በ12 የመግደል ሙከራ እና በ2 የነፈስ ወንጀል አስገራሚ የመልካም ወጣት ምስክርነት SEP 05,2021 MARSIL TVWORLDWIDE

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 6 ก.ย. 2024
  • SUBSCRIBE TO
    OUR YOU TUBE CHANNEL MARSIL TV WORLD WIDE TEACHING BY PROPHET YONATAN AKILILU
    UNAUTHORIZED DISTRIBUTION AND RE UPLOAD OF THIS CONTENT IS STRICTLY PROHIBITED

ความคิดเห็น • 318

  • @genettekle4477
    @genettekle4477 3 ปีที่แล้ว +84

    ዮኒ በጌታ እሱን ማዳን ሀገር ማዳን ነው እሱን የምትረዱ ብለህ ብትጣራ እንሳተፋለን አትለየው ታላቅ እርዳታ ይፈልጋል አገልጋይ ይሆናል አንተ ግን ምን እጣ ነው የወደቀብህ ጌታ ዘመንህን ይባርክ ተባረክ

  • @kibineshyohannes2866
    @kibineshyohannes2866 3 ปีที่แล้ว +55

    አቤት የአምላክ ቸርነት ምህረቱ እጅግ ብዙ ነው ሃይሉና ችሎታው ትልቅ ነው በፍቅሩ አመጸኞችን አንበርክኮ የሚገዛ ሥራው ድንቅ ነው ስሙ ይባረክ 😭😭🙏🙏🙏❣️
    ዮኒ ጌታ አሁንም አቅም ይሁንልህ ጸጋው ይብዛልህ
    ክፉ እንዳይበቀልብህ ዙሪያህ ሁሉ በኢየሱስ ደም የተሸፈነ ይሁን 😭❣️❣️❣️🇪🇹🇪🇹🇪🇹

  • @emmyt311
    @emmyt311 3 ปีที่แล้ว +60

    እንደዚህ አይነት ሰው ሲቀየር በጣም ነው እሚቀየረው‼ ካለ እግዚአብሔር መንፈስ ቀያሪ የለም‼ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ የሰላም ዘመን ይሁንልህ‼ ዮኒዬ ተባረክ♥‼

  • @sweetlove2592
    @sweetlove2592 3 ปีที่แล้ว +73

    አቤቱ ምህረትህ እጅግ ያስደንቃል የመውደድህ የፍቅርህ ብዛት ከአይምሮ በላይ ነው ስምህ ብሩክ ይሁን ለዘለአለም ዮኒ ዘመንህ ይለምልም ጸጋው ይብዛልህ።

  • @user-mm6ch4bl2x
    @user-mm6ch4bl2x 3 ปีที่แล้ว +34

    የክርስቶስ ደም ከሃጥያት ሁሉ ያነጻል

  • @rb2782
    @rb2782 3 ปีที่แล้ว +7

    ዮኒ ይህንን ሰው እባክህን እርዳታ ያስፈልገዋል እና አንተ ብዙ ሰዎች እየረዳህ ነው ያለሆው ግን ሌሎች ሰዎች እንዲረዱት ብታደርክ በዛ በደብረ ዘይት ያለው የመንፈስ አሰራር ወጣቱን የፈጀ በሱስ ያጠፋ በዚህ ልጅ ምክንያት ይፈታል ብዬ አስባለሁ አትልቀቀው
    ዮኒዬ የትውልድ አባት እልፍ ሁንልን ተባረክ ዘርህ ይባረክ በዚህ እድሜህ በወንጌል ያልገባሆው ስፍራ እና ቦታ የለም እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክህ ሌላ ማንም አልልም

  • @ethiopiaeritrea7586
    @ethiopiaeritrea7586 3 ปีที่แล้ว +34

    አልቅሼ አልወጣ አለኝ ዮኒዬ እባክህን እኛም ልናግዘዉ የምንችልበትን መንገድ አመቻችልን። ወንድሜ ሁሉም አልፎ ነፃ ሆነህ እንደተረት የምታወራበትን ዘመን ጌታ ያምጣልህ።

    • @mesfeneegebre4511
      @mesfeneegebre4511 2 ปีที่แล้ว +2

      የኔም አስተያየት ነው እኛም የምነረዳበትን መንገድ አመቻችልን
      ዮኒ ተባረክ

  • @tiosam1616
    @tiosam1616 3 ปีที่แล้ว +32

    በህይወቴ እንደዚህ ዓይነት ምስክርነት ሰምቼ አላውቅም ጌታ ይባረክ ያለ ጠመንጃ የሚያንበረክክ

  • @user-jw9qk9rg3b
    @user-jw9qk9rg3b 3 ปีที่แล้ว +46

    ዮኒዬ በጌታ ይሄን ሰው አትልቀቀው እኛም ከጎንህ እንሆናለን በጣም ያሳዝናል በእውነት ዘመኑን በሙሉ ሰይጣን በልቶበታል ወንድሜ ቀሪው ዘመንህ ይባረክ የካሳ ይሁን

  • @ethiopia7544
    @ethiopia7544 3 ปีที่แล้ว +9

    እረረረ በዚህ እየሱስ ተገረምኩ ተደነኩ 💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚

  • @amenenbakom1874
    @amenenbakom1874 3 ปีที่แล้ว +18

    ከሁሉም መጀመሪያ ዛሬን እድታይ የረዳህ የጠበቀህ ምህረት ያረገልህ ጌታ ይክበር ዮንዬ ምንም ቃላታ አጣውለት ትምህርትህ ስንቱን ነው የለወጠው ሀገርን ነው የምትገነባው ለምልምልኝ

  • @edanyegeta8176
    @edanyegeta8176 3 ปีที่แล้ว +5

    ባለማውቅክ ብዙ ሰህተት ብትሰራም ባንተም በደርሰው ብርሃንን አተክም የይቅርታ ልብ እግዚአብሔር ሰለሰጠክ ጌታ ይባረክ በቀረልህ ዘመን የባለፈው ሰህተት በህይውትክ እንዳይደግም በእግዚአብሔር ቤት ተተክለህ ኑር ዮኒ ዘመንህ ይለምልም

  • @ethio...2123
    @ethio...2123 3 ปีที่แล้ว +69

    ከደብረዘይት ወቶ ሌላ አካባቢ ቢኖር መልካም ይመስለኛል እሱ ቢተው የተጎዱ ሰዎች አይተውትምና አለ የሚለውን ቦታ ሸጦ የግል አስተያየቴ ነው

    • @ruthmebratu1049
      @ruthmebratu1049 2 ปีที่แล้ว +2

      yiqir teblual be geta.yesew fird lela new.

