Withholding part 3 , ቅድመ ግብር የመያዝ ግዴታ የሌለባቸው ሰዎች እና ተፈጻሚ የማይደረግባቸው ግብይቶች, ቅድመ ግብር ክፍል 3

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 28 เม.ย. 2024
  • ቅድመ ግብር (Withholding)
    ግብር ቀንሶ የመያዝ ግዴታ የማይመለከታቸው ሰዎች
    ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች
    ላኪዎች/ወደ ውጭ ለሚልኩአቸው ምርቶች በግብአትነት ለሚያገለግሉ እቃዎችብቻ
    በዲፕሎማቲክና አለም አቀፍ ስምምነትመሰረት የተመሰረቱ ድርጅቶች፣ የውጭ ዲፕሎማቲክ ኮንሱላር ሚሲየኖች፣ ኤምባሲዎች፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አካላትና የዲፕሎማቲክ መብት ያላቸው ተመሳሳይ አካላት
    ቅድመ ግብር የመያዝ ግዴታ ከተጣለባቸው ግለሰብ ግብር ከፋዮች ውጪ ያሉ ግለሰብ ግብር ከፋዮች
    ቅድመ ግብር ተፈጻሚ የማይደረግባቸው ግብይቶች
    የሰው/የእንሰሳት ህክምና አገልግሎት፤
    የመደበኛ ትምህርትአገልግሎት (ስልጠናን አይጨምርም)፤
    የፋይናንስ አገልግሎት(ባንክ የደንበኞቹን ንብረት ሲሸጥ የሚቀበለውን ክፍያ አይጨምርም)፤
    የኤሌክትሪክ አገልግሎት፤
    የቴሌ ኮሚኒኬሽን አገልግሎት፤
    የየብስ፣ የአየር፣ የባህር እና የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት (ኪራይን አይጨምርም)
    የውሃ አገልግሎት (የታሽገ ውሃን አይጨምርም)፤
    ከገቢ ግብር ነፃ መብት (Tax Holiday) የተሰጣቸው ኢቨስተሮች ከግብር ነፃ በሆኑበት ጊዜ ውስጥ የሚሠጡት አገልግሎት ወይም የሚያቀርቡት ዕቃ፤
    በገቢ ግብር አዋጅ መሰረት ከተከፋይ ሂሳብ ላይ ግብር ተቀናሽ የሚደረግባቸው የሠንጠረዥ “መ” ገቢዎች
    የነዳጅ አቅርቦት ( ቅባትና ዘይቶችን አይጨምርም )፤
    የፋብሪካ ምርት ያልሆነ የአርብቶ አደር እና የአርሶ አደር የግብርና ውጤት እንዲሁም ከእንሰሳት የሚገኝ አገልግሎት፣
    የፌዴራል፣የክልል፣ የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የመንግስት መ/ቤቶች የሚያቀርቧቸው ዕቃዎችና አገልግሎቶች፤
    ከመንግስት በተሠጣቸው ውክልና መሰረት ዕቃ ወይም አገልግሎት የሚያቀርቡ ድርጅቶች፤
    በዲፕሎማቲክና ሌሎች ዓለም አቀፍ ስምምነቶች መሠረት ለተቋቋሙ የአለም አቀፍ ድርጅቶች የውጭ ዲፕሎማቲክ ወይም ኮንሱላር ሚስዮኖችና ኢምባሲዎች እና ለተባበሩት መንግስታት አካላት የሚፈጸም ክፍያ፤
    በገቢ ግብር ህግ መሰረት ከግብር ነፃ የሆነ ገቢ (የሠንጠረዥ “ሠ” ገቢዎች)፣
    የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች የሚፈፅምለት ክፍያ፤
    የመኖሪያ ቤት ሽያጭ፤
    በሰው ጉልበት የሚከናወን ዕቃ የመጫን እና የማውረድ አገልግሎት፣
    ቅይጥ ግብይት (አንድ ግብይት ውስጥ ቅድመ ግብር የሚመለከተውና የማይመለከተው ግዥ)፤
    በማቋቋሚያ ህጋቸው ከገቢ ግብር ነፃ የሆኑ ተቋማትን
    ምንጮች
    ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008
    የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 979/2008
    የቅድመ ግብር ክፍያ ሥርዓት አፈጻጸም ቁጥር 2/2011
    ከተከፋይ ሂሳብ ላይ የንግድ ትርፍ ግብር ቀንሰው እንዲያስቀሩ ኃላፊነት የተሰጣቸው ግለሰብ ታክስ ከፋዮችን ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 145/2011

ความคิดเห็น •