፍ የሥራ ውልን አያቋርጠውም (አንቀጽ 23/2)፡፡
    የስራ ክርክር
    በቦርድ (ከግለሰብ ያለፈ ጉዳይ ሲሆን) ጉዳዩን ለጊዜው የሚመለከተው አንድ ሰራተኛን ቢሆንም
    በፍርድ ቤት (ጉዳዩ የሚጎዳው 1ግለስብን ብቻ ሲሆን)

ความคิดเห็น • 9

  • @belabela1475
    @belabela1475 4 หลายเดือนก่อน

    ለመጀመሪያ ጊዜ አየሁሽ። በጣም አሪፍ ነው።።በጥያቄ ልጀምር አገልግሎትና ሰርቪስ ልዩነታቸውን?? ማተሚያ ቤቶች ምኑ ውስጥ ነው የሚካተቱት አገልግሎት ወይስ ሰርቪስ??? ለምን??

  • @AzmerawBayih
    @AzmerawBayih 3 หลายเดือนก่อน

    ይሄ ነገር ለመምህራን ይሰራል የአመት ፈቃድ አለ!

  • @Diamond21192
    @Diamond21192 4 หลายเดือนก่อน +1

    አሠሪና ሠራተኛ ያቀረብሽው እጅግ ጠቃሚ ነገር ነው።🙏🙏🙏 ደሞዝ, 7000 የቤት አበል 5000 የበረሐ አበል 3000, የምግብ እና መጠጥ1000 በብር ቢታሰብለት የስራ ግብር ይቆረጥበታል ወይ??? ስራ ግብር የማይቆረጥባቸው ምን ምን ናቸው??

    • @BekoTube-BM
      @BekoTube-BM  4 หลายเดือนก่อน

      አመሰግናለው🙏

    • @BekoTube-BM
      @BekoTube-BM  4 หลายเดือนก่อน

      ደመወዝና የቤት አበል ያለገደብ ታክስ ይሰላባቸዋል::
      የበረሓ አበል እና የምግብና የመጠጥ አበል በገደብ ታክስ ይሰላባቸዋል በገቢ ግብር ነፃ የተደረጉ ገቢዎች አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 1/2011 መሰረት፡፡ የበረሓ አበል ለማስላት ደረጃውን ማወቅ አለብን (የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ባወጣው መመሪያ መሠረት 1ኛ ደረጃ ቆላ ከሆነ ከደመወዙ 40%፣ 2ኛ ደረጃ 30% እና 3ኛ ደረጃ 20%)፡፡
      የምግብና የመጠጥ ለማስላት ድርጅቱ ምን ሴክተር ላይ እንደሚሰራ ማወቅ ያስፈልጋል ምክንያቱም ከታክስ ነፃ የመሆን መብት የተሰጣቸው ለእነዚህ ብቻ ስለተፈቀደ (በማዕድን ማወጣት በማኑፋክቸሪንግ በግብርናነ ሆርቲካልቸር በሆቴሎችነ ሬስቶራንቶች የምግብ አገልግሎት ስራ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች)::
      በመጨረሻ ታክስ የሚከፈልበትን መጠን አንድ ላይ ደምረን በ employee tax rate እናሰላለን

    • @Diamond21192
      @Diamond21192 4 หลายเดือนก่อน

      @@BekoTube-BM 🙏🙏🙏🙏🙏🙏😍😍😍😍😍😍

    • @muhamedmarye
      @muhamedmarye 4 หลายเดือนก่อน

      ስራካለ በሹፍርና እና በሌላም ዘርፍ አገናኙኝ ፈልጉልኝ

    • @AzmerawBayih
      @AzmerawBayih 3 หลายเดือนก่อน

      አመሰግናለሁ እህቴ። ስለዚህ ምን ይሻለኛል የስራ ልምዴን ቢያንስ ማግኘት እፈልጋለሁ።