#withholdingtax

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 5 ต.ค. 2024
  • #withholdingtax ቅድመ ግብር ክፍል 1 (Withholding part 1) የሀገር ውስጥ ግብይቶች ስለማካካስ እና ተመላሽ
    የንግድ ትርፍ/ የቤት ኪራይ ገቢ ግብረ አካል ነው
    በገዢው የሚሰበሰብ የግብር አይነት ነው
    ከውጭ የሚገቡ እቃዎች Withholding የሚያደርገው ጉምሩክ ነው
    ምጣኔው 2%፣30% እና 3%
    ከ1000 በላይ የእቃ ግብይት
    ከ3000 በላይ የአገልግሎት አቅርቦት
    ከውጭ የጉምሩክ ዋጋ፣ የኢንሹራንስና የትራንስፖርት ዋጋ 3%
    አላማው
    ገቢው በተገኘበት ወቅት ግብርን መሰብሰብ (time value of money)
    የግብር ስወራን ለመቀነስ
    በግዢ ወቅት ከሚፈፀም ጠቅላላ ክፍያ ላይ 2% ግብር ቀንሰው የማስቀረት ግዴታ አለባቸው፡
    በአንድ ግዥ ወይም በአንድ የዕቃ አቅርቦት ውል ከ10,000 ብር በላይ ለሆነ የዕቃ አቅርቦት ለሚፈፀም ክፍያ
    በአንድ የአገልግሎት ውል ከ3,000 ብር በላይ ለሚፈፀም ክፍያ
    ግብር ተቀናሽ የሚደረግበት ዕቃ/አገልግሎት አቅራቢ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን እና የፀና የንግድ ስራ ፈቃዱን (ሁለቱንም) ግብር ቀንሶ ለሚያስቀረው ገዢ ሊያቀርብ ካልቻለ ገዢው ለአቅራቢው ከሚፈጽመው ጠቅላላ ክፍያ ላይ 30% ግብር ተቀናሽ ማድረግ አለበት
    የቤት ኪራይ አገልግሎት እና የግዢ ማረጋገጫ ደረሰኝ (Purchase Voucher) መጠቀም ከሚቻልባቸው ግብይቶች ላይ ተቀናሽ የሚደረገው 2% ቅድመ ግብር ብቻ ነው፡፡
    አጠቃላይ የግዥውን (ገዢ) ወይም የሽያጩን (ሻጭ) ሙሉ ዋጋ መመዝገብ አለባቸው
    የቅድመ ግብር አፈፃፀም
    ተቀናሽ የሚደረገው 2% እና 30% ግብር የሚሰላበት የዕቃ/የአገልግሎቱ ጠቅላላ የክፍያ መጠን በግብይቱ ላይ የሚከፈሉ የመንግስት ታክሶችን (ተጨማሪ እሴት ታክስ እና ተርን ኦቨር ታክስ የመሳሰሉትን) እና በሻጭ ገቢ ውስጥ የማይካተቱ ክፍያዎችን ሳይጨምር ነው፡፡
    በዕቃና አገልግሎት ግዥ ውል መሠረት ከሚፈፀም ቅድመ ክፍያ (Advance Payment) ላይ የቅድመ ግብር ክፍያ ተቀናሽ አይደረግም
    በአንድ ውል ውስጥ የተመለከተው አጠቃላይ የገንዘብ መጠን በተለያየ ጊዜያት ተከፋፍሎ ክፍያ የሚፈፀም ሲሆን ለቅድመ ግብር ክፍያ መሠረት የሚሆነው አጠቃላይ በውሉ ላይ የተመለከተው የገንዘብ መጠን ነው
    የኮንስትራክሽን አገልግሎት ግዢን በሚመለከት
    ለኮንስትራክሽኑ ስራ የሚያስፈልጉ ዕቃዎችን ኮንትራክተሩ የሚያቀርብ በሚሆንበት ውል መሰረት ለኮንትራክተሩ ከሚፈጸም ክፍያ ላይ ግብር ተቀናሽ የሚደረገው እንደ ኮንስትራክሽን ስራው አይነት ከጠቅላላው ክፍያ ቀጥሎ የተመለከተው መቶኛ ብቻ ተወስዶ ይሆናል፡፡
    የህንጻ ግንባታ ----------------------------------------------45
    የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ሲቪል ስራ --------------------50
    የመንገድ ግንባታ