    • @anafijohn7981
      @anafijohn7981 2 ปีที่แล้ว

      Betikekil

    • @Redhauk
      @Redhauk 2 ปีที่แล้ว

      ምን አለው የት ይሂዲ።የቤተሠብ ውርስ ንብረት ባይኖረው ጥሩ ነበር እሱ ይጎትተዋል

    • @eysusyadenaleysusfekernaw627
      @eysusyadenaleysusfekernaw627 2 ปีที่แล้ว

      Tikikl naw geta ba damu yeshfenu

  • @user-it8ut8fj3s
    @user-it8ut8fj3s 3 ปีที่แล้ว +10

    ውይ አደራቹን ይህን ሰው በደንብ ያዙት እንዴት ያሳዝናል ጌታ እግዚአብሔር ወንድሙን አቤልን የገደለውን ቃየልን ያገኘው ሁሉ እንዳይገለው ምልክት እንዳደረገለት በየሱስም የክርስቶስ ደም ይሸፍንህ።መፅሀፍ ቅዱስ ላይ ሰው የገደለ ደም ተበቃዩ አግኝቶት እንዳይገለው ቶሎ ሸሽቶ ወደመማፀኛ ከተማ መግባት አለበት እዛም ከተማ ካህኑ በህይወት እስካለ ድረስ ከከተማው ሳይወጣ በህይወት ይኖራል። ዛሬም ሸሽተህበት የመጣከው እየሱስ ከደም ተበቃዮች ሁሉ ይሸሽግህ ሊቀ ካህናት እየሱስ ዘላለም ስለሆነ ክነቱ በዘላለም ሂወት ጥላ ውስጥ ያስጠልልህ።

  • @sabawoldu5831
    @sabawoldu5831 3 ปีที่แล้ว +12

    በሰው ተስፋ ይቆረጣል በጌታ ግን ሁሊም ተስፋ አለው እንኩዋን ጌታ እረዳህ ወንድሚ

  • @godisgoodallthetime836
    @godisgoodallthetime836 3 ปีที่แล้ว +15

    በእውነት በጣም የሚያሳዝን ታሪክ ነው ጌታ ሆይ

  • @werkineshhailemelekot64
    @werkineshhailemelekot64 3 ปีที่แล้ว +16

    ጌታ በደሙ ከጠላት ይሸፍንህ ሞገስ ከለላ ይሁንህ ይችላል አይዞኝ ደግሞ ያንን ሁሉ ያሳለፈህ ለመልካም ነው ወንድም 💪❤🙏

  • @tademahi857
    @tademahi857 3 ปีที่แล้ว +5

    ታምራት ጉርታ እኔ ከልጅነቴ ጀምሮ አውቀዋለሁ።የእርሱን ታሪክ ገና አልተናገረም።ሳየው ማመን ነው ያቃተኝ።ከልጅነታችን ጀምሮ ስንፈራው ነው ያደግነው።በጣም የሚገርመኝ ፓሊስ እርሱን ለመያዝ ይከፍሉት የነበረው ዋጋ።እግዚአብሔር ነፍስህን ያቆየበት ምክንያት አለው።ስለ አንተ እግዚአብሔርን አመሰገንኩ። ዩኒ ይሄን መድረክ ስላዘጋጀህ ጌታ ይባርክህ።

  • @healthyfood7119
    @healthyfood7119 3 ปีที่แล้ว +8

    ፈጣሪ ይህን የተረፈዉን እድሜህን ይባርክልህ ጌታ እየሱሰ ልጆቹን አይራሰም 👨‍👩‍👦‍👦👨‍👩‍👧‍👦 ተባረክ ዮወኒ ምን እንደምል አላዉቅም ተባረኪ እህቴ አንድ ሂወት ማዳን ማለት ቀላል አይደለም ተባረኪ እግዚአብሔር ጸጋውን ያብዛልሸ ።

  • @prophetrobelkiya8053
    @prophetrobelkiya8053 2 ปีที่แล้ว +3

    ዮንዬ ዛሬ በጣም ነዉ ያለቀስኩት እድመክን ያራዘመው መዳንያለም አንተ ድንቅ ስጦታችን ነክ 💖💖📖📖📖📖🏥🏥🎤🎤🎤

  • @tigisttakle6112
    @tigisttakle6112 3 ปีที่แล้ว +6

    አቤት የእግዚአብሔር ምህረት ዮኒዬ የማቱሳለን እድሜ ይሰጥክ ልዩ ነክ❤️
    ወንድሜ እግዚአብሔር አምለክ በቤቱ የቆምህ❤️🙏

  • @werkineshhailemelekot64
    @werkineshhailemelekot64 3 ปีที่แล้ว +11

    እግዝያብሄርን እድሜ ቀጥሎልካል ወንድሜ ታሪክ ነው ጌታ ይጠብቃል ለምስክርነት ያበቃል ዮኒ አንተኮ አንዳንዴ ልብህ ቅንነትህን እረ ማቀፍህን ንጹሕ ወንድ ምን ይህን ሳስብ ዋይ ብየ የደስታ መጮህ ያምረኛል ሺ ሁንልንዮኒ❤🙏

