እግዚአብሔር ይመጣል (መዝ. 50)

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 26 ส.ค. 2024
  • መዝሙር 50 በዳዊት ድንኳን ውስጥ መዘምራንና የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋቾችን እንዲመራ ከተሾመው ከአሳፍ ዝማሬዎች አንዱና የመጀመሪያው ነው። አሳፍ እግዚአብሔር ሊፈርድ ወደ ቤቱ እንደሚመጣ፣ ፍርድንም ከቤቱ እንደሚጀምር ይጽፋል። በሲና ተራራ ለእስራኤል ሕግን የሰጠው እግዚአብሔር ሕጉ መፈጸም አለመፈጸሙን ሊቆጣጠር ወደ ጽዮን፣ ወደ መቅደሱ እንደሚመጣ ይነግረናል። ሲመጣም የሚፈርደው በሁለት ነገሮች ነው። አንዱ ሕዝቡ ለእሱ ባለውና እርስበርሱ ባለው ፍቅር ነው። ይህም በአዲስ ኪዳን ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርት ጋር ይስማማል። የጌታ ትምህርት የሚጠቃለለው እግዚአብሔርን … ውደድ፤ ባልንጀራህን … ውደድ በሚል ነው። ዛሬም ጌታ ፍርድን ከቤቱ እንደሚጀምር ጴጥሮስ ይነግረናል። ፍርዱም የሚመዘነው ለጌታ ባለንና እርስበርስ ባለን ፍቅር ነው። ይህ መልዕክት ጁላይ 22፣ 2021 በፎር ኮርነርስ ቤተክርስቲያን ሲልቨር ስፕሪንግ፣ ሜሪላንድ የተላለፈ ሲሆን ከልብ ለሚሰሙት መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለው የጊዜው ቃል ነው።
    www.goldenoil.org

ความคิดเห็น • 78