    ለጠጠር መንገድ ---------------------------------72
    ለአስፋልት መንገድ
    አስፋልት ኮንክሪት (Gravel Asphalt Concrete)-----65
    በድርብ አስፋልት (Gravel Double Surface) --------60
    መንገድ ማሻሺያ (Rehabilitation) -----------------------40
    ድልድይ ስራ -------------------------------------55
    ግብር ተቀናሽ የሚደረግበት ለጥገና እና ወይም ለእድሳት የሚፈፀም የክፍያ መጠን
    የጥገና እና /ወይም የዕድሳት አገልግሎት ሰጪዎች ከአገልግሎት ገዢ ጋር ለጥገና ወይም ለዕድሳት በሚያደርጉት ውል መለዋወጫ ዕቃዎችን አገልግሎት ሰጪ በደረሰኝ ገዝቶ ሲያቀርብ ገዢ ገንዘቡን እንደሚተካለት ከተስማሙ አገልግሎት ሰጪው ለመለዋወጫ ዕቃዎች ግዢ ከሚፈጽመው ክፍያ ላይ ግብር ተቀናሽ አድርጐ ገቢ የማድረጉ ግዴታ እንደተጠበቀ ሆኖ አገልግሎት ሰጪው ለመለዋወጫ ግዥ ያወጣው ገንዘብ በደረሰኙ መሠረት በገዢው ሲተካለት ከተከፋይ ሂሣብ ላይ 2% ግብር ተቀናሽ የማይደረግበት ሲሆን ግብር ተቀናሽ የሚደረገው ከ3,000 ብር በላይ በተከፈለ የአገልግሎት ዋጋ ላይ ብቻ ነው፡፡
    አገልግሎት ሰጪው ራሱ አገልግሎቱን ከመለዋወጫ ዕቃው ጋር በአንድነት የሚያቀርብ እና ለዚሁ ጠቅላላ ዋጋ የሚከፈለው በሚሆንበት ጊዜ አገልግሎት ሰጪው ከሚያገኘው ጠቅላላ ተከፋይ ሂሣብ ላይ ክፍያውን የፈፀመው ገዢ 2% ግብር ቀንሶ ገቢ ማድረግ አለበት ፡፡ የመለዋወጫ እቃና የአገልግሎት ዋጋውን መለየት አዳጋች ከሆነ ሙሉ ለሙሉ የአገልግሎት አቅርቦት እንደሆነ የቆጠራል
    የጥገናና እድሳት ማለት የተሸከርካሪ፣ የተለያዩ ማሽነሪዋች (ሎደር፣ ግሬደር፣ የፋብሪካ ማሽኖች የመሳሰሉት) እና የመሳሪያዎች ጥገናና እድሳት
    የቅድመ ግብር ሂሳብ አመዘጋገብ
    በገዢው
    ግዢ ሲፈፀም
    Asset (100%)……………1000
    Cash (98%)……………………….....….980
    Withholding tax payable (2%)………..….20
    ለገቢዎች ሲከፈል
    Withholding tax payable ……....20
    cash/bank………………….………..20
    በሻጭ
    Cash (98%)…………………..……………..980
    Prepaid tax/advance profit tax (2%)…......…...20
    Revenue (100%)………………………………………1000
    ለገቢዎች ሲከፈል
    Profit tax payable……….50
    Advance profit tax…………………………20
    Cash/bank…………………………………..30
    ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008
    የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 979/2008
    የቅድመ ግብር ክፍያ ሥርዓት አፈጻጸም ቁጥር 2/2011
    ከተከፋይ ሂሳብ ላይ የንግድ ትርፍ ግብር ቀንሰው እንዲያስቀሩ ኃላፊነት የተሰጣቸው ግለሰብ ታክስ ከፋዮችን ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 145/2011

ความคิดเห็น •