  • @Mom2023new
    @Mom2023new 2 ปีที่แล้ว +1

    ወደ ንስሐ የሚያመጣ እውነተኛ የእግዚአብሔር ድምጽ!!! (ከ1989--2014 ዓም. ) አዋጅ!! አዋጅ!! ጆሮ ያለው ይስማ!!!
    (ህዝ2:3-8,ዘፀ.3:13-15, ዮሐ.8:26, ኤር 26:) ፣ ወገኖቼ፣ እግዚአብሔር ከህዝቡ ጋር ክርክር አለው!! በልጁ በኩል በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ለአመታት በፀሎት ላይ እያለሁና በሌሊት ድምጹን እያሰማኝ፣ከዘመኑ የሁካታ መድረክ ሸሽጎኝ፣በዘመኔ ሁሉ የገጠሙኝን የጠላት ፈተናዎች፣ በትእግሥት እንዳልፍ፣ መንፈስ ቅዱስ ቃሉን በመግለጥ እየስተማረኝና እየመከረኝ፣ እየገሰጸኝ፣ እያጽናናኝ፣ ለህዝቡ መልእክተኛው አደረገኝ፣ የጌታ ስም ለዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን። ኢየሱስንም በተቃወሙት ጊዜ፣ ይሁን እንጂ የላከኝ እውነተኛ ነው፣እኔም ለዓለም የምናገረው፣ ከእርሱ የሰማሁትን ብቻ ነው አላቸው፣ (ዮሐ8:26,) ጌታም፣ ስለ ህዝቡ እንዲህ ሲል ቅሬታውን ይናገረኝ ጀመር፣ ....ጌታስ ከሆንኩኝ መፈራቴ ወዴት አለ..?(ሚል.1:6-8,)..ሰማይ ዙፋኔ ነው፣ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፣ የምትሰሩልኝ ቤት ምን አይነት ነው..? እስከ ዛሬ ድረስ ይህን ድምጽ የናገረኛል፣በዚህም ውስጥ መን/ቅዱስ፣ አገልጋዮችን ይጠቁመኛል፣ (ኢሳ 66:1-4, ኢሳ 55:8-9,ኢሳ 59:1-2,) በተደጋጋሚ በተለያዩ ቀናት በሌሊት ይናገረኝ ነበር፣ ጌታም፣ ይህ ህዝብ መስማትን ይሰማል!!፣ ነገር ግን አይኖርበትም!! ህዝቤ የራሱን ነገር አስቀድሟል!! ክብሩን አልጣለም!! ቤቴን በእኔነት፣ በማስመሰልና በስሜታዊነት ሞልተውታል!!እውነተኛ ፍቅር የላቸውም!! እርስ በርሳቸውም ይነቃቀፋሉ!! ሰላምም የላቸውም!! ይቅር መባባልን እንቢ ብለዋል!!ለትውልዱ መልካም ምሳሌ መሆን አልቻሉም!! ይህ ትውልድ የሆሴዕን ዘመን ትውልድ ይመስላል!! ህዝቤ መመለስ እንቢ ብሏል!! በጎቼን ለሚገፉ እረኞች ወዮላቸው!! ይህ ህዝብ አስቆጥቶኛልና አመጸኞችን አልምርም!! አለኝ። ባሬያዎቼ ተንቀዋል!! (እውነተኞቹን) ይህ ህዝብ ልቡ የሸፈተ ነው!! ክብሬን ደግሞ ይጋፋል!! ክብሬን እኮ! ጣሉ!! አለኝ። በሌላም ቀን፣ይህ ህዝብ አፉ ከእኔ ጋር ነው፣ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው!! ህዝቤ በእውነትና በመንፈስ አላመለከኝም!! አብዝቼ ብጠራቸው፣ አጥብቀው ከፊቴ ራቁ!! እስራኤል ( የእግዚአብሔር ህዝብ) የለመለመ ወይን ሆኖ ሳለ፣ እንግዶች ጉልበቱን በሉት!! የወይኔን ቦታ ፍሬ አጣሁበት!! እኔን የህይወት ውሀ ምንጭ ትተውኛል!! ለራሳቸውም ሌሎች ጉድጟዶችን ቆፍረዋል!! ክርስቲያን ሳይሆኑ ክርስቲያን የሚመስሉ፣ ህዝቤን ግን ኃጢአት የሚያለማምዱ በቤቴ አሉ!! እኔም ብዙ ጊዜ ዝም አልኩኝ!! እነርሱም አልሰሙኝም ፣ወደ እኔም አልተመለሱም!! ህዝቡ በንስሐ ካልተመለሰና ለቃሌ ካልታዘዘ፣ መርገም ከህዝቡና ከምድሪቱ ላይ እንዴት ይሰበራል? ቃሉ ያረጀባቸው የሚመስላቸው ብዙዎች በቤቴ አሉና የእግዚአብሔርን ነገር ለሚታክቱ ወዮላቸው!! የማያስተውል ህዝብ ይገለበጣል !! አለኝ። በሌላም ቀን፣ ህዝቤ ሲጠፋ የማይመክሩና የማይገስጹ ቸልተኞች ኤሊዎች በቤቴ በዙ!!አለኝና ቤቴን ትቼአለሁ፣ እርስቴንም ጥያለሁ፣ እንደ ዥንጉርጉር አሞራ ሆነውብኛልና!! አለኝ። ክብር ከእስራኤል ሸሸ!! አለኝና ህዝቤ እውቀትን ከማጣቱ የተነሳ ጠፍቷል!! የጠፉ በጎችም ሆነዋል!!የሚያስተውልም የለም!! ነብያቶቿ ጉቦ ተቀባዮች ናቸው!! አለኝ፣ ኢሳ 66፣ 1-4,ያለውን ከነገረኝ በኋላ፣ህዝቤ የወንበዴዎች ዋሻ ሆነ!! እኔ ግን ወንፊትና መንሼን ይዤ እነሳለሁ፣ የሌዊንም ቤት አጠራለሁ!! የሊባኖስን ዝግባ አናውጣለሁ፣ ያውም የጽድቅ ዛፎችን ነው!! አለኝ፣ መኔ! መኔ! አለኝና ባለራእይችን አጠራለሁ !! (አፀዳለሁ) ከፍታዎችን እንዳለሁ!! ከአሁን በኋላ የመድረኩ ቁልፍ በእጄ ይሆናል!! ያከበሩኝን አከብራለሁ!! እስራኤልንም በቃኘሁ ጊዜ፣ ምድርን ሁሉ እዳስሳለሁ አለኝ መንፈስ ቅዱስ።
    *ጌታም መሃሪ ስለሆነ፣የተሰፋውን ቃል በማሰብ፣ እግዚአብሔር ይጣራል!! በያቸው አለኝ፣ ህዝቤ ግን በንስሐ ወደ እኔ ቢመለስ ምህረትን አደርጋለሁና የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው!! እንግዲህ ንሰሐ ግቡ!! ትልቅነታችሁንም አስወግዱ!! ልባችሁን አጥሩ!! ወጪቱ ይጥራ!!ፈጥናችሁ ተስማሙ!! በፍቅሬ ኑሩ!! የምትወዱኝስ ከሆነ ትእዛዜን ጠብቁ!! የምትወዱኝስ ከሆነ በጎቼን ጠብቁ!!!ሊታረዱ ያሉትን አድኑ!!የምታደርጉትን ሁሉ በስሜ አድርጉት!! የከበረውን ከተዋረደው ለዩ!! እርሱን ብቻ ስሙት!! ለእርሱ ብቻ ስገዱ!! እውነተኛ ፍርድንና ጽድቅን አድርጉ!! አሳች ወጥቷልና ንቁ!! እናንተ የእግዚአብሔርን እቃ የምትሸከሙ፣እልፍ ፣ በሉ.!! ህዝቤ ሆይ ወደ እልፍኝህ ግባ!!፣ የሚንበረከኩ ብዙ ናቸው!! የሚፀልዩ ግን ጥቂት ናቸው!! በደልን ተሞልተዋልና፣ አልሰማቸውም!! ህዝቤ ንስሐ አይገባም!! እራሱንም እንደ በደለኛ አይቆጥርም!! ድምጼንም እንደ ሻገተ እንጀራ ጣሉት!!!ስለዚህ፣ የፈረሰውን መሰዊያችሁን አድሱ!! ልባችሁን እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ!! ለፀሎትም በቆማችሁ ጊዜ ንስሐ ግቡ!! የበደሉአችሁንም ይቅር በሉ!!ይህ ዘመን በንስሐ የመንጻት ዘመን ነው!! አጥብቃችሁ ፊቴን ፈልጉ!! ሳታቋርጡ ጸልዩ!! ምጽአቴ ቀርቧልና ዘመኑን ዋጁ!! ሙታን ድምጼን የሚሰሙበት ዘመን ይመጣል!!(ዮሐ 5:25,)የወደቀችውንም የዳዊትን ድንኳን አነሳለሁ!! እሠራታለሁም አለኝ፣ በምጥ የወለድኩአቸውን ልጆቼን አልጥልም!! ወደ ከፍታም አወጣቸዋለሁ! የኢትዮጵያን ቤ/ክ.የምጎበኘው በነብያት ነው!!ትውልድን ቀብቼ አስነሳለሁ!! ሪቫይቫል በምድሪቱ ላይ ይመጣል!! ለዓለም በረከት ይሆናሉ!! ስለ ቃሌም እተጋለሁ!!አለኝ። በሌላም ቀን፣ ከአሁን በኋላ ያለው ዘመን የመከር ዘመን ነው፣ የአጨዳውም ጊዜ ደርሷል!! መከሩ ብዙ ነውና ፣ ሰራተኞችን እንዲልክ፣ የመከሩን ጌታ ለምኑ!!አለኝ፣ ስለዚህ የነገርኩሽንም ሁሉ ለህዝቤ ንገሪልኝ አለኝ ጌታ መንፈስ ቅዱስ!! አዋጅ!! አዋጅ!! ጆሮ ያለው ይስማ!! ወገኖቼ፣( በተቻላችሁ መጠን ለቤተክርስቲያን መሪዎችና ለህዝብ እንድታደርሱልኝ በጌታ ፍቅር እለምናለሁ፣ ጊዜው የንስሐና የእርቅ ጊዜ ነው! ለጌታ ድምጽ ስፍራ ልንሰጠው ይገባናል!! ጌታ ሊመጣ ነወ!!) ተባረኩ። እማማ ነኝ፣ እውነተኛ የጌታ መልእክተኛ።ሐ

