የቅባቱ ዕቃ

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 26 ส.ค. 2024
  • ይህ መልዕክት በመቀባትና በባህሪ መካከል ያለውን መስተጋብር በዳዊትና በሳዖል ሕይወት ውስጥ አንደኛ ሳሙኤል ላይ በመመሥራት የሚተነትን መልዕክት ነው። መልዕክቱ በወንጌላዊ ያሬድ ጥላሁን በሲልቨር ስፕሪንግ ሜሪላንድ በሚገኘው የሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ውስጥ የተላለፈ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቅባት የመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ሆኖ ተገልጿል፤ ቅባት የሚቀመጠው በቅባት ዕቃ ውስጥ እንደ ሆነ ሁሉ እኛም የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ዕቃዎች ነን። ሳዖልና ዳዊት በአንድ ሰው በሳሙኤል የተቀቡ ቢሆንም ሳዖል በብርሌ፣ ዳዊት በቀንድ እንደተቀቡ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ይነግረናል። የእኛም ባሕሪና ልባዊ ማንነት በቅባቱ ዕቃ ሊመሰል ይችላል። ዛሬ ልባችን ምን ይመስላል? ብርሌ ወይስ ቀንድ?

ความคิดเห็น • 123