Labour Law ከስራው ለተባረረ ሠረተኛ የሚከፈል ካሳ /COMPENSATION/ የሠራተኛ ቅነሳ ድርጅቱ በመክሰሩ/በሌላ ምክንያት/ የማስጠንቀቂያ ጊዜ

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 6 พ.ค. 2024
  • የአሰሪና ሰራተኛ ህግ/labour law ሠራተኛው ያለማስጠንቀቂያ ስራውን ሲለቅ
    አሰሪው ከህግ ውጪ ሠራተኛውን ሲያባርረው
    የሠራተኛ ቅነሳ ሲደረግ
    ድርጅቱ በመክሰሩ/በሌላ ምክንያት ለዘለቄታው ሲዘጋ
    ያለማስጠንቀቂያ ሥራ ለሚለቅ ሠራተኛ ስለሚሰጥ ካሣ
    አሠሪው ወይም የሥራ መሪው የሠራተኛውን ሰብአዊ ክብርና ሞራል የሚነካ ወይም በወንጀል ሕጉ መሠረት የሚያስቀጣ ሌላ አድራጎት የፈጸመበት እንደሆነ፤
    ለሠራተኛው ደኅንነት ወይም ጤንነት የሚያሰጋና ሊደርስ የተቃረበ አደጋ መኖሩን አሠሪው እያወቀ ወይም አደጋውን ለመከላከል የሚያስፈልጉ እርምጃዎችን እንዲወስድ ኃላፊነት እርምጃዎችን ያልወሰደ እንደሆነ፤
    አሠሪው ለሠራተኛው መፈጸም ያለበትን ግዴታዎች በመደጋገም ያልፈጸመ እንደሆነ፡፡
    የሥራ ውሉን የሚያቋርጥ ሠራተኛ ከሥራ ስንብት ክፍያ በተጨማሪ የመጨረሻ ሣምንት አማካይ የቀን ደመወዙ በ30 ተባዝቶ ካሣ ይከፈለዋል፡፡ ይህ ድንጋጌ አግባብ ባለው የጡረታ ሕግ በተሸፈነ ሠራተኛ ላይም ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
    የሥራ ውሉን ያቋረጠው ሠራተኛው በአሠሪው ወይም በሥራ መሪው ወሲባዊ ትንኮሳ ወይም ጥቃት የተፈጸመበት እንደሆነ፤ ምክንያት የሆነ እንደሆነ ከሥራ ስንብት ክፍያው በተጨማሪ የቀን ደመወዙ በ90 ተባዝቶ ይከፈለዋል፡፡ይህ ድንጋጌ አግባብ ባለው የጡረታ ሕግ በተሸፈነ ሠራተኛ ላይም ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
    በነዚህ ምክንያቶች የሥራ ውሉን የሚያቋርጥ ሠራተኛ ውሉ የሚቋረጥበትን ምክንያትና ቀን በጽሑፍ ለአሠሪው ማስታወቅ አለበት፡፡
    በነዚህ ምክንያቶች የሥራ ውሉን ለማቋረጥ ያለው መብት ድርጊቱ ከተፈጸመ ወይም ሁኔታው ከተወገደ 15 የሥራ ቀናት በኋላ በይርጋ ይታገዳል፡፡
    የሥራ ውል ከሕግ ውጭ ሲቋረጥ
    ሠራተኛው በሠራተኞች ማኅበር አባል መሆኑ ወይም በማኅበሩ ሕጋዊ ተግባሮች ተካፋይ መሆኑ፤
    ሠራተኛው የሠራተኞች ተጠሪ ሆኖ ለመሥራት መፈለጉ ወይም መሥራቱ፤
    ሠራተኛው በሠሪው ላይ ቅሬታ ማቅረቡ ወይም በፍርድ ቤት በቀረበ ክስ ፤
    የሠራተኛው ብሔር፣ ፆታ፣ ሐይማኖት፣ የፖለቲካ አመለካከት፣ የጋብቻ ሁኔታ፣ ዘር፣ ቀለም፣ የቤተሰብ ኃላፊነት፣ የዘር ሐረግ፣ እርግዝና፣ አካል ጉዳተኝነት፣ ወይም ማኅበራዊ አቋም፡፡
    በእነዚህ ምክንያቶች አሠሪው የሥራ ውሉን ቢያቋርጥ ሠራተኛውን ወደ ሥራው የመመለስ ግዴታ አለበት፡፡ ሆኖም ሠራተኛው ወደ ሥራው ለመመለስ ካልፈለገ ካሣ እንዲከፈለው የመጠየቅ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
    ወደ ሥራው የማይመለስ ሠራተኛ ከሥራ ስንብት ክፍያ በተጨማሪ የሚከተለውን ክፍያ ያገኛል፡፡ ይህ ድንጋጌ አግባብ ባለው የጡረታ ሕግ የተሸፈነ ቢሆንም:-