  • @amashewakena8378
    @amashewakena8378 3 ปีที่แล้ว +3

    አገሬ የፈውስ ዘመን ደረሰ ነፍሰ ገዳይ ንሰሀ እየገባ ማየት እንዴት ደስ ያሰኛል እየሱስ ያድናል ወንድሜ የሐጢያትኞች ወዳጅ ነው ጌታ ይወድሀል ፀንተህ ኑር ፈውስህ ይፅና

  • @honeyb4984
    @honeyb4984 3 ปีที่แล้ว +14

    እንኳን ጌታ ረዳህ ወንድሜ.ዘመንህ ከጌታ ጋር ይለቅ.ተባረኩ 🙏🏽💕

  • @teshaleworku4124
    @teshaleworku4124 3 ปีที่แล้ว +53

    ወይ እግዚአብሔር ብቻውን መንግስት የሆነን ሰው ያለምንም ማስፈራራት ያለምንም መሣሪያ ያንሰረክካል

  • @amkelehawaz
    @amkelehawaz 3 ปีที่แล้ว +5

    ለሁሉም ጊዜ አለው እግዚአብሔር መልካም ነው የእውነት ሳየው በጣም ነው ደስ ያለኝ እግዚአብሔር አንድ ቀን ታሪክ ይቀይራል

  • @godisgoodallthetime836
    @godisgoodallthetime836 3 ปีที่แล้ว +8

    ዮዬ እግዚአብሔር ዘመንህን ይባርከው ለምልምልን ይሄንን ራዕይ በልብህ ያስቀመጠ ያሸከመህ ጌታ ይባረክ እግዚአብሔር ትውልዱን እያዳነ ነው ስሙ ይባረክ

  • @monaali9356
    @monaali9356 3 ปีที่แล้ว +2

    እግዛከብሔር ህይወት የቀጠለልህ ለንሰሀ ነው እና በዚች እድ ተጠቀም አባ ዬኒ ተባረክ በብዙ ።

  • @godisgoodallthetime836
    @godisgoodallthetime836 3 ปีที่แล้ว +29

    እሱ ከሰራው ወንጀል በእስር ቤት የደረሰበት ጭካኔ እንዴት ሊያርመው ይችላል ??
    ሰው እላዩ ላይ ሲፀዳዳ በዛ ጉዳት ውስጥ እያለ ቅድሚያ ህክምና ቢሰጡት ትንሽ ሰብአዊነት ቢያሳዩት እንዲህ ክፉ አይሆንም ሁሉም ሰው የበኩሉን ቢወጣ ብቻ የእግዚአብሔር ማዳን ይገርማል አስለቀሰኝ በጣም ቀሪ ዘመንህን እግዚአብሔር ያቅናው

  • @mhsenailmhsenail2098
    @mhsenailmhsenail2098 3 ปีที่แล้ว +6

    አቤት እግ/ር እንዴት ይወድሀል እረረረረረረረረረ ስንትጊዜ ከሞት ታደገህ አቤት የእግ/ር ምህረት

  • @Selam694
    @Selam694 3 ปีที่แล้ว +6

    ቀን እየሰራ ማታ መማር አሁንም ትችላለህ ወንድሜ :: በ 72 አመታቸው 1 ኛ ክፍል የጀመሩት ለሁላችን ምስክር ናቸው :: ዮኒ ለዚህ ልጅ ሁሉም እንዲተባበር ካደረክልን ያቅማችንን እንልካለን 5 ም ይሁን 10 በውጭ ያለነው እንረዳዋለን :: ከዚህ በሁዋለ ተቸግሮ መኖር የለበትም :: የነፍሱን ጌታ ደርሶለታል የስጋውን ግን የኛ የሰዎች ሀላፊነት ይመስለኛል :: ገገማ ሰገጤ ፖሊሶች ግን አይናችሁን እና እጃችሁን ከዚህ ሰው ላይ አንሱለት እባካችሁ

  • @dureessaaterefe82
    @dureessaaterefe82 3 ปีที่แล้ว +3

    በእውነት እንባዬ ነው የመጣው፣ ጌታ መሃሪ ነው። እግዚአብሔር ይርዳህ። እባካችሁ የእርዳታ ነገር ብታስተባብሩ እንሳተፋለን። እንዲህ ያለ ሰው ሕይወት መቀየር ለብዙዎች ትምህርት ይሆናል።

  • @selamebegetamulunawe
    @selamebegetamulunawe 3 ปีที่แล้ว +4

    ዮኒ ይሄ ሰው ስራ አይደለም የሚያስፈልገው እኛ ያለንን እንርዳው እባክህን በአንዱ ልጅህ ይዘንሀል ይሄ ሰው ካንተ አይራቅ እዛው አንተአካባቢ ቤት ተከራይተህለት ይቀመጥና መፅሀፍቅዱስ ይማር እባክህ ይሄ ሰው ነገ ለብዙዎች መፍትሄ ነው እኔ የምበላውን ትቼ ያለኝን እረዳለው ኢትዮጵያን የሚወድ ሰው ሁሉ ለዚህ ልጅ አድርጉ ቢባል መቼም እምቢ የሚል የለም ዮኒ እባክህ🙏🙏😭😭😭

