የጌታ ወዳጅ አባ ቢሾይ / Aba Bishoy

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 10 ก.ย. 2024
  • አባ ቢሾይ
    ✨ አባ ቢሾይ የበቁና ክርስቶስ የሚያናግራቸው አባት ነበሩ። ከዕለታት በአንዱ ቀን የገዳሙ መነኮሳት አባ ቢሾይን ክርስቶስ ለኛም ይገለጥልን ዘንድ ንገሩልን ይሏቸዋል። እሳቸውም እሺ ይላሉ። ማታ ሲጸልዩ ክርስቶስ መጣ ከዛ እሷቸው ጌታ ሆይ ለወንድሞቼ መነኮሳት ተገለጥላቸው አሉት። ጌታም ቢሾይ ልጄ ነገ በተራራው ላይ በ6 ሰዓት እንደምገለጥላቸው ንገራቸው አላቸውና ተሰወረ። ቢሾይም ለመነኮሳቱ ነገሯቸው።
    - ከቀኑ 6 ሰዓት በሆነ ጊዜም መነኮሳቱ ክርስቶስን ለማየት ወደ ተራራ ሲሮጡ አንድ አቅመ ደካማ ሽማግሌ ተራራው ስር ቁጭ ብለው፥ "ልጆቼ እባካቹ ጌታን ላየው እሻለውና እኔንም ውሰዱኝ" እያሉ ለመኗቸው። መነኮሳቱ ግን አንተን ይዘን ታዘገየናለህ ሳናየው ታሳልፈናለህ እኛ ቸኩለናል እያሉ እያለፏቸው ሄዱ። መጨረሻ ላይ አባ ቢሾይ ሲመጡ እነዛ ሽማግሌ አባ ቢሾይን "እባክህ ውሰደኝ" አሏቸው።

    - አባ ቢሾይም አቅፈዋቸው ጉዞ ጀምሩ ትንሽ ቆይተውም ሽማግሌው ሰውዬ ከበዷቸው ዝቅ ብለው ቢያዩዋቸው ሽማግሌው ወደ ወጣትነት ተቀየሩ እጁና እግሩን ሲያዩት ችንካር አለው። ደነገጡ! ክርስቶስ ነው። ቢሾይ ልጄ እንዳከበርከኝ አከብርሀለው። ለመነኮሳት ወንድሞችህ ተገልጬ እንደነበርና በንቀታቸው ምክንያት እንዳለፍኳቸው ንገራቸው።
    ✨ አጠገባቹ ያለውን ሳትወዱና ሳታከብሩ እኔን እንወድሃለን እናከብርሀለን ብትሉ ፍቅራቹ ውሸት ነው በላቸው ብሎ ክርስቶሰ ተሰወረ። ሰውን ስናከብር ፈጣሪ ያከብረናል ሰው የፈጣሪ አምሳል ነውና። ፈጣሪን በቀጥታ አናገኘውም በሰው ውስጥ ግን እናገኘዋለንና ሰውን እናክብር። ለዚህ ነው አምላካችን መድኃኔዓለም ክርስቶስ ለፍርድ ሲመጣ ከነዚ ከታናናሾች ለአንዱ ያደረጋችሁት ለኔ እንዳደረጋችሁት እቆጥረዋለው ያለን።
    ©መጽሐፈ መነኮሳት

ความคิดเห็น • 908