    ሀ) ላልተወሰነ ጊዜ የተደረገ የሥራ ውል ከሕግ ውጭ ሲቋረጥ የሠራተኛው አማካይ የቀን ደመወዙ በ180 ተባዝቶ ይከፈለዋል፣
    ለ) ለተወሰነ ጊዜ /ሥራ የተደረገ የሥራ ውል ከሕግ ውጭ ሲቋረጥ ሠራተኛው የውሉ ጊዜ ወይም ሥራ እስኪያልቅ ቢቆይ ኖሮ ያገኝ የነበረውን ደመወዝ የሚያህል ገንዘብ ይከፈለዋል፡፡ ሆኖም ካሣው የሠራተኛው ማዕከላዊ የቀን ደመወዙ በ180 ተባዝቶ ከሚያገኘው ውጤት መብለጥ የለበትም፡፡
    ወደ ሥራው እንዲመለስ በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሥራ ክርክር ችሎት የተወሰነለት ሠራተኛ ከ6 ወር የማይበልጥ ውዝፍ ደመወዝ እንዲከፈለው ፍርድ ቤቱ ይወስንለታል፡፡ ጉዳዩ በይግባኝ ታይቶ የሠራተኛው ወደ ሥራ መመለስ ውሣኔ ከፀና ከ1 ዓመት ያልበለጠ ውዝፍ ደመወዝ ፍርድ ቤቱ ለሠራተኛው ይወስንለታል፡፡
    በሕግ በተደነገገው መሠረት የሥራ ውልን ስለማቋረጥ
    በመክሰር /በሌላ ምክንያት ድርጅቱ ለዘለቄታው ሲዘጋ (በአንቀጽ 24 (4))
    በአንቀጽ 29 መሠረት የሥራ ውል ሲቋረጥ
    ከስራ ስንብት ክፍያ በተጨማሪ የሠራተኛው የመጨረሻ ሣምንት አማካይ የቀን ደመወዝ በ60 ተባዝቶ ይከፈለዋል፡፡
    ማስጠንቀቂያ የመስጠት ሥነ ሥርዓት
    በአሰሪው/በሰራተኛው የሚሰጥ ማስጠንቀቂያ በጽሑፍ መሆን አለበት፡፡ ማስጠንቀቂያውም ውሉ የሚቋረጥበትን ምክንያት እና ቀን መግለጽ አለበት፡፡
    በአሠሪው /በወኪሉ የሚሰጥ ማስጠንቀቂያ ለሠራተኛው በእጁ መሰጠት አለበት፡፡ ሠራተኛውን ማግኘት የማይቻል ከሆነ ወይም ማስጠንቀቂያውን ለመቀበል ፈቃደኛ ካልሆነ ግን ማስጠንቀቂያው ሠራተኛው በሚገኝበት የሥራ ቦታ ለ10 ተከታታይ ቀናት ግልጽ በሆነ የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ መለጠፍ ይኖርበታል፡፡
    በሠራተኛው የሚሰጥ ማስጠንቀቂያ ለአሠሪው /ለአሠሪው ወኪል መስጠት ወይም ለድርጅቱ መዝገብ ቤት ገቢ መደረግ አለበት
    የማስጠንቀቂያ ጊዜ
    በአሠሪው የሚሰጠው የማስጠንቀቂያ ጊዜ እንደሚከተለው ይሆናል፤
    የሙከራ ጊዜውን የጨረሰና እስከ 1 ዓመት ያገለገለ ሠራተኛን በሚመለከት 1 ወር፤
    ከ1 ዓመት በላይ እስከ 9 ዓመት ያገለገለ ሠራተኛን በሚመለከት ረገድ 2ወር፤
    ከ9 ዓመት በላይ ያገለገለ ሠራተኛን በሚመለከት 3ወር፤
    የሙከራ ጊዜውን ጨርሶ በቅነሳ ምክንያት የሥራ ውሉ የሚቋረጥበት ሠራተኛን በሚመለከት 2ወር፡፡
    አሠሪው ለሠራተኛው ማስጠንቀቂያ ሳይሰጠው ያሰናበተ እንደሆነ በማስጠንቀቂያው ጊዜ ሊከፈል ይገባ የነበረውን ደመወዝ ለሠራተኛው ይከፍላል፡፡
    የማስጠንቀቂያ አስፈላጊ ሁኔታዎች ያላሟላ ሠራተኛ ለአሠሪው ካሣ ይከፍላል

ความคิดเห็น • 2

  • @Gezahegnofficial
    @Gezahegnofficial หลายเดือนก่อน

    Enamesgenaln berche !

    • @BekoTube-BM
      @BekoTube-BM  หลายเดือนก่อน

      እሺ ክብረት ይስጥልኝ