  • @martatesfaye7773
    @martatesfaye7773 3 ปีที่แล้ว +3

    ጌታ ከክፉ ይጠብቅህ በጣም ነው ልቤ የተንሰፈሰፈው እንኳን ጌታ ረዳህ እንኳን ምህረትን አገኘህ ፦ ዮኒዬ ዮኒ ተባረክ ለምልም

  • @fekerhaylu5390
    @fekerhaylu5390 3 ปีที่แล้ว +7

    😭😭😭😭😭😭የእውነት ከልቤ አዘንኩል አለቀስኩ የእንድ ሰው ቁስሉ ሲነካ ነው ሰው ሚያለቅሰው የኔም ወንድሞች እንዳንተ ነብስ ባያጠፉም የዘቀጠ ህይወት ነው ሚኖረው አይ እነዚህን የወለደች እናት መባል ከባድ ነው እግዚአብሔር ግን ቀን አለው

    • @rahelayele4116
      @rahelayele4116 3 ปีที่แล้ว +1

      Ayezone le hulu geza alew sis kechalishe endeadu adergi

  • @mememalase9018
    @mememalase9018 3 ปีที่แล้ว +5

    Thank you jesus 🙏🏻💕🙏🏻💕🙏🏻💕🇪🇹

  • @tigestermayse8641
    @tigestermayse8641 3 ปีที่แล้ว +1

    Amen Amen Amen Amen Amen Amen Amen 🙏 Tabarekeuuu Egzaibher Zamanachu Yetabareke Shalom Shalom Shalom ✨✨✨ 🙏

  • @beletetigist9830
    @beletetigist9830 3 ปีที่แล้ว +8

    😥ማነው ምህረትህ ሳየቆመው ሠው የሆነ?
    መተላለፉን ሳተውለት ዛሬን ያየ ?
    እጅ በእጅ ብትቀጣው ማን ይቆማል ?
    ምስክር ነኝ ምህረትህ ለኔ በዝትዋል ።
    ሠው ሁሉ የረሳው ፊቱን ያዞረበት
    ባንተ አይደለም ወይ እንዲህ ያማረበት
    እየራራህለት ስንቱን አባት ሆንከው ?
    ወገን የለኝ ያለን ስንቱን ተዛመድከው ።
    አባ እየሱስ እየ ተባረክ

  • @senaitalemayehu2689
    @senaitalemayehu2689 3 ปีที่แล้ว +3

    ዮኒ መቼም ምን ልበልህ ዘመንህ ይባረክ

  • @zerituzed8531
    @zerituzed8531 27 วันที่ผ่านมา

    ዮኒዬ❤ ለላ ቃል አጣክ ለሰው ልጅ ኑሪልን ጌታ የእዲ ድሜ ዘመን ህን ይቀጥል❤❤❤❤❤❤❤❤

  • @masiratwoldigiors8126
    @masiratwoldigiors8126 3 ปีที่แล้ว +7

    እድል ነው በ አንድ ዐይን በህይወት ታርፋክ ለ ንሰሃ መብቃት ቀር ዘመንህ በቤቱ ይለቅ

  • @fikrtetefye8224
    @fikrtetefye8224 3 ปีที่แล้ว +7

    ዮኒ ጠንከር እስኪል ካንተጋር ቢሆን❤❤👏👏

  • @hanahana4519
    @hanahana4519 3 ปีที่แล้ว +6

    አቤት እንደ እግዚኣብሔር ያለው መንም የለም 📖🌷🌱🌲🇪🇹👂😥🇱🇧🙇

  • @sifenshume7726
    @sifenshume7726 3 ปีที่แล้ว +6

    አቤት የጌታ ምህረት ብዙ ነው ወንድሜ እግዚአብሔር እንኩዋን ደረሰልህ ያለፈውን ጥፋትህን ረስተህ ወደፊት እግዚአብሔር የሰጠህን እድሜ ለእግዚአብሔር እና ለራስህ እንድትኖር እግዚአብሔር ይርዳህ ተባረክ ከአሁን በኃላ ክፉ አያግኝህ እግዚአብሔር ይጠብቅህ 🙏
    ዮንዬ ዘመንህ ይባረክ እግዚአብሔር ለዚህ ትውልድ ስላስነሳህ ስሙ ይባረክ እጅግ አድርጌ ጌታን አመሰግናለሁ 🙏❤️

