5.2 ቢሊዮን ብር የተመደበለት የፌደራል መንግስት ቢሮዎች ግንባታ ፕሮጀክት፤ የአዋጭነት ጥያቄ ቀረበበት

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 24 มิ.ย. 2024
  • የፌደራል መንግስት ለ2017 ካዘጋጀው በጀት ውስጥ፤ 5.2 ቢሊዮን ብር ያህሉን ለቢሮዎች ግንባታ ፕሮጀክት መመደቡ የአዋጭነት ጥያቄ አስነሳ። የቢሮዎች ግንባታ መንግስት ለኪራይ የሚያወጣውን “ከፍተኛ ወጪ” እንደሚያድን የገለጸው የገንዘብ ሚኒስቴር፤ ፕሮጀክቱ “እንደሌሎቹ ሴክተሮች የአዋጭነት ጥናት ተረጋግጦ የሚኬድበት አይደለም” ብሏል።
    የመንግስት ቢሮዎች ግንባታ ጉዳይ ጥያቄ የተነሳበት ትላንት ሰኞ ሰኔ 17፤ 2016፤ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተደረገ የበጀት ውይይት ላይ ነው። ውይይቱን የጠራው የምክር ቤቱ የፕላን፣ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፤ የገንዘብ ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች ማብራሪያ እንዲሰጡባቸው 12 ጥያቄዎችን አዘጋጅቶ ነበር።
    የቋሚ ኮሚቴው አባል በሆኑት ዶ/ር ሚልኪያስ አየለ አማካኝነት በንባብ ከቀረቡት ከእነዚህ ጥያቄዎች የመጨረሻው፤ ለመንግስት ቢሮዎች ግንባታ ፕሮጀክት “የቅድመ ግንባታ የአዋጭነት ጥናት” መከናወኑን ያጠየቀ ነበር። ዶ/ር ሚልኪያስ የግንባታ ፕሮጀክቱ “አግባብነት ካለው ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የአዋጭነት ማረጋገጫ ሰነድ ወይም ሰርተፍኬት” ስለመሰጠቱም ማብራሪያ ጠይቀዋል።
    (ኢትዮጲያ ኢንሳይደር)
    ተጨማሪውን ለማንበብ ይሄን ሊንክ ይጫኑ ethiopiainside...
    -------------------------------------------------------------------------------------------
    የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ትኩስ ዜናዎችን እና ወቅታዊ ዘገባዎችን ለመከታተል፦
    ድረ ገጽ ፦ ethiopiainsider...​
    ፌስቡክ ፦ / ethiopiainsider
    ትዊተር (ኤክስ) ፦ / ethiopiainsider
    ቴሌግራም፦ t.me/EthiopiaI...
    ቲክቶክ፦ / ethiopiainsider

ความคิดเห็น •