  • @user-ni3kb9ef5l
    @user-ni3kb9ef5l 3 ปีที่แล้ว +76

    ሰላም አደራቹ በእግዚአብሔር የተወደዳችሁ በሙሉ 🥰

    • @user-mm6ch4bl2x
      @user-mm6ch4bl2x 3 ปีที่แล้ว +2

      እግዚአብሔር ይመስገን

  • @tigestermayse8641
    @tigestermayse8641 3 ปีที่แล้ว +5

    Amen Amen Amen 🙏

  • @dagmawisamuel7250
    @dagmawisamuel7250 2 ปีที่แล้ว +2

    እዚይ ቦታ ስላየሁህ ደስ ብሎኛል እኔም ይቅር ብዬሀለው 99 አ/ም ላይ ወንትድ ሆኜ ከሸገር እና የተለያዩ ክልሎች ላይ እፈለግ ስለነበር ለአጭር ጊዜ ደዘ ነበርኩ ነፍሱን ይማረውና አንድ ሴንታ የተባለ ጀለሴ ጋር ደዘ 07 አየርወለድ ሆቴል እየጠጣን ነበር እዛ የነበሩት አጠቃላይ አይናቸው እኛ ላይ እንደሆነ የገባው ቆይቶ ነው አጋጣሚ ፍሬንድ ትልቅ ጃኬትና ኮፍያ አርጎ ስለነበረ ታምራት የሚባለው በስም እንጂ በአይን አይተዋት የማያውቁት ሰው ነው ብለው እርግጠኛ ሆነዋል ጀለሴ እና እኔ ቤቱ ውስጥ በሚሰሩ ሴቶች ተከበናል አንዷ ቀበሮ ጠጋ ብላ ለጀለስ እሚከታተሉን ሰዎች እንዳሉ ነገረችው ተከተለኝ ብሎ ወደጓሮ ሲሔድ ሶስት ሰዎች ተከተሉት እኔም ፉግሮች ተከትለውን ነው ብዬ እርግጠኛ ሆንኩ ከተወሰነ ደቂቃዎች በኃላ የተኩስ ድምፅ ሰማው ብድግ ብዬ እግሬ ላይ ሻግ አድርጌው የነበረውን ቤሎታ አውጥቼ በገባሁበት በር ወጣሁ በያስኩት ስለት በርላይ የነበሩ የሆኑ ሁለት ሶስት ሰዎች ላይ ጉዳት አደረስኩ ጣራ ለጣራ እያባረሩኝ አምልጬ ሰላም የምትባል ደዘ የማቃት አጭር ጊዜ ቢሆንም እሷ ጋር ሄጄ አደርኩ ወሰን እና እስፔን የሚባሉ ምርጥ ወንድሞችዋን አስተዋወቀችን እዛ አደርኩ ከሆቴሉ ብዚ አይርቅም ወጥተው ፍሬንድ የት እንዳለ ንገሩኝ ብያቸው ወተው ሲመለሱ የሰማሁት ይሔን ስም ነው ታምራት ጉልታ መስሎዋቸው ፍሬንድ በደንብ እንኳን መልኩን አጣርተው ሳያውቁ ስለት ስለያዝንና ኮፍያ ስላደረገ ተሸጠዋል ደጋግመው ተኩሰውበት እንዳመለጣቸው ነገሩኝ ደዘ ብዙ ሳልቆይ ሰላምና ሔዋን ከተባሉ መንታ የደዘ ልጆች ጋር አዳማ ሔድን አዳማ በሌላ ፉዎል ተይዤ ዴፖ ታስሬ የደዘ ዛፖዎች መያዜን ሰምተው ናዝሬት ድረስ በመምጣት ታምራት ወይም አብሮ ሲጠጣ የነበረው ያለበትን ምራ ብለው ሲያስጨንቁኝ ነበር ከወር በላይ ያለበትን ንገረን እያሉ ብዙ አሰቃይተውኛል በመጨረሻም ከዴፖ ጣቢያ አመለጥኩ ብራ ይቅር ብዬሻለሁ በስምሽ ተደውኬአለሁ በመግደል አላምንም ግን ፉዎለኛ ነኝ ብዙ ሰው አስቀይሜያለሁ ዛፖ ልብሱን ሳየው ራሱ ያመኝ ነበር ከሀገር እስከምወጣ ድረስ እግዚአብሔር ይመስገን አሁን ሌላ ሰው ነኝ የማይወሩ የብዙ ታሪኮች ባለቤት ነኝ ባጋጣሚ የዮኒን ፕሮግራም ሳየው ይሔን ስም አስታወስኩት በማላውቀው ተደውኬበታለሁ ለዛ ነው ብሮዬ ቀሪ ዘመንሽ የተባረከ ይሁን

    • @solomonkebede3512
      @solomonkebede3512 ปีที่แล้ว

      ናዝሬት በጣም የሚፈራ ልጅ አክሰር የሚባለውን ልጅ ታቀዋለህ ዕንዴ እዚ መልካም ወጣት ላይ እና ናዝሬት እያለውም በጣም ያወሩለታል ከዳዊት ድሪባ የበለጠ ታሪክ አለው ዕንዴ ብሮ ?

  • @seble8135
    @seble8135 3 ปีที่แล้ว +2

    እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም!! ወንድሜ ዮኒ ጌታ ኢየሱስ ይባርክህ !! ምን እላለሁ እግዚአብሔር ይመስገን!!

  • @ashenafiseifu13gamilseifu79
    @ashenafiseifu13gamilseifu79 3 ปีที่แล้ว +5

    Amen egzehaber yemesgen yoni tebarekh.

  • @hanaweba4436
    @hanaweba4436 3 ปีที่แล้ว +1

    እግዚአብሔር አምላክ ከዚህ ሁሉ ያለፈ ታሪክህ ድጋሚ እንዳታስብ ሊያሳርፍህ የታመነ ነው እንኳን በእሱ እጆች ላይ ማረፍ ሆነልህ አቅማችን በቻለ ከጎንህ የምንሆን ወገኖችህ አለን አይዞህ ጌታ በእንዳንተ አይነቶቹ የክብሩ መገለጫ እቃዎች አድርጎ ማዳኑን ያሳያል ሰው እንደሚያይ እሱ ጃጅ አያረግም ነጉ ታሪክህ ተቀይሮ እናይሀለን በበኩሌ ጉዳትህ እጅግ አሳዝኖኛል የጌታ እየሱስ ፍፁም እብሮነት ከአንተ ጋር ይሁን እንወድሀለን

  • @user-dv8pg7jy2o
    @user-dv8pg7jy2o 3 ปีที่แล้ว +2

    የእግዚአብሔር ምህረቱ ብዙ ነው
    የእግዚአብሔር ይቅርታው ብዙ ነው
    አቤት የኔ ጌታ ስምህ ይባረክ
    አይዞህ ወንድሜ እግዚአብሔር ሊያስተምርህ ስለፈለገ ነው ቀሪ ዘመንህ የደስታ የሰላም ይሁንልህ

  • @yekibirzufan1027
    @yekibirzufan1027 3 ปีที่แล้ว +2

    ይሁን አለ ሆነ
    ጌታ ሲል ማንም ሁን ምንም ሁን በሙሉ እጁ አቅፎ ይቀበልሀል
    ሀገሬ ተስፋ አላት!!!!!!
    ጌታ ይባርካችሁ!!!

  • @senaitalemayehu2689
    @senaitalemayehu2689 3 ปีที่แล้ว +5

    ያለፍክበት በጣም ዘግናኝ ነዉ ግን ጌታ መልካም ነዉ

  • @allotech6314
    @allotech6314 3 ปีที่แล้ว +11

    ዮንዬ ታባረክ ለኛ የታፋጣርክ ነህ 🙏

  • @dejenwogayehu1240
    @dejenwogayehu1240 2 ปีที่แล้ว

    1 ሰው ሁሉ ኃጢአተኛ ነው
    “ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤”
    ሮሜ 3፥23
    2 የኃጢአት ዉጤት ሞት ነው
    “የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው።”
    ሮሜ 6፥23
    3 ሰው ፍርድ ይጠብቀዋል
    “ለሰዎችም አንድ ጊዜ መሞት ከእርሱ በኋላም ፍርድ እንደ ተመደበባቸው፥”
    ዕብራውያን 9፥27
    4 ሰው በራሱ የፅድቅ ሥራ እራሱን ማዳን አይችልም
    "ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤
    ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።"
    ኤፌሶን 2÷8:9
    5 የሰው ልጅ የመዳን ተስፋው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው
    “ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው፤ ከኃጢአተኞችም ዋና እኔ ነኝ፤”
    1ኛ ጢሞቴዎስ 1፥15
    “መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።”
    ሐዋርያት 4፥12

  • @sonyshop2288
    @sonyshop2288 3 ปีที่แล้ว +2

    አባቴ የእግዚአብሔር ምሕረት የዘላለም ነው የኒዮ እልፍ በል በብዙ ፀጋ ጌታ እየሱስ ይባርክ ❤❤❤❤

  • @user-jw9qk9rg3b
    @user-jw9qk9rg3b 3 ปีที่แล้ว +9

    ወጣቶች ከዚህ ሰው ብዙ መማር ትችላላችሁ ህይወት የዋላ ማርሽ የላትም

  • @user-fm1tu5hb2k
    @user-fm1tu5hb2k 3 ปีที่แล้ว +3

    ዮኒዬ እኔ ምን እላለው እግዚአብሄር አምላክ በ ክርስቶስ ኢየሱስ ደም ይሸፍንህ አንተ ወንድሜ ዘመንህን ያድስልህ ደም በጌታ በ ኢየሱስ ክርስቶስ ደም የተሻረ ይሁን 🙏🏽😭😭😭😭

    • @sahareahare6242
      @sahareahare6242 3 ปีที่แล้ว

      😭😭😭😭😭😭😭😭😭❤❤❤❤❤❤

  • @user-ts5pu1ic8l
    @user-ts5pu1ic8l 2 ปีที่แล้ว

    አቤት የድንግል ማርያም ልጅ ተመስገን ስንቱ ከጠፍበት ተመለሰ ተመስገን።

  • @Myen0912
    @Myen0912 3 ปีที่แล้ว +3

    በዚህ ልጅ ላይ እግዚአብሔር ትልቅ ዓላማ አለው።

  • @user-ys8rl3cr5v
    @user-ys8rl3cr5v 3 ปีที่แล้ว +1

    በጣም የተጎዳ ሰው ነው ዘመኑን ሁሉ ጠላት ሲያሯርጠው ነው ዘመኑን ሙሉ ተከራተተ ጌታ በቃ ይበልህ !!!

  • @temesgenpaulos8046
    @temesgenpaulos8046 3 ปีที่แล้ว +4

    አይዞህ ወንድሜ በወስጥ ያልሁ ክፉ ነው ያንን ሁሉ ስያደረግ የነበር አሁን ግን ከአንተ ሄዶሃል እሽ ተባረክ ዮኒያን ምርጥ አገልጋይና አስተማር ሺህ አመት ኑርልን

  • @zenylema8717
    @zenylema8717 3 ปีที่แล้ว +1

    ይገርማል እግዚአብሔር ይመስገን አንተ እድለኛ ነህ እግዚአብሔር እደገና እድል ሰጠህ ቀሪ ዘመንህ ሴይጣን የበላብህን ዘመን የምትበቀልበት ይሁንልህ ቀሪ ዘመንህ የካሳ ይሁን ወንድሜ አይዞህ ዮኒ እደሚለው አረፈደም ወንድሜ ተባረክ

  • @konjeteeshetu3118
    @konjeteeshetu3118 3 ปีที่แล้ว +2

    የእኔ ጌታ ታራክህ ይቀይራል ዮኒ ጌታ ይባርክህ የዝህን ልጅ የዘአሬ አመት ለውጣ ማይትህ አለብን የምገርምህ ታሬክህ ነው

  • @mulatukebede9656
    @mulatukebede9656 3 ปีที่แล้ว +1

    ኦ ጌታ ፍቅርህ ይገርማል ይህ በደንብ ወንጌልን ቢማር እንደሱ ያለ ህይወት ውስጥ የገቡትን ሊያስተምር ጌታም ሊገለገልበት ይችላል

  • @tsionandualem8742
    @tsionandualem8742 3 ปีที่แล้ว +7

    Wow even this kind of cruel heart changed by the love of our almighty.
    Geta hoy tebareklgn!

  • @salmasalmaaa1625
    @salmasalmaaa1625 3 ปีที่แล้ว +1

    አቤት እግዚአብሔር ወይይይ ምን ይከፈለዋል 😭😭😭😭😭እግዚአብሔር ወይ አንተ ትልቅ ነህ አቤት ምምህረትህ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ጳውሎስ ሁን

  • @miami8347
    @miami8347 3 ปีที่แล้ว +5

    ዮንያ እባክህን ለተወሰነ ለውጡ እስኪፀና ከስርህ አትለየው እባክህን እባክህን ።

  • @burtkanfitamo3871
    @burtkanfitamo3871 3 ปีที่แล้ว +1

    Uuuuuuuuuuffffffffffff 💔💔💔💔😭😭😭😭baxami yasazinane igzabieri malikami New sila hulumi kibiri Hulu la anite yihuni

  • @Yabseratube
    @Yabseratube 3 ปีที่แล้ว +7

    ዮኒዬዬዬ አተ እኮ ትለያለህ የምልህ በምክኛት ነዉ ❤❤❤❤

  • @tigisttilaye5651
    @tigisttilaye5651 3 ปีที่แล้ว +2

    ዮኒዬዬዬ
    የእኔ ውድ ምን እንደ ምል አላውቅም ግን
    ብቻ የድካም ፍሬ እግዚአብሔር ያሳይክ 💗❤❤❤❤💔ወንድሜ ጌታ ይረዳክ

  • @sulamith8910
    @sulamith8910 3 ปีที่แล้ว +2

    Wow, no word, egziabher yimesgen.

  • @rahelasmerinabelalifestyle5566
    @rahelasmerinabelalifestyle5566 3 ปีที่แล้ว +1

    ዕድለኛ ነህ ያኔ አለማብቃቱ ሂወትክ ወንድሜ ይብቃህ መከራህ ያልሞትከው እግዚአብሔር እንድትጠፋበት ስላልፈለገ ነው ቀሪውን ዘመንህ በቤቱ ያኑርህ ዮንየ ብርክ በልልን የስንቱን ችግርና ቀረፍክ ካባትህ ስር ቅባቱን ጨምሮ ያብዛልክ ሀሌ ሉያ ያመጣሽው እህታችን ደሞ ተባረኪ በረከትሽ ይብዛ ለዚህ ምክንያት ነው አባትሽ የታመሙት እና ፈጣሪ ዐድሜና ጤና ይስጥልሽ አሜንንን 🙏😇❤🇪🇷❤🇪🇹❤

  • @ethio...2123
    @ethio...2123 3 ปีที่แล้ว +8

    ከዛ ሕይወቱን ካጨለመበት ጨለማ መላቀቁ እግዚአብሔር ቸር ነው ስሙ ይክበር

  • @angeldessesiferaw4603
    @angeldessesiferaw4603 3 ปีที่แล้ว +7

    አቤት ይጌታ ምርት

  • @dawitassefa9288
    @dawitassefa9288 3 ปีที่แล้ว

    ዬኒ እኔ በእናተ ሃይማኖት ውስጥ አይደለሁኝም የምኖረው ደዘ ነው ታምራትን ለዘመናት ስሙን ስሰማ ነው ያደኩትኝ በአካል ያየሁት አሁን ነው የነገረክ ነገር ሁሉ እውነትም ከመሆኑ ባሻገር ምንአልባት በተናገርው ልክ አይደለም አሳንሶታል ከምለው በላይ የሰው ልጅ እንዲህ ተለውጦ ማየት እጅግ ደስ ያሰኛል እናንተንም እግዚአብሔር ይባርካችሁ

  • @selamebegetamulunawe
    @selamebegetamulunawe 3 ปีที่แล้ว +3

    ይሄ ሁሉ አልፎብህ ሂወትህ እንዳታልፍ ያደረገህ ነገ የብዙዎች መፍትሄ ሊያደርግህ ነው እኔ ለሰው አዝኜ አውቃለሁ እንዳንተ ያዘንኩለት ያለቀስኩለት ስው የለም ግን ደሞ ይሄን ሁሉ ሞት ያሳለፈህ ያለምክንያት አይደለም ሊከብርብህ ነው በደንብ ሰው ሆነህ ትኖራለህ እኔ ያንተን ምስክርነት ድጋሚ እስክሰማ ድረስ በጌታ ፊት ስላንተ መፀለዬን አላቆምም ጌታ ይርዳህ ለበቀል ከሚፈልግህ በእየሱስ ደም ይሸፍንህ ጌታ ከለላ ይሁንህ

  • @enatalme9259
    @enatalme9259 3 ปีที่แล้ว +1

    Hi man say thanks God lot because God he give to you more life to see these day thanks

  • @yigeremueyoel379
    @yigeremueyoel379 3 ปีที่แล้ว +5

    WHAT AN AMAZING,POWERFUL, MARVELOUS,LIFECHANGING, MIRACULOUS,WONDERFUL, BEAUTIFUL,LIFETOUCHING, BLESSED,GOLDEN,TEACHABLE, ICON AND ANOINITED TESTIMONY AND ENCOUNTER PRAISE THE LORD HALLELUJAH::

  • @dawihabtu599
    @dawihabtu599 3 ปีที่แล้ว +1

    እግዚአብሔር ለተአምር እኮ ነው ያተረፈ
    በቀረው ዘመንህ ጌታ ይርዳህ አይዞህ

  • @hirutyedemufire8758
    @hirutyedemufire8758 3 ปีที่แล้ว

    አቤት የጌታ ምህረት😭😭😭የኔብሳችን መልህቅ ነህ ኢየሱሴ ክብር ለአንተ ይሁን የኔ ጌታ💓💓💓

  • @makimaki7260
    @makimaki7260 3 ปีที่แล้ว

    መ ማ ር የማይሰለችህ የኛ እግዚአብሔር ክብር ይግባህ🙏🙏🙏

  • @user-lw5mh9bl4z
    @user-lw5mh9bl4z 3 ปีที่แล้ว +2

    ይገርማል በጣም ዮኒ የዘንድሮዉ በጣም ልዩ ነው

  • @ethio...2123
    @ethio...2123 3 ปีที่แล้ว +5

    ለውጥህ እንደ አለት በአለቱ ኢየሱስ ላይ ጸንቶ ይቅር

    • @Selam694
      @Selam694 3 ปีที่แล้ว

      አሜን አሜን 🙏

  • @frehiwotwondemagagnhu1645
    @frehiwotwondemagagnhu1645 3 ปีที่แล้ว

    ዋና ዋናው ለጌታ ገቢ እየተደረገ ነው ፡፡ እግዙአብሄር ይመስገን ዮኒዬ ተሳክተልሃል፡፡

  • @mekdeswakene4158
    @mekdeswakene4158 3 ปีที่แล้ว +2

    Yoniye zemeneh yelemelem May God bless you more and more 🙏❤♥

  • @nigistasfaw962
    @nigistasfaw962 3 ปีที่แล้ว +1

    ዮንዬ ተባረክ የንተ ነፍስ እና መንፈስ ቅዱስ ናቸዉ

  • @ethiopia7131
    @ethiopia7131 2 ปีที่แล้ว

    Mini biye sili linagare sila anite fikire ❤❤📚📚📚🇪🇹 yene geta tamasigani libali inji❤🇪🇹

  • @godisgoodallthetime836
    @godisgoodallthetime836 3 ปีที่แล้ว +2

    የእግዚአብሔር ምህረት ይገርማል

  • @tegbarucanido9740
    @tegbarucanido9740 2 ปีที่แล้ว

    ዮኒዬ እግዚአብሔር ይባርክህ!

  • @senafekeshwgiorges2058
    @senafekeshwgiorges2058 3 ปีที่แล้ว

    ዪኒዬ ተባረክ የዚህን ሁሉ እናቶች እንባ ስላበስክ ቡዙ ወጣት ጌታ እየረዳህ ስላስመለጥክ መንግስትህ ያስፋልህ እንደገና በሶስት ልጅ ተባረክ አንድ ወንድ ሁለት ሴት ልጅ አጠቃላይ አራት ልጅ የኔ ሀሳብ ነው ጌታ ይረዳን እፀልያለሁ

  • @zzzzzz40
    @zzzzzz40 3 ปีที่แล้ว

    ማን እንደ እግዚአብሔር ሃያል የሆናውን ሃያልናቱ ስያሰይ ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን

  • @ayelechalemu3356
    @ayelechalemu3356 2 ปีที่แล้ว

    እግዚአብሔር ይመሥገን ይቅር ብሎ ለዚህ እድል ስላበቃህ ይክበር ይመሥገን ግን አሁን የምትኖርበትን አካባቢህን ብትቀይርና በጌታ ብቻ ነው መኖር ይኖርብሀል በርታ ዳግም አደራህን ወንጀል ውስጥ አትግባ አምላክ ይርደህ አሜን ።

  • @pawlorobrto9976
    @pawlorobrto9976 2 ปีที่แล้ว +1

    wow god is like this god bless you yoni🙏🙏🙏💖💕

  • @ArsemaVlog
    @ArsemaVlog 3 ปีที่แล้ว +1

    All the glory to our sweet Jesus Christ

  • @godisgood4259
    @godisgood4259 3 ปีที่แล้ว

    በየሱስ ስም አንት ብሮክ ስው አንት መልካም ስው ተባርክ ዘመንህ ይባርክ ዮኒ አንት አኩ አንድ ልጅ አይደልም የለህ ይህ ከሀያ አስክ ሀያ አምስት ሺ የሚቆጥሩ የመልካም ወጣት ትማሪዎች አባት ነህ ተባርክ እግዚአብሄር ለኛ ያስንሳህ ነህ አወድሀልሁ የ ሺ ውች አባት

  • @azebfekadu858
    @azebfekadu858 3 ปีที่แล้ว +1

    ለሰው የማይቻል ለእ/ር ይቻላል ስምህ ብሩክ ይሁን አባ!!!

  • @nanishow-6604
    @nanishow-6604 3 ปีที่แล้ว +4

    ዮኒ እባክህ ለዚህ ሠው ልዩ ክትትል ስጠው ብዙ ቁስል ልቡ ውስጥ አለ በጣም ነው ያሳዘነኝ😓😢

  • @ermiasalemayehu973
    @ermiasalemayehu973 3 ปีที่แล้ว +1

    yezin sewye tarik wede film bikeyer yebeletee astemari nw biye amnalewu yoni